መዝሙር 100:1-5

  • ፈጣሪን ማመስገን

    • “ይሖዋን በደስታ አገልግሉት” (2)

    • ‘የሠራን አምላክ ነው’ (3)

የምስጋና ማህሌት። 100  ምድር ሁሉ፣ በድል አድራጊነት ለይሖዋ እልል በሉ።+   ይሖዋን በደስታ አገልግሉት።+ በእልልታ ወደ ፊቱ ቅረቡ።   ይሖዋ፣ አምላክ መሆኑን እወቁ።*+ የሠራን እሱ ነው፤ እኛም የእሱ ንብረት ነን።*+ እኛ ሕዝቡና የማሰማሪያው በጎች ነን።+   በምስጋና ወደ በሮቹ፣በውዳሴም ወደ ቅጥር ግቢዎቹ ግቡ።+ ምስጋና አቅርቡለት፤ ስሙንም አወድሱ።+   ይሖዋ ጥሩ ነውና፤+ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም፣ታማኝነቱም ከትውልድ እስከ ትውልድ ጸንቶ ይኖራል።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እውቅና ስጡ።”
“እኛም አይደለንም” ማለትም ሊሆን ይችላል።