በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ መሣሪያዎች

ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ መሣሪያዎችን የያዘው ቤተ መጻሕፍታችን፣ መጽሐፍ ቅዱስን ጠለቅ ብለህ ለማጥናትና የአምላክን ቃል ይበልጥ ለመረዳት ያግዝሃል። ለጥናትህ እንዲያግዙህ በማሰብ የመጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፒዲያ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት መፍቻና ሌሎች ነፃ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ መሣሪያዎችም አዘጋጅተንልሃል።

መጽሐፍ ቅዱስን ኢንተርኔት ላይ እንዳለህ አንብብ

ትክክለኛና ለመረዳት ቀላል የሆነውን የአዲስ ዓለም ትርጉም አንዳንድ ገጽታዎች እንድትመለከት እንጋብዝሃለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛ ቪዲዮዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያዎች

ከእያንዳንዱ የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎች።

መሠረታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች

እነዚህ አጫጭር ቪዲዮዎች ለሚከተሉት ወሳኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ፦ አምላክ ምድርን የፈጠረው ለምንድን ነው? የሞቱ ሰዎች በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? አምላክ መከራ እንዲኖር የፈቀደውስ ለምንድን ነው?

አጋዥ የመጽሐፍ ቅዱስ ማጥኛዎች እና ማመሣከሪያዎች

የመጽሐፍ ቅዱስ ኢንሳይክሎፒዲያ

ጠለቅ ብሎ ማስተዋል በሺዎች የሚቆጠሩ ርዕሰ ጉዳዮችን በሰፊው ይዳስሳል። ከእነዚህ መካከል ሰዎች፣ ቦታዎች፣ ዕፀዋት፣ እንስሳት፣ ወሳኝ ክንውኖች እና መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ አባባሎች ይገኙበታል። ይህን ኢንሳይክሎፒዲያ በፒዲኤፍ ፎርማት ስታወርድ ካርታዎች፣ ፎቶግራፎች፣ ሥዕላዊ መግለጫዎች እንዲሁም የርዕሰ ጉዳይና የጥቅስ ማውጫ ማግኘት ትችላለህ።

የመጽሐፍ ቅዱስ ፍሬ ሐሳብ

መጽሐፍ ቅዱስ የያዘው መልእክት ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስን ፍሬ ሐሳብ በአጭሩ ይዟል፤ ይህ ብሮሹር የመጽሐፍ ቅዱስን አጠቃላይ መልእክት ለመረዳት ያስችላል።

የመጽሐፍ ቅዱስ አትላስ

“መልካሚቱን ምድር ተመልከቱ” የተባለው አትላስ ብዙ ካርታዎችና ሠንጠረዦች ይዟል፤ አትላሱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ ቦታዎችን በተለይም ተስፋይቱ ምድር በተለያዩ ዘመናት የነበራትን ይዞታ ያሳያል።

ለየዕለቱ የሚሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

ቅዱሳን መጻሕፍትን በየዕለቱ መመርመር የተባለው ቡክሌት ለእያንዳንዱ ቀን አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እንዲሁም ለጥቅሱ የሚሆን ማብራሪያ ይዟል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም

ይህ ፕሮግራም ለየዕለቱ የሚሆን የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ፕሮግራም ይዟል፤ በታሪክ ቅደም ተከተል ለማንበብ የሚያስችል እንዲሁም ለጀማሪ የሚሆን ፕሮግራምም አካትቷል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ማውጣት የሚቻለው እንዴት ነው?

ይህ ዝርዝር አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች 66ቱን የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በሚያስቀምጡበት ቅደም ተከተል መሠረት የተዘጋጀ ነው። ከመጽሐፉ ስም በኋላ የሚገኘው የመጀመሪያው ቁጥር ምዕራፉን፣ ሁለተኛው ደግሞ ቁጥሩን ይናገራል።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

መጽሐፍ ቅዱስ አምላክን፣ ኢየሱስን፣ ጸሎትን፣ ቤተሰብን፣ መከራንና የመሳሰሉትን ጉዳዮች አስመልክቶ ምን እንደሚል እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው

በሰፊው የሚታወቁ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና አባባሎችን ትክክለኛ ትርጉም እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት (አዲስ ዊንዶው ክፈት)

የይሖዋ ምሥክሮች ያዘጋጇቸውን ጽሑፎች በመጠቀም ኢንተርኔት ላይ እንዳለህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምርምር አድርግ

መጽሐፍ ቅዱስን አስተማሪ ተመድቦልህ አጥና

የይሖዋ ምሥክሮች የሚሰጡት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ምን ይመስላል?

የይሖዋ ምሥክሮች ያለክፍያ በሚሰጡት አሳታፊ ኮርስ ላይ የፈለግከውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም መጠቀም ትችላለህ። ከፈለግክ ሙሉውን ቤተሰብህን ወይም ጓደኞችህን በጥናቱ ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ነፃነት ይሰማህ።

አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ትፈልጋለህ?

መልስ ያላገኘህለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄ አለ? ወይም ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትፈልጋለህ? አንድ የይሖዋ ምሥክር እንዲያነጋግርህ ጥያቄ አቅርብ።