በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ

ሕይወት ከባድ ሲሆንብህ

ሁሉ ነገር አልጋ በአልጋ በሆነበት ወቅት ሕይወት አስደሳች ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ሕይወት ከባድ እንዲሆንብህ የሚያደርጉ አንዳንድ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህስ?

ለምሳሌ ያህል፣ በከባድ አውሎ ነፋስ ምክንያት አብዛኛውን ንብረቷን ያጣች በዩናይትድ ስቴትስ የምትኖር ሳሊ * የተባለች ሴት እንዲህ ብላለች፦ “የሚሰማኝ ጭንቀት ልሸከመው ከምችለው በላይ እንደሆነ ተሰምቶኝ ነበር። ‘አሁንስ በቅቶኛል’ ያልኩባቸው ብዙ ጊዜያት ነበሩ።”

በሕይወታችን ውስጥ ሊያጋጥመን የሚችለው ሌላው ተፈታታኝ ሁኔታ ደግሞ የምንወደውን ሰው በሞት ማጣት ነው። በአውስትራሊያ የምትኖረው ጃኒስ እንዲህ ብላለች፦ “ሁለቱንም ወንዶች ልጆቼን ሞት ሲነጥቀኝ ሁሉ ነገር ጨለመብኝ፤ ወደ ቀድሞ ሕይወቴ ለመመለስ ብዙ ጥረት ጠይቆብኛል። ‘ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም! እባክህ ሞቼ ልገላገል። ዳግመኛ መንቃት አልፈልግም’ በማለት አምላክን ተማጽኜው ነበር።”

በሌላ በኩል ደግሞ ዳንኤል፣ ባለቤቱ በትዳራቸው ላይ ክህደት እንደፈጸመች ሲያውቅ ስሜቱ ክፉኛ ተጎድቶ ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “ባለቤቴ ምንዝር እንደፈጸመች ስትነግረኝ ልቤ ላይ ጩቤ የተሰካብኝ ያህል ሕመም ተሰምቶኝ ነበር። ይህ አካላዊ ሕመም በተደጋጋሚ እየመጣ ለብዙ ወራት አሠቃይቶኛል።”

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በሚከተሉት አስቸጋሪ ሁኔታዎች ሥር እንኳ፣ ‘በሕይወት መኖር ዋጋ አለው’ የምንልበትን ምክንያት ያብራራል፦

በመጀመሪያ፣ የተፈጥሮ አደጋ በሚያጋጥምበት ጊዜ ሁኔታውን መቋቋም የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመልከት።

^ በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ውስጥ የተጠቀሱት አንዳንዶቹ ስሞች ተቀይረዋል።