መዝሙር 146:1-10

  • በሰው ሳይሆን በአምላክ መታመን

    • ሰው ሲሞት ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል (4)

    • አምላክ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል (8)

146  ያህን አወድሱ!*+ ሁለንተናዬ* ይሖዋን ያወድስ።+   በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይሖዋን አወድሳለሁ። በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የውዳሴ መዝሙር እዘምራለሁ።   በመኳንንትም* ሆነማዳን በማይችሉ ሰዎች አትታመኑ።+   መንፈሱ* ትወጣለች፤ ወደ መሬት ይመለሳል፤+በዚያው ቀን ሐሳቡ ሁሉ ይጠፋል።+   የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ፣+በአምላኩ በይሖዋ ተስፋ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው፤+   እሱ የሰማይ፣ የምድር፣የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ነው፤+ደግሞም ለዘላለም ታማኝ ነው፤+   ግፍ ለተፈጸመባቸው ፍትሕ ያሰፍናል፤ለተራቡት ምግብ ይሰጣል።+ ይሖዋ እስረኞችን ነፃ ያወጣል።*+   ይሖዋ የዓይነ ስውራንን ዓይን ያበራል፤+ይሖዋ ያጎነበሱትን ቀና ያደርጋል፤+ይሖዋ ጻድቃንን ይወዳል።   ይሖዋ የባዕድ አገር ሰዎችን ይጠብቃል፤አባት የሌለውን ልጅና መበለቲቱን ይደግፋል፤+የክፉዎችን ዕቅድ ግን ያጨናግፋል።*+ 10  ይሖዋ ለዘላለም ይነግሣል፤+ጽዮን ሆይ፣ አምላክሽ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይገዛል። ያህን አወድሱ!*

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።
ወይም “ነፍሴ።”
ወይም “በታላላቅ ሰዎችም።”
ወይም “እስትንፋሱ።”
ቃል በቃል “የታሰሩትን ይፈታል።”
ወይም “የክፉዎችን መንገድ ግን ያጣምማል።”
ወይም “ሃሌሉያህ!” “ያህ” የይሖዋ ስም አጭር መጠሪያ ነው።