በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አካላዊ እና አእምሯዊ ጤንነት

ጤናማ አኗኗር

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጤና ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ በሽታንና ሕክምናን በተመለከተ የሚሰጠውን ሐሳብ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ጤንነትህን ማሻሻል የምትችልባቸው መንገዶች

ጤንነትህ እንዲሻሻል የሚረዱ አምስት መንገዶችን ተመልከት።

በሽታን መከላከል የሚቻለው እንዴት ነው?

ሰውነትህ በዓይን ከማይታዩና ድምፅ ከሌላቸው ሆኖም ሞት ሊያስከትሉ ከሚችሉ ጠላቶች ጋር በየዕለቱ ይዋጋል።

አመለካከት ለውጥ ያመጣል!

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ያዘለ ምክር ደስተኛ እንድትሆን ይረዳሃል?

የተሻለ ሕይወት—ስሜታዊ ጤንነት

ስሜታችንን የመቆጣጠር ችሎታ ካዳበርን በእጅጉ እንጠቀማለን።

ደስታ የሚያስገኝ መንገድ—ጥሩ ጤንነትና ችግርን ተቋቁሞ የመኖር ችሎታ

አንድ ሰው የጤና ችግር ካለበት በሐዘን ተቆራምዶ ከመኖር ውጭ ምንም አማራጭ የለውም?

ከተሳሳተ መረጃ ራስህን ጠብቅ

አሳሳች ዜናዎች፣ የሐሰት ሪፖርቶችና የሴራ ትንታኔዎች በጣም ተስፋፍተዋል፤ በአንተም ላይ ጉዳት ሊያደርሱብህ ይችላሉ።

ለምግብ ደህንነትና ለጤናማ አመጋገብ ወሳኝ የሆኑ ሰባት ነገሮች

ሕይወት ስጦታ ነው፤ ስለዚህ የራሳችንንም ሆነ የቤተሰባችንን አባላት ጤንነት በመንከባከብ ለዚህ ስጦታ ያለንን አድናቆት ማሳየት ይኖርብናል። ይህን ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

ውፍረት መቀነስ የምችለው እንዴት ነው?

ውፍረት መቀነስ ካለብህ ለየት ያለ የአመጋገብ ሥርዓት (ዳየት) ከመከተል ይልቅ ይበልጥ ጤናማ ለመሆን የሚያስችል የአኗኗር ለውጥ አድርግ።

ወጣቶች ስለ ጤናማ አኗኗር የሰጡት ሐሳብ

ተገቢ አመጋገብ እንዲኖርህ ማድረግና ስፖርት መሥራት ይከብድሃል? አንዳንድ ወጣቶች ጤንነታቸው ለመጠበቅ ምን እንደሚያደርጉ በዚህ ክሊፕ ላይ ተናግረዋል።

የተመጣጠነ ምግብ መመገብ የምችለው እንዴት ነው?

ጤናማ አመጋገብ የሌላቸው ወጣቶች አዋቂ ከሆኑ በኋላም አመጋገባቸው ጤናማ አይሆንም፤ በመሆኑም ከአሁኑ ጤናማ የአመጋገብ ልማድ ማዳበርህ አስፈላጊ ነው።

የተሻለ ሕይወት—አካላዊ ጤንነት

መጽሐፍ ቅዱስ አካላዊ ጤንነታችንን እንድንንከባከብ ያበረታታናል።

ከመጠን ባለፈ ውፍረት የሚሠቃዩ ወጣቶች ምን መፍትሔ አላቸው?

በፍጥነት የሚዘጋጁ ለጤና ጠቃሚ ያልሆኑ ምግቦችን የማግበስበስ ልማድ የነበረው አንድ ወጣት ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ የአመጋገብ ልማዱን እንዴት እንደተቆጣጠረ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

እንዳማሩ ማርጀት ይቻላል?

በሕይወታችሁ የሚያጋጥሟችሁን ለውጦች ለመቀበል የሚረዷችሁን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ስድስት ምክሮች ተመልከቱ።

ንጹሕ አየርና የፀሐይ ብርሃን—የተፈጥሮ “አንቲባዮቲክ”

በ1800ዎቹ ዓመታት የነበሩ ሰዎች የተገነዘቧቸው አንዳንድ ነገሮች ትክክል እንደሆኑ በዘመናችን ያሉ የሳይንስ ሊቃውንት አረጋግጠዋል።

ሕመምን ተቋቁሞ መኖር

ድንገተኛ የጤና እክል ሲያጋጥም

መጽሐፍ ቅዱስ ያልተጠበቀ የጤና እክል ሲያጋጥምህ ሊረዳህ የሚችል ምን ምክር ይዟል?

ከከባድ በሽታ ጋር መኖር—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው እርዳታ አለ?

አዎ! ከባድ በሽታን ለመቋቋም የሚረዱ ሦስት እርምጃዎች እነሆ!

ከአእምሮ ጤንነት መቃወስ ጋር የሚታገሉ ሰዎችን መርዳት

የአእምሮ ጤንነት መቃወስ ያጋጠመውን ጓደኛህን መርዳትህ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ከከባድ ሕመም ጋር እየታገሉም ደስተኛ መሆን ይቻላል?

ከከባድ ሕመም ጋር የሚታገሉ አንዳንድ ሰዎች ሁኔታውን መቋቋም የቻሉት እንዴት እንደሆነ አንብብ።

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 1)

አራት ወጣቶች ያለባቸውን የጤና ችግር ለመቋቋምና አዎንታዊ አመለካከት ለመያዝ የረዳቸው ምን እንደሆነ ተናግረዋል።

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 2)

አንዳንድ ወጣቶች ከባድ የጤና ችግር ቢያጋጥማቸውም በሽታቸውን እንዲቋቋሙና አዎንታዊ አመለካከት እንዲይዙ የረዳቸው ምን እንደሆነ ራሳቸው የተናገሩትን ተመልከት።

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 3)

የሦስት ወጣቶች ተሞክሮ ያለብህን የጤና ችግር መቋቋም የምትችልበትን መንገድ ለመማር ይረዳሃል።

“ሕመሜን እያሰብኩ አልብሰለሰልም”

ኢላይዛ ጥንካሬ እንዲኖራት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ሕመሟን እንድትረሳ የረዳት ምንድን ነው?

የአካል ጉዳትን ተቋቁሞ መኖር

ከድክመቴ ጥንካሬ ማግኘት

አለተሽከርካሪ ወንበር መንቀሳቀስ የማትችል አንዲት ሴት በአምላክ በመታመኗ ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነ ኃይል’ ማግኘት ችላለች።

ዓይነ ስውርነት

ዓይነ ስውራን የማዳመጥ፣ የማሽተት፣ የመዳሰስና የመቅመስ ችሎታቸውን ይበልጥ ይጠቀማሉ?

በዓይኖቹ አምላክን የሚያገለግለው ሃይሮ

ከሁሉ የከፋው የሴሬብራል ፖልዚ በሽታ ዓይነት ቢኖርበትም ሃይሮ ደስተኛ ከመሆኑም ሌላ ሕይወቱ ትርጉም ያለው ነው።

አምላክን ማገልገሉ መድኃኒት ሆነለት!

ኦኔስመስ በዘር የሚተላለፍ ኦስቲዎጄነሲስ ኢምፐርፌክታ የተሰኘ የአጥንት በሽታ አለበት። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት አምላክ ቃል የገባቸው ተስፋዎች ያበረታቱት እንዴት ነው?

በዳሰሳ መኖር

ጄምስ ራያን ሲወለድ ጀምሮ መስማት የተሳነው ነው፤ በኋላ ላይ ደግሞ ዓይነ ስውር ሆነ። ሕይወቱ ትርጉም እንዲኖረው የረዳው ምንድን ነው?

ይሖዋ ከሚገባው በላይ አድርጎልኛል

ፌሊክስ አላርኮን በሞተር ብስክሌት በደረሰበት አደጋ ሳቢያ ከአንገቱ በታች ሽባ ቢሆንም ሕይወቱ ትርጉም ያለው ሆኗል።

በጣም በሚያስፈልገኝ ወቅት ያገኘሁት ተስፋ

ሚክሎሽ ሌክስ በ20 ዓመቱ በደረሰበት አሳዛኝ አደጋ ምክንያት መንቀሳቀስ የማይችል ሰው ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ እንዲኖረው የረዳው እንዴት ነው?

ሌሎችን መንከባከብ

መጽሐፍ ቅዱስ አረጋውያን ወላጆችን መጦርን በተመለከተ ምን ይናገራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ወላጆቻቸውን ስለጦሩ የእምነት ሰዎች ይናገራል። በተጨማሪም አረጋውያንን ለሚንከባከቡ ሰዎች የሚጠቅሙ ግሩም ምክሮች ይሰጣል።

ልጃችሁ የጤና እክል ቢኖርበት

ሊያጋጥሟችሁ የሚችሉ 3 ተፈታታኝ ሁኔታዎችንና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ የሚንጸባረቅበት ምክር እንዴት እንደሚረዳችሁ እንመልከት።

አባቴ ወይም እናቴ ታማሚ ቢሆኑስ?

እንዲህ ዓይነት ችግር ያጋጠመህ አንተ ብቻ አይደለህም። ሁለት ወጣቶች ይህን ሁኔታ ለመቋቋም የረዳቸው ምን እንደሆነ አንብብ።

የቤተሰባችን አባል የማይድን በሽታ ሲይዘው

የቤተሰብ አባላት የማይድን በሽታ የያዘውን ሰው ለማጽናናትና ለመንከባከብ ምን ማድረግ ይችላሉ? በሽተኛውን በሚያስታምሙበት ወቅት የሚሰሟቸውን የተለያዩ ስሜቶች መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?

በሽታዎች እና የአቅም ገደቦች

የቫይረስ ወረርሽኝ—ምን ማድረግ ትችላለህ?

ወረርሽኝ በሚከሰትበት ጊዜ አካላዊ፣ ስሜታዊና መንፈሳዊ ጤንነትህን መንከባከብ የምትችለው እንዴት ነው?

የአእምሮ ሕመም—ምን ማወቅ ይኖርብሃል?

የአእምሮ ሕመምን ተቋቁሞ ለመኖር የሚረዱ ዘጠኝ እርምጃዎች።

ደም ማነስ—መንስኤው፣ ምልክቶቹና ሕክምናው

ደም ማነስ ምንድን ነው? ደም ማነስን መከላከል ወይም ማዳን ይቻላል?

የስኳር በሽታ—በበሽታው የመያዝ አጋጣሚህን መቀነስ ትችላለህ?

ቅድመ የስኳር በሽታ ካለባቸው ሰዎች መካከል 90 በመቶ ገደማ የሚሆኑት ሕመሙ እንዳለባቸው አያውቁም።

የሚጥል በሽታ—ልታውቀው የሚገባው ነገር

ብዙ ሰዎች ስለዚህ የጤና እክል የተሳሳተ አመለካከት አላቸው፤ እስቲ ይህን የጤና እክል አስመልክቶ አንዳንድ መሠረታዊ ነገሮችን እንመልከት።

የድድ በሽታ—አንተን ያሰጋህ ይሆን?

የድድ በሽታ በዓለም ላይ ካሉ በጣም የተለመዱ የአፍ በሽታዎች አንዱ ነው። መንስኤው ምንድን ነው? በሽታው እንዳለብህ ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው? በዚህ በሽታ የመያዝ አጋጣሚህን መቀነስ የምትችለው እንዴት ነው?

የምግብ አለርጂ እና የምግብ አለመስማማት—ልዩነታቸው ምንድን ነው?

ይህ ችግር አለብኝ ብለህ በራስህ መደምደም ምን ጉዳት አለው?

ስለ ወባ በሽታ ማወቅ ያለብህ ነገር

የምትኖረው ለወባ በሽታ በተጋለጠ አካባቢ ቢሆን ወይም ወደዚያ አካባቢ ለመሄድ የምታስብ ሰው ብትሆን እንኳ ራስህን ከበሽታው መጠበቅ ትችላለህ።

ማረጥ የሚያስከትላቸውን አስቸጋሪ ሁኔታዎች መቋቋም

አንቺም ሆንሽ በዙሪያሽ ያሉ ሰዎች ስለ ማረጥ ይበልጥ ባወቃችሁ መጠን ከዚህ ሁኔታ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን ለመቋቋም ይበልጥ ዝግጁ ትሆናላችሁ።

የመንፈስ ጭንቀት

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መንፈስ ጭንቀት ምን ይላል?

ሰዎች በመንፈስ ጭንቀት የሚጠቁት ለምን እንደሆነ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ አሉታዊ ስሜቶችን ለማስወገድ እንዴት እንደሚረዳህ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

መኖር ምን ዋጋ አለው?

አንድ ሰው ሞትን እንዲመኝ የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል?

ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ

ምንም ዓይነት ከባድ ሁኔታ ቢያጋጥምህ በሕይወት መኖርህ ዋጋ አለው።

የመንፈስ ጭንቀትና ወጣቶች—መንስኤውና መፍትሔው

ምልክቱና መንስኤው ምንድን ነው? ወላጆችና ሌሎች ሰዎች የመንፈስ ጭንቀት ያለባቸውን ወጣቶች መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?

አሉታዊ አመለካከትን ማስወገድ የምችለው እንዴት ነው?

እነዚህ ሐሳቦች አዎንታዊ አመለካከት ለማዳበር ይረዱሃል።

የወጣቶች የአእምሮ ጤንነት ማሽቆልቆል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ የአእምሮ ጤንነት ቀውስ ለሚያጋጥማቸው ወጣቶች የሚሆን ጠቃሚ ምክር ይዟል።

ሰውነቴን የምቆርጠው ለምንድን ነው?

ብዙ ወጣቶች፣ በሰውነታቸው ላይ ጉዳት የማድረስ ችግር አለባቸው። አንቺም እንዲህ ዓይነት ችግር ካለብሽ፣ እርዳታ ማግኘት የምትችዪው እንዴት ነው?

የመንፈስ ጭንቀትን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

እነዚህ ጠቃሚ ሐሳቦች ስሜትህን ለማስተካከል የሚያስችሉ እርምጃዎችን እንድትወስድ ይረዱሃል።

ጭንቀት ውስጥ ስገባ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?

አምላክ ጭንቀት ውስጥ የገቡ ሰዎችን ለመርዳት የሚጠቀምባቸው ሦስት መንገዶች አሉ።

ራሴን የማጥፋት ሐሳብ ሲመጣብኝ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳኝ ይችላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን የማጥፋት ሐሳብ ለሚመጣበት ሰው ምን ጠቃሚ ምክር ይዟል?

ጭንቀት እና ውጥረት

የሚያስጨንቁ ነገሮችን መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው?

አላስፈላጊ ጭንቀትን ለማስወገድ የሚረዱህ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እና ጠቃሚ ምክሮች ናቸው?

በወንዶች ላይ የሚከሰት ጭንቀት—መጽሐፍ ቅዱስ ምን የመፍትሔ ሐሳብ ይሰጣል?

በዚህ አስጨናቂ ዘመን፣ ጭንቀት ብዙዎችን የሚያጠቃ ችግር ሆኗል። አንተም ጭንቀትህን ለመርሳት እየታገልክ ከሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ ይችላል?

ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

ለብቻህ ለመሆን ስትገደድ ተስፋ፣ ደስታና እርካታ ማግኘት ከባድ እንደሆነ ሊሰማህ ይችላል፤ ሆኖም ማግኘት ይቻላል።

ወረርሽኙ የሚፈጥረውን ሥነ ልቦናዊ ጫና መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ስሜቱን ካልተዋጋነው የኮቪድ-19 የደህንነት መመሪያዎችን ለመከተል ያለን ተነሳሽነት ቀስ በቀስ ሊጠፋ ይችላል።

ውጥረትን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

ውጥረትን በተሻለ መንገድ ለመቋቋም አልፎ ተርፎም ለመቀነስ የሚረዱ አንዳንድ ጠቃሚ ምክሮችን ተመልከት።

ጭንቀትን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

የሚሰማህ ጭንቀት እንዲጎዳህ ሳይሆን እንዲጠቅምህ የሚያደርጉ ስድስት ነጥቦች።

መጽሐፍ ቅዱስ ጭንቀትን እንድትቋቋም ሊረዳህ ይችላል?

ጭንቀት የሕይወታችን ክፍል እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ ሰዎች አሉ።ከጭንቀት የምንገላገልበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጭንቀት ምን ይላል?

ጭንቀት አንዳንድ ጊዜ ጠቃሚ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ ጎጂ ነው። ጎጂ ጭንቀትን መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው?

ውጥረትን መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ

ብዙውን ጊዜ ውጥረት የሚያመጡ አራት ነገሮችን ለመቋቋም የሚረዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮችን አንብብ።

ተፈታታኙ ነገር፦ ተደራራቢ ኃላፊነት

ሁሉን ነገር ራሳችን ለማድረግ የምንሞክር ከሆነ አተርፍ ባይ አጉዳይ ልንሆን እንችላለን። የሚሰማህን ውጥረት መቀነስ የምትችለው እንዴት ነው?

ኃይሌ እንዳይሟጠጥና እንዳልዝል ምን ሊረዳኝ ይችላል?

አንድን ሰው ኃይሉ እንዲሟጠጥና እንዲዝል የሚያደርገው ምን ሊሆን ይችላል? ይህ ሁኔታ አንተንስ ያሰጋሃል? ከሆነ ምን ልታደርግ ትችላለህ?

ወጣት ልጃችሁ ውጥረትን እንድትቋቋም መርዳት

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ልጃገረዶች የሚያጋጥሟቸው ለውጦች ውጥረት ይፈጥሩባቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው ውጥረትን እንዲቋቋሙ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ውጥረትን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ውጥረት ሊያስከትሉ የሚችሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ምን እንደሆኑ እንዲሁም ውጥረትን እንዴት መቋቋም እንደምትችል ለማወቅ ይህን ርዕስ አንብብ።

ከራሴ ፍጽምና እጠብቃለሁ?

ጥሩ ደረጃ ላይ ለመድረስ በሚደረግ ጥረትና ሊደረስበት የማይችል ግብ ላይ ለመድረስ በመጣጣር መካከል ሰፊ ልዩነት አለ።

ለውጥን ማስተናገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ለውጥ የማይቀር ነገር ነው። አንዳንዶች ያጋጠማቸውን ለውጥ ለማስተናገድ ምን እንዳደረጉ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

አሉታዊ ስሜቶችን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

አሉታዊ ስሜቶችን ለመቋቋም የሚረዱ ሦስት ነገሮች።

የሕክምና እርዳታ

ክርስቲያኖች የሕክምና እርዳታ ይቀበላሉ?

አምላክ የሕክምና ምርጫችን ያሳስበዋል?

የምንወደው ሰው ሲታመም

የሕክምና ቀጠሮዎችና ሆስፒታል ውስጥ የምናሳልፈው ጊዜ ውጥረት ሊፈጥሩብን ይችላሉ። ጓደኛህ ወይም ዘመድህ ያጋጠመውን ፈታኝ ሁኔታ በተሳካ መንገድ እንዲወጣ መርዳት የምትችለው እንዴት ነው?

ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎች

ከ40 ከሚበልጡ አገሮች የተውጣጡ እውቅ ባለሙያዎች ያለ ደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎችን አስመልክቶ ስላገኙት መረጃ የሰጡትን አስተያየት እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ደም መውሰድ—በዘመናችን ያሉ የሕክምና ባለሙያዎች ምን ይላሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች ደም ለመውሰድ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ነቀፋ ይሰነዘርባቸዋል፤ አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች ደምን በተመለከተ ስላለን አቋም ምን ይሰማቸዋል?

የይሖዋ ምሥክር የሆኑ ታካሚዎች ደም አለመውሰዳቸው ቶሎ እንዲያገግሙ ረድቷቸዋል

ሪፖርቶች እንደሚያሳዩት ደም የማይወስዱ ታካሚዎች በሕይወት የመትረፍ አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው፤ ሆስፒታል ውስጥ የሚቆዩበት ጊዜም አጭር ነው።