በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ለቤተሰብ

በዚህ ዓምድ ሥር የሚወጡት ርዕሶች፣ መጽሐፍ ቅዱስ ለቤተሰቦች የሚሰጠውን ጠቃሚ ምክር ይዘዋል። a ለቤተሰቦች የወጡ ርዕሶችን የተሟላ ዝርዝር ማየት ከፈለግክ “ትዳር እና ቤተሰብ” በሚለው ክፍል ሥር ተመልከት።

a በእነዚህ ርዕሶች ላይ የተጠቀሱ አንዳንድ ሰዎች ስማቸው ተቀይሯል።

ትዳር

የትዳር ጓደኛችሁ ያለውን የሚያበሳጭ ጠባይ በአዎንታዊ መንገድ ማየት

የትዳር ጓደኛችሁ ያለው የሚያበሳጭ ጠባይ በመካከላችሁ ግጭት እንዲፈጥር ከመፍቀድ ይልቅ ያንን ጠባይ በአዎንታዊ መንገድ ለማየት ጥረት አድርጉ።

ትዕግሥት ማዳበር የሚቻለው እንዴት ነው?

ትዳር ፍጹም ያልሆኑ ሁለት ሰዎች ጥምረት ስለሆነ የተለያዩ ችግሮች መነሳታቸው አይቀርም። ለስኬታማ ትዳር ትዕግሥት ወሳኝ ነገር ነው።

ለሰመረ ትዳር፦ አክብሮት ማሳየት

በትዳራችሁ ውስጥ መከባበር ጠፍቷል? መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ረገድ ሊረዳችሁ ይችላል።

አክብሮት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?

አክብሮት አንዳንድ ጊዜ ብቻ ልናሳየው የሚገባ ነገር አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ ለትዳር ወሳኝ የሆነ ባሕርይ ነው። ለትዳር ጓደኛችሁ አክብሮት ማሳየት የምትችሉት እንዴት ነው?

አድናቆት ማሳየት የሚቻለው እንዴት ነው?

ባለትዳሮች አንዳቸው የሌላውን ጥሩ ባሕርይ ለማስተዋልና ለማድነቅ ጥረት የሚያደርጉ ከሆነ ትዳራቸው ጠንካራ ይሆናል። ታዲያ አድናቆት ለማዳበር ምን ሊረዳህ ይችላል?

ለሰመረ ትዳር፦ ፍቅር መግለጽ

ሥራ፣ ውጥረት እንዲሁም የሕይወት ሩጫ ባለትዳሮች በስሜት እንዲራራቁ ሊያደርግ ይችላል። ታዲያ ባለትዳሮች ቀድሞ የነበራቸውን ሞቅ ያለ ፍቅር እንደገና ማቀጣጠል የሚችሉት እንዴት ነው?

ፍቅርን መግለጽ የሚቻለው እንዴት ነው?

የትዳር ጓደኛሞች አንዳቸው ለሌላው ፍቅራቸውን መግለጽ የሚችሉት እንዴት ነው? በመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች ላይ የተመሠረቱ አራት ጠቃሚ ሐሳቦችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የጋብቻን ቃለ መሐላ ጠብቆ መኖር የሚቻለው እንዴት ነው?

ቃለ መሐላን የምትመለከተው ካደረግከው መጥፎ ውሳኔ ጋር ጠፍሮ እንደሚያስር እግር ብረት አድርገህ ነው ወይስ ትዳራችሁ እንዳይናጋ እንደሚያደርግ መልሕቅ?

ሥራን ሥራ ቦታ መተው

ሥራችሁ በትዳራችሁ ውስጥ ጣልቃ እንዳይገባ ለማድረግ የሚረዷችሁ አምስት ጠቃሚ ምክሮች።

ወጪን መቆጣጠር

ወጪያችሁን መቆጣጠር መጀመር ያለባችሁ ገንዘብ ሲያልቅባችሁ አይደለም። ታዲያ ይህን ማድረግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ከአማቶች ጋር ተስማምቶ መኖር

ከአማቶቻችሁ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሟችሁ ችግሮች በትዳራችሁ ውስጥ ችግር እንዳይፈጥሩ የሚረዷችሁ ሦስት ጠቃሚ ምክሮችን ተመልከቱ።

የአመለካከት ልዩነትን ማስታረቅ

ባለትዳሮች ችግሮችን ፈተው በሰላም መኖር የሚችሉት እንዴት ነው?

የአመለካከት ልዩነቶችን ማስታረቅ

ከትዳር ጓደኛህ ጋር ፈጽሞ እንደማትጣጣም ተሰምቶህ ያውቃል?

ቂምን መተው የሚቻልበት መንገድ

የትዳር ጓደኛችሁ የፈጸመውን ስህተት ይቅር ለማለት ጥፋቱን አቅልላችሁ መመልከት ወይም ምንም እንዳልተፈጠረ መሆን ይጠበቅባችኋል?

ቁጣን መቆጣጠር የሚቻለው እንዴት ነው?

በቁጣ መገንፈል ጤናን ሊጎዳ ይችላል፤ ቁጣን አምቆ መያዝም ቢሆን ጉዳት ያስከትላል። ታዲያ የትዳር ጓደኛችሁ ሲያናድዳችሁ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ልጆች ራሳቸውን ችለው መኖር ሲጀምሩ

አንዳንድ ባለትዳሮች ልጆቻቸው አድገው ከቤት ሲወጡ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ያጋጥሟቸዋል። ወላጆች በዚህ ወቅት የሚሰማቸውን ስሜት ማሸነፍ የሚችሉት እንዴት ነው?

ጓደኝነት ገደቡን ሲያልፍ

‘ከጓደኝነት ያለፈ ምንም ነገር የለንም’ ብላችሁ ታስባላችሁ? ይህ ዓይነቱ አመለካከት ትክክል መሆን አለመሆኑን ለማወቅ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን መርምሩ።

በትዳር ደስታ ማጣት

የሞቀ ትዳር ውስጥ ሳይሆን እስር ቤት ውስጥ እንዳላችሁ ይሰማችኋል? ትዳራችሁ ደስታ የሰፈነበት እንዲሆን የሚረዷችሁ አምስት እርምጃዎች እነሆ!

ፍቺ በስተርጅና—መከላከያው ምንድን ነው?

ሰዎች በስተርጅና የሚፋቱት ለምንድን ነው? የእናንተ ትዳር ተመሳሳይ ዕጣ እንዳይገጥመውስ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ቅናት ትዳራችሁን እንዳይበጠብጠው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ጥርጣሬና አለመተማመን የሰፈነበት ትዳር አይሰምርም። ታዲያ አግባብነት የሌለው ቅናት ትዳራችሁን እንዳይበጠብጠው ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ፖርኖግራፊ ትዳራችሁን ሊያናጋው ይችላል

እነዚህ ምክሮች የፖርኖግራፊ ሱስህን ለማሸነፍና ትዳርህና መልሰህ ለማጠናከር ይረዱሃል።

ከመጋባታችን በፊት አብረን ብንኖርስ?

አንዳንድ ጥንዶች አብረው መኖራቸው ለጋብቻ እንደሚያዘጋጃቸው ይሰማቸዋል። ይህ የጥበብ እርምጃ ነው? ወይስ የተሻለ አማራጭ አለ?

የሐሳብ ልውውጥ

አብራችሁ ጊዜ አሳልፉ

ባለትዳሮች፣ በአካል አብረው ሆነውም እንኳ እርስ በርስ ብዙም እንደማይነጋገሩ ይስተዋላል። ታዲያ አብረው የሚያሳልፉትን ጊዜ በተሻለ መንገድ መጠቀም የሚችሉት እንዴት ነው?

ቴክኖሎጂ ሕይወታችንን እንዳይቆጣጠረው ማድረግ

የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የምትጠቀሙበት መንገድ በትዳራችሁ ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ውጤት ሊኖረው ይችላል። ቴክኖሎጂ በትዳራችሁ ላይ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እያደረገ ነው?

በችግሮች ላይ መወያየት የሚቻልበት መንገድ

ወንዶችና ሴቶች ሐሳባቸውን የሚገልጹበት መንገድ የተለያየ ነው። ይህን ልዩነት መረዳታችሁ ከጭቅጭቅ ያድናችኋል።

ጥሩ አድማጭ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

ከልብ ማዳመጥ እንዲሁ የጥሩ ሥነ ምግባር መለኪያ ብቻ ሳይሆን የፍቅር መግለጫም ነው። ጥሩ አድማጭ መሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

መደራደር የሚቻለው እንዴት ነው?

የሚከተሉት አራት ምክሮች ከትዳር ጓደኛችሁ ጋር ከመጨቃጨቅ ይልቅ አብራችሁ ለችግሩ መፍትሔ እንድትፈልጉ ይረዷችኋል።

ኩርፊያን ማስወገድ የሚቻልበት መንገድ

አንዳንድ ባለትዳሮች የሚኮራረፉት ለምንድን ነው? በመካከላቸው የሚፈጠረውን አለመግባባት መፍታት የሚችሉትስ እንዴት ነው?

መጨቃጨቅ ማቆም የምትችሉት እንዴት ነው?

ከትዳር ጓደኛህ ጋር ነጋ ጠባ ትጨቃጨቃላችሁ? የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ትዳራችሁን ለማሻሻል የሚረዷችሁ እንዴት እንደሆነ እንድታነብብ እንጋብዝሃለን።

ጎጂ ንግግርን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

አንተም ሆንክ የትዳር ጓደኛህ የምትሰነዝሯቸው ጎጂ ቃላት በግንኙነታችሁ ላይ መጥፎ ተጽዕኖ እያሳደሩ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ይቅር ማለት የምትችሉት እንዴት ነው?

ይቅር ማለት ከባድ ሊሆን የሚችለው ለምንድን ነው? በዚህ ረገድ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው ምክር ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?

ልጆችን ማሳደግ

ጥሩ አባት መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?

አሁን የባልነት ድርሻህን የምትወጣበት መንገድ ልጁ ከተወለደ በኋላ የአባትነት ድርሻህን ስለምትወጣበት መንገድ ፍንጭ ይሰጣል።

ወላጆች ስለ ሕፃናት ማቆያ ማዕከላት ምን ማወቅ ይኖርባቸዋል?

ልጃችሁን ወደ ሕፃናት ማቆያ መላካችሁ የተሻለ አማራጭ መሆን አለመሆኑን ለመወሰን በዚህ ርዕስ ውስጥ የሚገኙትን አራት ጥያቄዎች ጠይቁ።

ልጄ ዘመናዊ ስልክ ሊኖረው ይገባል?

እናንተም ሆናችሁ ልጃችሁ ኃላፊነቱን ለመቀበል ዝግጁ መሆናችሁን ለማወቅ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቁ።

ልጆች ዘመናዊ ስልክን በጥበብ እንዲጠቀሙ ማስተማር

ስለ ቴክኖሎጂ ብዙ የሚያውቁ ልጆችም እንኳ ዘመናዊ ስልካቸውን በጥበብ ለመጠቀም የወላጆቻቸው ሥልጠና ያስፈልጋቸዋል።

ልጃችሁን ከፖርኖግራፊ ጠብቁ

ልጆች ከምታስቡት በላይ በቀላሉ ለፖርኖግራፊ ሊጋለጡ ይችላሉ። ልጆቻችሁን ለመጠበቅ ምን ነገሮችን ማወቅ ይኖርባችኋል? ምን ማድረግስ ትችላላችሁ?

ንባብ ለልጆች አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?—ክፍል 1፦ ማንበብ ወይስ ማየት?

ብዙ ልጆች ቪዲዮ ማየት ይወዳሉ። ወላጆች ልጆቻቸው የንባብ ልማድ እንዲያዳብሩ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ንባብ ለልጆች አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?—ክፍል 2፦ ስክሪን ወይስ ወረቀት?

ልጆች ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ላይ ቢያነቡ ይሻላል ወይስ ወረቀት ላይ? ሁለቱም የራሳቸው ጥቅሞች አሏቸው።

ልጆች በሚሰሟቸው የዜና ዘገባዎች እንዳይረበሹ መርዳት

ወላጆች፣ ልጆቻቸው በሚረብሹ የዜና ዘገባዎች የተነሳ ለጭንቀት እንዳይዳረጉ መርዳት የሚችሉት እንዴት ነው?

ልጅህ ስለ ሞት ሲጠይቅህ

ልጆች ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚያነሱትን ጥያቄ እንዴት መመለስ እንደምትችል እንዲሁም የቅርብ ሰው ሲሞትባችሁ ልጆች ሐዘኑን እንዲቋቋሙ መርዳት የምትችለው እንዴት እንደሆነ የሚገልጹ አራት ነጥቦችን አንብብ።

ልጄ ቤት ውስጥ ቁጭ ማለት ቢሰለቸውስ?

ልጃችሁ ቤት ውስጥ መቀመጥ ስልችት ብሎታል? ይህ ርዕስ፣ ልታስቡባቸው የምትችሏቸውን አንዳንድ ነጥቦች ይዟል።

የፈጠራ ችሎታን የሚያበረታቱ ጨዋታዎች ያላቸው ጥቅም

እነዚህ ጨዋታዎች፣ ቁጭ ተብለው ከሚታዩ መዝናኛዎች እንዲሁም ለልጆች ተብለው ከሚደረጉ ዝግጅቶች ይልቅ በርካታ ጥቅሞች አሏቸው።

ልጆች የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዲሠሩ ማድረግ ያለው ጥቅም

ወላጆች ልጆቻችሁ ቤት ውስጥ እንዲሠሩ ከማድረግ ወደኋላ ትላላችሁ? ከሆነ ልጆቻችሁ የቤት ውስጥ ሥራዎችን እንዲሠሩ ማድረግ ልጆች ኃላፊነት የሚሰማቸውና ደስተኛ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ምን ጥቅም እንዳለው ተመልከቱ።

ልጆች ሽንፈትን በጥሩ ሁኔታ እንዲወጡ መርዳት

ስህተት የማይሠራ ማንም ሰው የለም። ልጆቻችሁ አንድ ነገር ሳይሳካላቸው ሲቀር ለጉዳዩ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖራቸውና መፍትሔ የመፈለግ ችሎታ እንዲያዳብሩ እርዷቸው።

ልጃችሁ የትምህርት ውጤቱን እንዲያሻሽል መርዳት የምትችሉት እንዴት ነው?

ልጃችሁ ዝቅተኛ ውጤት ያመጣበትን ምክንያት ለይታችሁ ማወቅ እንዲሁም ትምህርቱ ላይ እንዲያተኩር ማድረግ የምትችሉት እንዴት እንደሆነ አንብቡ።

ልጄን ጉልበተኞች ቢያስቸግሩት ምን ላድርግ?

ልጃችሁ ጉልበተኞችን እንዲያሸንፍ ለመርዳት የሚያስችሏችሁ አራት እርምጃዎች!

ልጆችን ማድነቅ የሚቻልበት መንገድ

ልጆችን ማድነቅ የሚቻልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ የትኛው ነው?

ፍቺ በልጆች ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ

አንዳንድ ሰዎች፣ ወላጆች መፋታታቸው ለልጆች የተሻለ እንደሆነ ቢያስቡም ጥናቶች እንደሚያሳዩት ፍቺ በልጆች ላይ ከባድ ጉዳት ያደርሳል።

ልጃችሁ የጉርምስናን ዕድሜ እንዲወጣ መርዳት

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ አምስት ምክሮች ብዙውን ጊዜ ተፈታታኝ የሆነውን ይህን ዕድሜ በተሻለ መንገድ ለመወጣት ይረዳሉ።

ልጃችሁን ስለ ፆታ ማስተማር

ልጆች ከትንሽነታቸው ጀምሮ ከፆታ ግንኙነት ጋር ለተያያዙ መልእክቶች ተጋላጭ እየሆኑ ነው። ወላጆች ሊያውቁት የሚገባው ነገር ምንድን ነው? ልጆቻችሁን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ልጃችሁን ስለ አልኮል መጠጥ ማስተማር

ወላጆች ልጆቻቸውን ስለዚህ አስፈላጊ ጉዳይ ሊያስተምሩ የሚገባው መቼና እንዴት ነው?

ልጆችን ስለ ዘረኝነት ማስተማር

ዕድሜውን ባገናዘበ መልኩ ልጃችሁን ማስተማራችሁ ከዘር መድልዎ ጋር በተያያዘ ሌሎች ተጽዕኖ እንዳያሳድሩበት ሊረዳው ይችላል።

ራስን መግዛትን ለልጆች ማስተማር

ለልጆቻችሁ የጠየቁትን ሁሉ የምትሰጧቸው ከሆነ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ትነፍጓቸዋላችሁ።

ልጆችን ትሕትና ማስተማር

ልጃችሁ ለራሱ ያለው ግምት ሳይቀንስ ትሕትናን እንዲማር እርዱት።

ልጆቻችሁን አመስጋኝ እንዲሆኑ አስተምሯቸው

ሕፃናትንም እንኳ ሰው አንድ ጥሩ ነገር ሲያደርግላቸው ‘አመሰግናለሁ’ እንዲሉ ማስተማር ይቻላል።

ልጆች ታዛዥ እንዲሆኑ ማሠልጠን

እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል ከልጆቻችሁ ጋር ትጨቃጨቃላችሁ? እንዲህ የመሰለውን ጭቅጭቅ ለማስቀረት ወላጆችን የሚረዱ አምስት ነጥቦች።

“አይሆንም” ማለት የምትችሉት እንዴት ነው?

ልጃችሁ በማልቀስ ወይም በመለማመጥ ውሳኔያችሁን እንድትቀይሩ ቢፈታተናችሁ ምን ታደርጋላችሁ?

ልጆች እልኸኛ ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?

ልጃችሁ እልኸኛ ቢሆን ምን ማድረግ ትችላላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ተፈታታኝ ሁኔታ ለመወጣት ይረዳችኋል።

ልጃችሁ ሲዋሽ

ልጃችሁ ሲዋሽ ምን ማድረግ አለባችሁ? በዚህ ርዕስ ላይ የቀረቡት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ምክሮች፣ ሐቀኛ መሆን ያለውን አስፈላጊነት ለልጃችሁ ለማስተማር ይረዷችኋል።

በአሥራዎቹ ዕድሜ ያሉ ልጆችን ማሳደግ

በአሥራዎቹ ዕድሜ ከሚገኝ ልጃችሁ ጋር የሐሳብ ልውውጥ ማድረግ

ከልጃችሁ ጋር በምታደርጉት ጭውውት ተስፋ ቆርጣችኋል? ይህን ሁኔታ ተፈታታኝ የሚያደርገው ምንድን ነው?

ወጣት ልጃችሁ ውጥረትን እንድትቋቋም መርዳት

በአሥራዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ልጃገረዶች የሚያጋጥሟቸው ለውጦች ውጥረት ይፈጥሩባቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው ውጥረትን እንዲቋቋሙ ሊረዷቸው የሚችሉት እንዴት ነው?

ልጃችሁ ሕይወቷን የማጥፋት ሐሳብ ቢኖራት

አንድ ልጅ ሕይወቱን የማጥፋት ሐሳብ ቢኖረው ወላጆች ምን ማድረግ ይችላሉ?

ወጣት ልጃችሁ እምነት ሲያጓድል

ልጃችሁ ዓመፀኛ እንደሆነ ለማሰብ አትቸኩሉ። ልጃችሁ ያጣውን እምነት መልሶ ማግኘት ይችላል።

ለልጆቻችሁ አመራር መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው?

ልጆች ከወላጆቻቸው ይልቅ እኩዮቻቸውን መቅረብ የሚቀናቸው ለምንድን ነው?

በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ ለሚገኙ ልጆቻችሁ ተግሣጽ መስጠት የምትችሉት እንዴት ነው?

ተግሣጽ መስጠት ሲባል ማስተማር ማለት ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችሁን ታዛዥነትን ለማስተማር እንድትችሉ ይረዷችኋል።

በጉርምስና ዕድሜ ላይ ለሚገኝ ልጃችሁ መመሪያ ማውጣት

ጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚገኘው ልጃችሁ ባወጣችኋቸው መመሪያዎች ሁልጊዜ የሚናደድ ከሆነ ምን ማድረግ ትችላላችሁ?

ኢንተርኔት ስለሚያስከትለው አደጋ ወጣቶችን ማስተማር

ለልጃችሁ ሕግ ከማውጣት ይልቅ በራሱ ጥሩ ውሳኔ እንዲያደርግ ልትረዱት የምትችሉት እንዴት ነው?

ልጄ ማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጠቀም ልፍቀድለት?

ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ የሚረዷችሁ አራት ጥያቄዎች።

በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ልጃችሁ ማኅበራዊ ሚዲያን በማይጎዳ መንገድ እንዲጠቀም ማሠልጠን

በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኝ ልጃችሁ ራሱን ከጉዳት እንዲጠብቅ እርዱት።

ስለ ሴክስቲንግ ከልጃችሁ ጋር መነጋገር የምትችሉት እንዴት ነው?

ችግሩ በልጃችሁ ላይ እስኪደርስ ድረስ አትጠብቁ። ሴክስቲንግ ስላለው አደጋ ከልጃችሁ ጋር ተወያዩ።

በሰውነታቸው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወጣቶችን መርዳት

በአሥራዎቹ ዕድሜ የሚገኙ አንዳንድ ወጣቶች ሆን ብለው በሰውነታቸው ላይ ጉዳት ያደርሳሉ። እንዲህ እንዲያደርጉ የሚገፋፋቸው ምንድን ነው? ልጃችሁን ልትረዷት የምትችሉት እንዴት ነው?

ወጣቶች

የእኩዮችን ተጽዕኖ መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

የእኩዮች ተጽዕኖ ጥሩ ሰዎችን መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የእኩዮች ተጽዕኖን በተመለከተ ማወቅ የሚገባህ ነገር ምንድን ነው? እንዴትስ መቋቋም ትችላለህ?

የሚሰጥህን እርማት እንዴት ልትቀበል ይገባል?

ስሜትህን እንደጎዳ የተሰማህ ምክር ወይም እርማት እንዲያውም በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እንዴት?

የጽሑፍ መልእክት ስትለዋወጡ መልካም ምግባር ማሳየት

የጽሑፍ መልእክትህን ለማየት ጨዋታህን ማቋረጥ ተገቢ ነው? ወይስ ጨዋታውን ላለማቋረጥ ስትል መልእክቱን ችላ ማለት ይሻላል?

ፈታኝ ስሜቶችን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

ሰዎች ከፈለጉ ፈታኝ የሆኑ ስሜቶችን ማሸነፍ ይችላሉ። ሁልጊዜ ትክክለኛ የሆነውን ለማድረግ ያለህን ቁርጠኝነት ለማጠናከር እንዲሁም በፈተና እንዳትሸነፍ የሚረዱህን ስድስት ምክሮች ተመልከት።

ቁጣን መቆጣጠር የሚቻልበት መንገድ

ቁጣን ለመቆጣጠር የሚረዱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ አምስት ምክሮች።

ብቸኝነትን መቋቋም የሚቻለው እንዴት ነው?

የብቸኝነት ስሜት በጤንነትህ ላይ በየቀኑ 15 ሲጋራዎችን ከማጨስ ጋር የሚተካከል ጉዳት ሊያስከትልብህ ይችላል። እንደተገለልክ ወይም ብቸኛ እንደሆንክ እንዳይሰማህ ምን ማድረግ ትችላለህ?

መጠናናት ስታቆሙ

ከአንድ ሰው ጋር መለያየት የሚያስከትለውን ሥቃይ ተቋቁሞ መቀጠል የሚቻለው እንዴት ነው?

ወደ ቤተሰቦችህ መመለስ ሲኖርብህ

ከቤት ወጥተህ ራስህን ችለህ መኖር ከጀመርክ በኋላ ኑሮ ከብዶሃል? በዚህ ርዕስ ውስጥ የቀረቡት ሐሳቦች እንደገና ራስህን ችለህ እንድትኖር ሊረዱህ ይችላሉ።

እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?

ጓደኝነትን ለማጠናከር የሚረዱ አራት ነጥቦችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ለውጥን ማስተናገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ለውጥ የማይቀር ነገር ነው። አንዳንዶች ያጋጠማቸውን ለውጥ ለማስተናገድ ምን እንዳደረጉ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ወላጅ ሲሞት

ወላጅን በሞት ማጣት ከባድ ሐዘን ያስከትላል። ወላጃቸውን በሞት ያጡ ልጆች የደረሰባቸውን ሐዘን እንዲቋቋሙ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

የጀብደኝነት ድርጊት መፈጸም ምን ጉዳት አለው?

ብዙ ወጣቶች አቅማቸውን የሚፈትን ድርጊት መፈጸም ያስደስታቸዋል፤ አንዳንድ ጊዜ ይህን የሚያደርጉት ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ነው። አንተስ እንዲህ ለማድረግ ትፈተናለህ?