በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

E+/taseffski/via Getty Images (Stock photo. Posed by model.)

ነቅታችሁ ጠብቁ!

የወጣቶች የአእምሮ ጤንነት ማሽቆልቆል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የወጣቶች የአእምሮ ጤንነት ማሽቆልቆል—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) የካቲት 13, 2023 በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ወጣቶችን የአእምሮ ጤንነት የተመለከተ ሪፖርት አውጥቶ ነበር። ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ከ40 በመቶ የሚበልጡ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የማያባራ የሐዘንና የተስፋ ቢስነት ስሜት ይሰማቸዋል።

 “ባለፉት 10 ዓመታት የወጣቶች የአእምሮ ጤንነት እያሽቆለቆለ እንደመጣ አይካድም፤ ሆኖም በአሁኑ ጊዜ በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ ሴቶች ልጆች ላይ የሚታየው የአእምሮ ጤንነት ቀውስ ብሎም ራስን የማጥፋት ሐሳብና ሙከራ ከመቼውም ጊዜ የባሰ ነው።”—የሲዲሲ የወጣቶችና የትምህርት ቤት ጤንነት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ካትሊን ኢቲየር

 ሪፖርቱ እንደገለጸው

  •   ከ10 ወጣት ሴቶች አንዷ (14 በመቶ) ያለፍላጎቷ የፆታ ግንኙነት እንድትፈጽም ተገድዳለች። ዶክተር ኢቲየር እንዲህ ብለዋል፦ “ይህ በጣም አስደንጋጭ ነው። ከምታውቋቸው አሥር ወጣት ሴቶች መካከል ቢያንስ አንዷ፣ ምናልባትም ከዚያ የሚበልጡት ተገድደው ተደፍረዋል።”

  •   በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኙ 3 ሴቶች አንዷ (30 በመቶ) የራሷን ሕይወት ለማጥፋት አስባ ታውቃለች።

  •   በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኙ 5 ሴቶች 3ቱ (57 በመቶ) በማያባራ የሐዘን ወይም የተስፋ ቢስነት ስሜት ይዋጣሉ።

 እነዚህን አኃዞች መመልከት ልብ የሚሰብር ነው። ወጣትነት የደስታና የሐሴት ጊዜ ሊሆን ይገባ ነበር። ታዲያ ወጣቶች በዛሬው ጊዜ የሚያጋጥማቸውን ውጥረት ለመቋቋም ምን ሊረዳቸው ይችላል? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ለወጣቶች ጠቃሚ ምክር ይሰጣል

 መጽሐፍ ቅዱስ የምንኖርበት ዘመን አስጨናቂ እንደሆነ በግልጽ ይናገራል። ዘመናችንን “ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን” በማለት ይጠራዋል። (2 ጢሞቴዎስ 3:1-5) ያም ቢሆን መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎች መወጣት እንዲችሉ እየረዳቸው ነው። የሚከተሉትን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ርዕሶች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

 ራሳቸውን ለማጥፋት የሚያስቡ ወጣቶችን የሚረዳ ምክር

 ከድባቴ፣ ከሐዘን ወይም ከአሉታዊ ስሜት ጋር የሚታገሉ ወጣቶችን የሚረዳ ምክር

 ጉልበተኞች ወይም በኢንተርኔት ጥቃት የሚሰነዝሩ ሰዎች የሚያስቸግሯቸውን ወጣቶች የሚጠቅም ምክር

 ፆታዊ ትንኮሳና ጥቃት የሚያጋጥማቸውን ወጣቶች የሚጠቅም ምክር

መጽሐፍ ቅዱስ ለወላጆችም ጠቃሚ ምክር ይሰጣል

 መጽሐፍ ቅዱስ ለወላጆችም ጠቃሚ ምክር ይዟል፤ ወላጆች ይህን ምክር በመከተል በአሥራዎቹ ዕድሜ ያሉ ልጆቻቸው የሚያጋጥሟቸውን ተፈታታኝ ሁኔታዎችን እንዲቋቋሙ መርዳት ይችላሉ። የሚከተሉትን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ርዕሶች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።