በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የወጣቶች ጥያቄ

ልጠመቅ?—ክፍል 2፦ ለጥምቀት መዘጋጀት

ልጠመቅ?—ክፍል 2፦ ለጥምቀት መዘጋጀት

 የመጽሐፍ ቅዱስን መሥፈርቶች እየተከተልክ እንዲሁም ከአምላክ ጋር ወዳጅነት ለመመሥረት እየጣርክ ከሆነ ስለ ጥምቀት ማሰብህ አይቀርም። ታዲያ ይህን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆንህን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? a

በዚህ ርዕስ ውስጥ

 ምን ያህል እውቀት ሊኖረኝ ይገባል?

 ለጥምቀት መዘጋጀት ሲባል በትምህርት ቤት ፈተና ለማለፍ እንደሚደረገው አንዳንድ መረጃዎችን መሸምደድ ማለት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ‘የማሰብ ችሎታህን በመጠቀም’ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ነገር እውነት ስለመሆኑ ያለህን እምነት ማጠናከር ይኖርብሃል። (ሮም 12:1) ለምሳሌ ያህል፦

 ምን ዓይነት ምግባር ሊኖረኝ ይገባል?

 መጠመቅ እንድትችል ፍጹም መሆን አይጠበቅብህም። ሆኖም ‘ክፉ ከሆነ ነገር መራቅና መልካም የሆነውን ማድረግ’ ከልብህ እንደምትፈልግ በምግባርህ ማሳየት ይኖርብሃል። (መዝሙር 34:14) ለምሳሌ ያህል፦

  •   አኗኗርህ ከይሖዋ መሥፈርቶች ጋር የሚስማማ ነው?

     መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ጥሩ ሕሊና ይኑራችሁ።”—1 ጴጥሮስ 3:16

     ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘“ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር መለየት” እንድችል የማስተዋል ችሎታዬን እንዳሠለጠንኩ ያሳየሁት እንዴት ነው?’ (ዕብራውያን 5:14) ‘የእኩዮቼን መጥፎ ተጽዕኖ የተቋቋምኩባቸውን ጊዜያት መጥቀስ እችላለሁ? ጓደኛ የማደርገው ትክክል የሆነውን ነገር እንዳደርግ የሚያበረታቱኝን ሰዎች ነው?’—ምሳሌ 13:20

     እገዛ ትፈልጋለህ?ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

  •   ለድርጊትህ ኃላፊነት ትወስዳለህ?

     መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለአምላክ መልስ እንሰጣለን።”—ሮም 14:12

     ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ለራሴም ሆነ ለሌሎች ሐቀኛ ነኝ?’ (ዕብራውያን 13:18) ‘ስህተቴን አምናለሁ? ወይስ ስህተቴን ለመሸፋፈን ወይም በሌሎች ለማሳበብ እሞክራለሁ?’—ምሳሌ 28:13

     እገዛ ትፈልጋለህ?ስህተት ስሠራ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

  •   ከይሖዋ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከር ጥረት እያደረግክ ነው?

     መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል።”—ያዕቆብ 4:8

     ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘ወደ ይሖዋ ለመቅረብ ስል የትኞቹን እርምጃዎች እየወሰድኩ ነው?’ ለምሳሌ ‘መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትሬ አነብባለሁ?’ (መዝሙር 1:1, 2) ‘አዘውትሬ እጸልያለሁ?’ (1 ተሰሎንቄ 5:17) ‘በደፈናው ከመጸለይ ባለፈ ዝርዝር ጉዳዮችን እጠቅሳለሁ? ጓደኞቼ የይሖዋ ወዳጆች ናቸው?’—መዝሙር 15:1, 4

     እገዛ ትፈልጋለህ?መጽሐፍ ቅዱስ ሊጠቅመኝ የሚችለው እንዴት ነው?—ክፍል 2፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ” እና “መጸለይ ጥቅም አለው?” የሚሉትን ርዕሶች ተመልከት።

 ጠቃሚ ምክር፦ ለጥምቀት ለመዘጋጀት እንዲረዳህ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 2 የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 37⁠ን አንብብ። በተለይ በገጽ 308 እና 309 ላይ ለሚገኘው የመልመጃ ሣጥን ትኩረት ስጠው።

a ራስን ለአምላክ መወሰንና መጠመቅ ስላለው ትርጉም እንዲሁም አስፈላጊነት የሚናገረውን “ልጠመቅ?—ክፍል 1” የሚለውን ርዕስ አንብብ።