ምሳሌ 18:1-24

  • ራስን ማግለል ራስ ወዳድነትና ጥበብ የጎደለው ነው (1)

  • “የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው” (10)

  • ሀብት ጥበቃ አያስገኝም (11)

  • ሁለቱንም ወገኖች መስማት ጥበብ ነው (17)

  • “ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ” (24)

18  ራሱን የሚያገል ሰው ሁሉ የራስ ወዳድነት ምኞቱን ያሳድዳል፤ጥበብንም* ሁሉ ይቃወማል።*   ሞኝ ሰው ማስተዋል አያስደስተውም፤ይልቁንም በልቡ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል።+   ክፉ ሰው ሲመጣ ንቀትም ይመጣል፤ከውርደትም ጋር ኀፍረት ይመጣል።+   ከሰው አፍ የሚወጣ ቃል ጥልቅ ውኃ ነው።+ የጥበብ ምንጭ የሚንዶለዶል ጅረት ነው።   ለክፉ ሰው ማድላት፣ጻድቁንም ፍትሕ መንፈግ+ መልካም አይደለም።+   የሞኝ ሰው ንግግር ጠብ ያስነሳል፤+አፉም ዱላ ይጋብዛል።+   የሞኝ አንደበት መጥፊያው ነው፤+ከንፈሮቹም ለሕይወቱ* ወጥመድ ናቸው።   ስም አጥፊ የሚናገረው ቃል ጣፋጭ እንደሆነ ቁራሽ ምግብ ነው፤*+በፍጥነት ተውጦ በቀጥታ ወደ ሆድ ይገባል።+   በሥራው ታካች የሆነ ሰው ሁሉ፣የአጥፊ ወንድም ነው።+ 10  የይሖዋ ስም ጽኑ ግንብ ነው።+ ጻድቅ ወደዚያ በመሮጥ ጥበቃ ያገኛል።*+ 11  የባለጸጋ ሰው ሀብት የተመሸገ ከተማው ነው፤በሐሳቡም ጥበቃ እንደሚያስገኝ ግንብ አድርጎ ይመለከተዋል።+ 12  ሰው ለውድቀት ከመዳረጉ በፊት ልቡ ይታበያል፤+ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።+ 13  እውነታውን ከመስማቱ በፊት መልስ የሚሰጥ ሰው፣ሞኝነት ይሆንበታል፤ ውርደትም ይከናነባል።+ 14  ጠንካራ መንፈስ ያለው ሰው ሕመሙን መቋቋም ይችላል፤+የተደቆሰን መንፈስ* ግን ማን ሊቋቋም ይችላል?+ 15  የአስተዋይ ሰው ልብ እውቀትን ያገኛል፤+የጥበበኛም ጆሮ እውቀትን ለማግኘት ይጥራል። 16  ስጦታ ለሰጪው መንገዱን ይከፍትለታል፤+በታላላቅ ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል። 17  ክሱን አስቀድሞ ያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤+ይህም ሌላው ወገን መጥቶ እስኪመረምረው ድረስ ነው።+ 18  ዕጣ መጣል ጭቅጭቅ እንዲያበቃ ያደርጋል፤+ኃይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል። 19  የተበደለ ወንድም ከተመሸገች ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤+እንደ ግንብ በሮች መቀርቀሪያም የጠነከረ ጠብ አለ።+ 20  ሰው በአፉ ፍሬ ሆዱ ይሞላል፤+ከንፈሩም በሚያስገኘው ምርት ይረካል። 21  አንደበት የሞትና የሕይወት ኃይል አላት፤+ሊጠቀምባት የሚወድ ፍሬዋን ይበላል።+ 22  ጥሩ ሚስት ያገኘ ጥሩ ነገር አግኝቷል፤+የይሖዋንም ሞገስ* ያገኛል።+ 23  ድሃ እየተለማመጠ ይናገራል፤ሀብታም ግን በኃይለ ቃል ይመልሳል። 24  እርስ በርስ ከመጠፋፋት ወደኋላ የማይሉ ጓደኛሞች አሉ፤+ነገር ግን ከወንድም ይበልጥ የሚቀርብ ጓደኛ አለ።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ማስተዋል የታከለበትንም ጥበብ።”
ወይም “ይንቃል።”
ወይም “ለነፍሱ።”
ወይም “ተስገብግበው እንደሚውጡት ነገር ነው።”
ቃል በቃል “ከፍ ይላል።” ግለሰቡ እንደማይደረስበትና ከአደጋ እንደሚጠበቅ ያመለክታል።
ወይም “ከባድ የተስፋ መቁረጥ ስሜትን።”
ወይም “በጎ ፈቃድ።”