በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በእምነታቸው ምሰሏቸው—የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች የሚመስጥ ታሪክ

ይህ ዓምድ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱ የእምነት ሰዎችን ታሪክ የያዘ ነው። a ስለ እነዚህ ሰዎች ታሪክና ስላሳዩት እምነት ስታነብ እምነትህ ይጠናከራል፤ እንዲሁም ከአምላክ ጋር ይበልጥ ትቀራረባለህ።

ከታማኝ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለታሪኮች ተጨማሪ ትምህርት እንድታገኝ በማሰብ በእምነታቸው ምሰሏቸው የተሰኙ ተከታታይ ቪዲዮዎችም አዘጋጅተናል።

a በዚህ ዓምድ ሥር የሚገኙት ርዕሶች፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኙ አንዳንድ ዝርዝር ሐሳቦችን ይጠቅሳሉ፤ ይህ የተደረገው አንባቢው በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ በዓይነ ሕሊናው እንዲስልና በታሪኩ እንዲመሰጥ ለመርዳት ነው። እነዚህ ዝርዝር ሐሳቦች የተካተቱት በጥንቃቄ ምርምር ከተደረገባቸው በኋላ ነው፤ በመሆኑም ሐሳቦቹ ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባም ሆነ ከታሪካዊ ማስረጃዎችና ከአርኪኦሎጂ ግኝቶች ጋር የሚስማሙ ናቸው።

ከፍጥረት እስከ ጥፋት ውኃ

አቤል​—‘ቢሞትም እንኳ አሁንም ይናገራል’

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አቤል የሚናገረው ነገር በጣም ጥቂት ነው፤ ታዲያ ስለ እሱም ሆነ ስላሳየው እምነት ያን ያህል የምንማረው ነገር ይኖራል?

ሄኖክ—‘አምላክን በሚገባ ደስ አሰኝቷል’

የምታስተዳድረው ቤተሰብ ካለህ ወይም ትክክል እንደሆነ ለምታውቀው ነገር ጥብቅና እንድትቆም የሚጠይቅ ሁኔታ ካጋጠመህ ሄኖክ ካሳየው እምነት ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

ኖኅ—“ከእውነተኛው አምላክ ጋር ይሄድ ነበር”

ኖኅና ሚስቱ ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች ገጥመዋቸዋል? መርከቡን በሚገነቡበት ወቅት እምነት ያሳዩት እንዴት ነው?

ኖኅ—“ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር” ዳነ

ኖኅና ቤተሰቡ የሰው ዘር በጨለማ የተዋጠበትን ወቅት ያሳለፉት እንዴት ነው?

ከጥፋት ውኃ እስራኤላውያን ከግብፅ እስከወጡበት

አብርሃም​—‘ለሚያምኑ ሁሉ አባት ሆኗል’

አብርሃም እምነት ያሳየው እንዴት ነው? የአብርሃምን እምነት መምሰል የምትችልባቸው መንገዶች የትኞቹ ናቸው?

ሣራ—“አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”

በግብፅ የነበሩት የፈርዖን መኳንንት ሣራ በጣም ውብ እንደሆነች ተመለከቱ። ከዚያ በኋላ የሆነው ነገር ያስገርምህ ይሆናል።

ሣራ—አምላክ “ልዕልት” ብሎ ጠርቷታል

ሣራ እንዲህ ተብላ መጠራቷ ተገቢ የሆነው ለምንድን ነው?

ርብቃ—“አዎ፣ እሄዳለሁ”

ርብቃ እምነት ብቻ ሳይሆን ሌሎች ግሩም ባሕርያትን አንጸባርቃለች።

ዮሴፍ—“ያየሁትን ሕልም ልንገራችሁ አድምጡኝ”

ዮሴፍ የነበረው ውጥንቅጡ የወጣ የቤተሰብ ሕይወት በዛሬው ጊዜ ሁለተኛ ትዳር ለመሠረቱ ቤተሰቦች ጥሩ ትምህርት ይሰጣል።

ዮሴፍ—‘እንዴት ይህን ክፉ ድርጊት እፈጽማለሁ?’

ዮሴፍ፣ የጲጥፋራ ሚስት ከእሷ ጋር ብልግና እንዲፈጽም የምታቀርብለትን ውትወታ መቋቋም የቻለው እንዴት ነው?

ዮሴፍ—“ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?”

ዮሴፍ የግብፅን የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃ፣ የዳቦ ጋጋሪዎቹን አለቃና የፈርዖንን ሕልሞች እንዲፈታ ያስቻለው ምንድን ነው? እስረኛ የነበረው ዮሴፍ በአንድ ጀምበር ከፍተኛ ባለሥልጣን መሆን የቻለው እንዴት ነበር?

ኢዮብ—“ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!”

የኢዮብ ታሪክ መከራ፣ ችግር ወይም ፈተና ሲያጋጥመን የሚረዳን እንዴት ነው?

ኢዮብ—ይሖዋ ከሥቃዩ ገላገለው

ሰይጣንን ለማሳፈርና አፍቃሪ የሆነውን አምላካችንን ይሖዋን ለማስደሰት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ኢዮብን በእምነቱ መምሰል ነው!

ሚርያም—“ለይሖዋ ዘምሩ”!

ነቢዪቷ ሚርያም የእስራኤልን ሴቶች በመምራት በቀይ ባሕር ዳርቻ የድል መዝሙር ዘመረች። የእሷ ታሪክ ድፍረትን፣ እምነትንና ትሕትናን አስመልክቶ ያስተምረናል።

እስራኤላውያን ከግብፅ ከወጡበት እስከ መጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ

ረዓብ—“በሥራ ጻድቅ ተብላ” ተጠርታለች

የረዓብ ታሪክ ይሖዋ ለሁሉም ሰው ትኩረት እንደሚሰጥ የሚያሳየው እንዴት ነው? እሷ ካሳየችው እምነት ምን እንማራለን?

ዲቦራ—“እኔ በእስራኤል እናት ሆኜ እስክነሳ”

ስለ ዲቦራ ከሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ስለ እምነትና ድፍረት ምን እንማራለን?

ሩት​—“ወደምትሄጂበት እሄዳለሁ”

ሩት ቤተሰቧንና የትውልድ አገሯን ትታ ለመሄድ ፈቃደኛ የሆነችው ለምንድን ነው? በይሖዋ ዘንድ እንድትወደድ ያደረጓት ባሕርያት የትኞቹ ናቸው?

ሩት​—“ምግባረ መልካም ሴት”

የሩትና የቦዔዝ ጋብቻ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ለምንድን ነው? ከሩትና ከኑኃሚን ታሪክ ስለ ቤተሰብ ዝምድና ምን እንማራለን?

ሐና—ለአምላክ የልቧን አውጥታ ነገረችው

ሐና በይሖዋ ላይ እምነት ስለነበራት መፍትሔ የሌለው የሚመስለውን ችግሯን መወጣት ችላለች።

ሳሙኤል—‘በይሖዋ ፊት እያደገ ሄደ’

የሳሙኤልን የልጅነት ሕይወት የተለየ የሚያደርገው ምንድን ነው? በማደሪያው ድንኳን ውስጥ በሚኖርበት ወቅት እምነቱ ጠንካራ እንዲሆን የረዳው ምንድን ነው?

ሳሙኤል—ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ቢያጋጥሙትም ጸንቷል

ሁላችንም እምነታችንን የሚፈታተኑ መከራዎችና ተስፋ የሚያስቆርጡ ሁኔታዎች ያጋጥሙናል። የሳሙኤል ጽናት ምን ያስተምረናል?

ከመጀመሪያው የእስራኤል ንጉሥ እስከ ኢየሱስ ልደት

ዮናታን—‘ይሖዋ ከማዳን የሚያግደው ነገር የለም’

ዮናታን በአንድ የፍልስጤማውያን የጦር ሰፈር በሚገኙ በሚገባ በታጠቁ ወታደሮች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ታሪካዊ ድል ተጎናጽፏል።

ዳዊት—“ውጊያው የይሖዋ ነው”

ዳዊት ጎልያድን እንዲያሸንፍ የረዳው ምንድን ነው?

ዳዊት እና ዮናታን—“የጠበቀ ወዳጅነት መሠረቱ”

የተለያየ አስተዳደግና ዕድሜ ያላቸው ሁለት ሰዎች ይህን ያህል የጠበቀ ወዳጅነት ሊመሠርቱ የቻሉት እንዴት ነው? የእነሱ ታሪክ ጥሩ ወዳጅነት ለመመሥረት የሚረዳህ እንዴት ነው?

አቢግያ—አስተዋይነት የተንጸባረቀበት እርምጃ ወስዳለች

አቢግያ ትዳሯ ጥሩ ባይሆንም ሁኔታውን ከያዘችበት መንገድ ምን እንማራለን?

ኤልያስ—ለንጹሕ አምልኮ ጥብቅና ቆሟል

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረውን ትምህርት የሚቃወሙ ሰዎች ሲያጋጥሙን የኤልያስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?

ኤልያስ—በንቃትና በትዕግሥት ተጠባብቋል

ነቢዩ ኤልያስ፣ ይሖዋ የገባውን ቃል የሚፈጽምበትን ጊዜ በትዕግሥት በሚጠባበቅበት ወቅት የጸሎት ሰው መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

ኤልያስ—አምላኩ አጽናንቶታል

ኤልያስ በከፍተኛ ፍርሃትና በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጦ ሞቱን እንዲመኝ ያደረጉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ኤልያስ—ግፍ በበዛበት ዘመን ጸንቶ ኖሯል

ግፍ ደርሶብህ ያውቃል? አምላክ ነገሮችን ሲያስተካክል ለማየት ትጓጓለህ? ታማኙን ኤልያስን መምሰል የምትችልባቸውን መንገዶች መርምር።

ኤልያስ—እስከ መጨረሻው ጸንቷል

ኤልያስ በታማኝነት በመጽናት ስለተወው ምሳሌ መመርመራችን እኛም አስቸጋሪ በሆኑ ወቅቶች እምነታችንን እንድናጠናክር ይረዳናል።

ዮናስ—ከሠራው ስህተት ተምሯል

ዮናስ የተሰጠውን ተልእኮ ከመፈጸም ይልቅ የፈራበትን ምክንያት ትረዳለታለህ? ከዮናስ ታሪክ ስለ ይሖዋ ትዕግሥትና ምሕረት ጠቃሚ ትምህርቶች እናገኛለን።

ዮናስ—ምሕረት ስለ ማሳየት ትምህርት አግኝቷል

የዮናስ ታሪክ ራሳችንን በሐቀኝነት እንድንመረምር ሊረዳን የሚችለው እንዴት ነው?

አስቴር—ለአምላክ ሕዝብ ጥብቅና ቆማለች

እንደ አስቴር የራስን ጥቅም መሥዋዕት በማድረግ ፍቅር ለማሳየት እምነትና ድፍረት ይጠይቃል።

አስቴር—ለሕዝቧ ስትል ሕይወቷን ለአደጋ ያጋለጠች ጠቢብና ደፋር ሴት

አስቴር ለይሖዋና ለሕዝቡ ስትል ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ምን እርምጃ ወስዳለች?

ከኢየሱስ ልደት እስከ ሐዋርያት ሞት

ማርያም—“እነሆ፣ እኔ የይሖዋ ባሪያ ነኝ!”

ማርያም ለመልአኩ ገብርኤል የሰጠችው መልስ ስለ እምነቷ ምን ይጠቁማል? ምን ሌሎች ግሩም ባሕርያትን አሳይታለች?

ማርያም—“በልቧ ታሰላስል ነበር”

ማርያም በቤተልሔም ያጋጠሟት ነገሮች ይሖዋ በገባው ቃል ላይ ያላትን እምነት አጠናክሮላታል።

ማርያም—የሐዘንን ሰይፍ ተቋቁማለች

በሐዘን “ሰይፍ” ተወግተህ ከሆነ የኢየሱስ እናት ማርያም የተወችው ምሳሌ ሊረዳህ ይችላል።

ዮሴፍ—ቤተሰቡን ጠብቋል፣ ተንከባክቧል፣ ኃላፊነቱን ተወጥቷል

ዮሴፍ ቤተሰቡን የጠበቀው በየትኞቹ መንገዶች ነው? ማርያምንና ኢየሱስን ይዞ ወደ ግብፅ የሄደው ለምንድን ነው?

ማርታ​—“አምናለሁ”

ማርታ ሐዘን ላይ በነበረችበት ወቅትም እንኳ አስደናቂ እምነት ያሳየችው እንዴት ነው?

መግደላዊቷ ማርያም—“ጌታን አየሁት!”

ይህች ታማኝ ሴት ለሌሎች ምሥራች የመናገር መብት ተሰጥቷታል።

ጴጥሮስ—ፍርሃትንና ጥርጣሬን ለማሸነፍ ታግሏል

ጥርጣሬ አጥፊ ሊሆን ይችላል። ይሁንና ጴጥሮስ ጥርጣሬንና ፍርሃትን አሸንፎ ኢየሱስን መከተል ችሏል።

ጴጥሮስ—ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷል

ጴጥሮስ እምነት ማዳበሩና ታማኝ መሆኑ ኢየሱስ የሰጠውን እርማት እንዲቀበል የረዳው እንዴት ነው?

ጴጥሮስ—ይቅር ባይነትን ከጌታው ተምሯል

ጴጥሮስ ይቅር ባይነትን በተመለከተ ከኢየሱስ ምን ተምሯል? ኢየሱስ ጴጥሮስን ይቅር እንዳለው ያሳየው እንዴት ነው?

ጢሞቴዎስ—‘በጌታ ልጄ የሆነው የምወደውና ታማኝ የሆነው ጢሞቴዎስ’

ጢሞቴዎስ ዓይናፋርነቱን አሸንፎ የተዋጣለት የበላይ ተመልካች እንዲሆን የረዳው ምንድን ነው?