በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የራእይ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • አምላክ በኢየሱስ በኩል የገለጠው ራእይ (1-3)

    • ለሰባቱ ጉባኤዎች የተላከ ሰላምታ (4-8)

      • ‘እኔ አልፋና ኦሜጋ ነኝ’ (8)

    • ዮሐንስ በመንፈስ ወደ ጌታ ቀን ተወሰደ (9-11)

    • ክብር የተጎናጸፈው ኢየሱስ በራእይ ታየ (12-20)

  • 2

    • ለኤፌሶን (1-7)፣ ለሰምርኔስ (8-11)፣ ለጴርጋሞን (12-17)፣ ለትያጥሮን የተላከ መልእክት (18-29)

  • 3

    • ለሰርዴስ (1-6)፣ ለፊላደልፊያ (7-13)፣ ለሎዶቅያ የተላከ መልእክት (14-22)

  • 4

    • ይሖዋ በሰማይ ላይ ሆኖ በራእይ ታየ (1-11)

      • ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር (2)

      • በዙፋኖች ላይ የተቀመጡ 24 ሽማግሌዎች (4)

      • አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት (6)

  • 5

    • በሰባት ማኅተሞች የታሸገ ጥቅልል (1-5)

    • በጉ ጥቅልሉን ወሰደ (6-8)

    • በጉ ማኅተሙን ለመክፈት ብቁ ሆኖ ተገኘ (9-14)

  • 6

    • በጉ የመጀመሪያዎቹን ስድስት ማኅተሞች ከፈተ (1-17)

      • በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ድል አድራጊ (1, 2)

      • ከምድር ላይ ሰላምን የሚወስድ ደማቅ ቀይ ቀለም ያለው ፈረስ ጋላቢ (3, 4)

      • ረሃብ የሚያመጣው የጥቁሩ ፈረስ ጋላቢ (5, 6)

      • ሞት የተባለው የግራጫው ፈረስ ጋላቢ (7, 8)

      • የታረዱ ሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያው በታች ታዩ (9-11)

      • ታላቅ የምድር ነውጥ (12-17)

  • 7

    • አጥፊ ነፋሳትን የያዙ አራት መላእክት (1-3)

    • የ144,000ዎቹ መታተም (4-8)

    • ነጭ ልብስ የለበሰ እጅግ ብዙ ሕዝብ (9-17)

  • 8

    • ሰባተኛው ማኅተም ተከፈተ (1-6)

    • የመጀመሪያዎቹ አራት መለከቶች ተነፉ (7-12)

    • ሦስት ወዮታዎች ታወጁ (13)

  • 9

    • አምስተኛው መለከት (1-11)

    • አንደኛው ወዮታ አልፏል፤ ሁለት ወዮታዎች ይመጣሉ (12)

    • ስድስተኛው መለከት (13-21)

  • 10

    • ትንሽ ጥቅልል የያዘ ብርቱ መልአክ (1-7)

      • “ከእንግዲህ ወዲህ መዘግየት አይኖርም” (6)

      • ‘ቅዱሱ ሚስጥር ይፈጸማል’ (7)

    • ዮሐንስ ትንሿን ጥቅልል በላ (8-11)

  • 11

    • ሁለቱ ምሥክሮች (1-13)

      • ማቅ ለብሰው ለ1,260 ቀናት ትንቢት ተናገሩ (3)

      • ተገድለው ሳይቀበሩ ቀሩ (7-10)

      • ከሦስት ቀን ተኩል በኋላ ሕያው ሆኑ (11, 12)

    • ሁለተኛው ወዮታ አልፏል፤ ሦስተኛው እየመጣ ነው (14)

    • ሰባተኛው መለከት (15-19)

      • “የጌታችንና የእሱ መሲሕ መንግሥት” (15)

      • ምድርን እያጠፉ ያሉት ይጠፋሉ (18)

  • 12

    • ሴቲቱ፣ ወንዱ ልጅና ዘንዶው (1-6)

    • ሚካኤል ከዘንዶው ጋር ተዋጋ (7-12)

      • ዘንዶው ወደ ምድር ተወረወረ (9)

      • ዲያብሎስ ጥቂት ጊዜ እንደቀረው ያውቃል (12)

    • ዘንዶው ሴቲቱን አሳደዳት (13-17)

  • 13

    • ሰባት ራሶች ያሉት አንድ አውሬ ከባሕር ወጣ (1-10)

    • ሁለት ቀንዶች ያሉት አውሬ ከምድር ወጣ (11-13)

    • ሰባት ራሶች ያሉት አውሬ ምስል (14, 15)

    • የአውሬው ምልክትና ቁጥር (16-18)

  • 14

    • በጉና 144,000ዎቹ (1-5)

    • ሦስት መላእክት ያስተላለፉት መልእክት (6-12)

      • ምሥራች የያዘ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር ታየ (6, 7)

    • “ከጌታ ጋር ያላቸውን አንድነት ጠብቀው የሚሞቱ ደስተኞች ናቸው” (13)

    • የምድር መከር (14-20)

  • 15

    • “ሰባት መቅሰፍቶች የያዙ ሰባት መላእክት” (1-8)

      • ‘የሙሴና የበጉ መዝሙር’ (3, 4)

  • 16

    • ‘የአምላክን ቁጣ የያዙ ሰባት ሳህኖች’ (1-21)

      • መላእክት በምድር (2)፣ በባሕር (3)፣ በወንዞችና በምንጮች (4-7)፣ በፀሐይ (8, 9)፣ በአውሬው ዙፋን (10, 11)፣ በኤፍራጥስና (12-16) በአየር ላይ አፈሰሱ (17-21)

      • በአርማጌዶን የሚካሄድ የአምላክ ጦርነት (14, 16)

  • 17

    • ‘በታላቂቱ ባቢሎን’ ላይ የተላለፈ ፍርድ” (1-18)

      • ደማቅ ቀይ አውሬ ላይ የተቀመጠችው ታላቂቱ አመንዝራ (1-3)

      • ‘አውሬው ከዚህ በፊት ነበር፤ አሁን ግን የለም፤ ከጥልቁም ይወጣል’ (8)

      • አሥሩ ቀንዶች ከበጉ ጋር ይዋጋሉ (12-14)

      • አሥሩ ቀንዶች አመንዝራዋን ይጠሏታል (16, 17)

  • 18

    • “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች!” (1-8)

      • ‘ሕዝቤ ሆይ፣ ከእሷ ውጡ’ (4)

    • በባቢሎን ውድቀት ያለቅሳሉ (9-19)

    • ባቢሎን በመውደቋ በሰማይ ደስታ ሆነ (20)

    • ባቢሎን እንደ ድንጋይ ባሕር ውስጥ ትጣላለች (21-24)

  • 19

    • ለወሰደው የፍርድ እርምጃ “ያህን አወድሱ!” (1-10)

      • የበጉ ሠርግ (7-9)

    • የነጭ ፈረስ ጋላቢ (11-16)

    • “ታላቁ የአምላክ ራት” (17, 18)

    • አውሬው ድል ተነሳ (19-21)

  • 20

    • ሰይጣን ለ1,000 ዓመት ታሰረ (1-3)

    • ከክርስቶስ ጋር ለ1,000 ዓመት ይገዛሉ (4-6)

    • ሰይጣን ይፈታል፤ ከዚያም ይጠፋል (7-10)

    • ሙታን በነጩ ዙፋን ፊት ፍርድ ተሰጣቸው (11-15)

  • 21

    • “አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር” (1-8)

      • “ከእንግዲህ ወዲህ ሞት አይኖርም” (4)

      • “ሁሉንም ነገር አዲስ አደርጋለሁ” (5)

    • ስለ አዲሲቱ ኢየሩሳሌም የተሰጠ መግለጫ (9-27)

  • 22

    • “የሕይወት ውኃ ወንዝ” (1-5)

    • መደምደሚያ (6-21)

      • ‘ና! የሕይወትን ውኃ በነፃ ውሰድ’ (17)

      • “ጌታ ኢየሱስ፣ ና” (20)