መዝሙር 36:1-12

  • የአምላክ ታማኝ ፍቅር

    • ክፉ ሰው አምላክን አይፈራም (1)

    • አምላክ የሕይወት ምንጭ ነው (9)

    • “በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን” (9)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ። የይሖዋ አገልጋይ የዳዊት መዝሙር። 36  ኃጢአት፣ ክፉውን ሰው በልቡ ውስጥ ሆኖ ያናግረዋል፤በዓይኖቹ ፊት አምላክን መፍራት የሚባል ነገር የለም።+   ስህተቱ ምን እንደሆነ ተረድቶ የሠራውን ነገር እንዳይጠላው፣ለራሱ ባለው አመለካከት ራሱን እጅግ ይሸነግላልና።+   ከአፉ የሚወጣው የክፋትና የሽንገላ ቃል ነው፤መልካም ነገር ለማድረግ ማስተዋል የለውም።   በአልጋው ላይ ሆኖ እንኳ ክፋትን ያውጠነጥናል። ጥሩ ባልሆነ መንገድ ላይ ይቆማል፤መጥፎ የሆነውን ነገር ገሸሽ አያደርግም።   ይሖዋ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ እስከ ሰማያት፣+ታማኝነትህ እስከ ደመናት ይደርሳል።   ጽድቅህ ግርማ እንደተላበሱ ተራሮች* ነው፤+ፍርዶችህ እንደ ጥልቅ ባሕር ናቸው።+ ይሖዋ ሆይ፣ አንተ ሰውንና እንስሳን ትጠብቃለህ።*+   አምላክ ሆይ፣ ታማኝ ፍቅርህ ምንኛ ክቡር ነው!+ የሰው ልጆች በክንፎችህ ጥላ ሥር ይሸሸጋሉ።+   በቤትህ ውስጥ ተትረፍርፎ የሚገኘውን ነገር* እስኪረኩ ድረስ ይጠጣሉ፤+መልካም ነገሮች ከሚፈስሱበት ወንዝህ ታጠጣቸዋለህ።+   የሕይወት ምንጭ ከአንተ ዘንድ ነው፤+በብርሃንህ፣ ብርሃን ማየት እንችላለን።+ 10  ለሚያውቁህ ታማኝ ፍቅርህን፣ቀና ልብ ላላቸው ደግሞ ጽድቅህን ዘወትር አሳያቸው።+ 11  የትዕቢተኛ እግር እንዲረግጠኝ፣ወይም የክፉዎች እጅ እንዲያፈናቅለኝ አትፍቀድ። 12  ክፉ አድራጊዎች የት እንደወደቁ ተመልከት፤ተመተው ወድቀዋል፤ መነሳትም አይችሉም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሰውንና እንስሳን ታድናለህ።”
ቃል በቃል “እንደ አምላክ ተራሮች።”
ቃል በቃል “ስቡን።”