መዝሙር 1:1-6

  • ተቃራኒ የሆኑ ሁለት መንገዶች

    • የአምላክን ሕግ ማንበብ ያስደስታል (2)

    • ጻድቃን እንደሚያፈራ ዛፍ ናቸው (3)

    • ክፉዎች ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው (4)

1  በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣በኃጢአተኞች መንገድ+ የማይቆም፣በፌዘኞችም+ ወንበር የማይቀመጥ ሰው ደስተኛ ነው።   ይልቁንም በይሖዋ ሕግ ደስ ይለዋል፤+ሕጉንም በቀንና በሌሊት በለሆሳስ ያነበዋል።*+   በጅረቶች ዳር እንደተተከለ፣ፍሬውን በወቅቱ እንደሚሰጥ፣ቅጠሉም እንደማይጠወልግ ዛፍ ይሆናል። የሚሠራውም ሁሉ ይሳካለታል።+   ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፤ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ገለባ ናቸው።   ከዚህም የተነሳ ክፉዎች በፍርድ ፊት ለዘለቄታው አይቆሙም፤+ኃጢአተኞችም በጻድቃን ጉባኤ ጸንተው አይቆሙም።+   ይሖዋ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፤+የክፉዎች መንገድ ግን ይጠፋል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያሰላስለዋል።”