መዝሙር 98:1-9

  • ይሖዋ፣ አዳኝና ጻድቅ ፈራጅ ነው

    • የይሖዋ ማዳን ታውቋል (2, 3)

ማህሌት። 98  ለይሖዋ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፤+እሱ አስደናቂ ነገሮች አድርጓልና።+ ቀኝ እጁ፣ አዎ ቅዱስ ክንዱ መዳን አስገኝቷል።*+   ይሖዋ ማዳኑ እንዲታወቅ አድርጓል፤+በብሔራት ፊት ጽድቁን ገልጧል።+   ለእስራኤል ቤት ታማኝ ፍቅርና ታማኝነት ለማሳየት የገባውን ቃል አስታውሷል።+ የምድር ዳርቻዎች ሁሉ የአምላካችንን ማዳን* አይተዋል።+   ምድር ሁሉ፣ ለይሖዋ በድል አድራጊነት እልል በሉ። ደስ ይበላችሁ፤ ደግሞም እልል በሉ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩ።+   ለይሖዋ በበገና የውዳሴ መዝሙር ዘምሩ፤በበገናና ደስ በሚል ዜማ ዘምሩለት።   በእምቢልታና በቀንደ መለከት ድምፅ+በንጉሡ በይሖዋ ፊት በድል አድራጊነት እልል በሉ።   ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ፣መሬትና* በላይዋ የሚኖር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰሙ።   ወንዞች በእጃቸው ያጨብጭቡ፤ተራሮችም በአንድነት በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤+   እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።* በዓለም* ላይ በጽድቅ፣በሕዝቦችም ላይ በትክክል ይፈርዳል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ድል አቀዳጅቶታል።”
ወይም “የአምላካችንን ድል።”
ወይም “ፍሬያማ የሆነችው ምድርና።”
ወይም “መጥቷልና።”
ወይም “ፍሬያማ በሆነችው ምድር።”