ምሳሌ 16:1-33

  • ‘ይሖዋ ውስጣዊ ዓላማን ይመረምራል’ (2)

  • ሥራህን ለይሖዋ አደራ ስጥ (3)

  • ‘ትክክለኛ ሚዛን ከይሖዋ ነው’ (11)

  • ‘ኩራት ጥፋትን ይቀድማል’ (18)

  • ‘ሽበት የውበት ዘውድ ነው’ (31)

16  ሰው የልቡን ሐሳብ ያዘጋጃል፤*የሚሰጠው መልስ* ግን ከይሖዋ ዘንድ ነው።+   ሰው መንገዱ ሁሉ ትክክል* መስሎ ይታየዋል፤+ይሖዋ ግን ውስጣዊ ዓላማን* ይመረምራል።+   የምታደርገውን ሁሉ ለይሖዋ አደራ ስጥ፤*+ዕቅድህም ሁሉ ይሳካል።   ይሖዋ ማንኛውንም ነገር ያዘጋጀው ለራሱ ዓላማ ነው፤ክፉውም ሰው እንኳ በመዓት ቀን እንዲጠፋ ያደርጋል።+   ይሖዋ ኩሩ ልብ ያለውን ሁሉ ይጸየፋል።+ እንዲህ ያለው ሰው ሳይቀጣ እንደማይቀር እርግጠኛ ሁን።   በታማኝ ፍቅርና በታማኝነት በደል ይሰረያል፤+ሰውም ይሖዋን በመፍራት ከክፋት ይርቃል።+   ይሖዋ በሰው አካሄድ ደስ በሚሰኝበት ጊዜጠላቶቹ እንኳ ሳይቀሩ ከሰውየው ጋር ሰላም እንዲኖራቸው ያደርጋል።+   አግባብ ባልሆነ መንገድ ከሚገኝ ብዙ ገቢ ይልቅበጽድቅ የሚገኝ ጥቂት ነገር ይሻላል።+   ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ይሖዋ ግን አካሄዱን ይመራለታል።+ 10  የንጉሥ ከንፈር በመንፈስ ተመርቶ ውሳኔ* መስጠት ይገባዋል፤+ፍትሕን ፈጽሞ ማዛባት የለበትም።+ 11  ትክክለኛ መለኪያና ሚዛን ከይሖዋ ናቸው፤በከረጢት ውስጥ ያሉት መለኪያዎች ሁሉ የእሱ ሥራ ናቸው።+ 12  ክፉ ድርጊት በነገሥታት ዘንድ አስጸያፊ ነው፤+ዙፋን የሚጸናው በጽድቅ ነውና።+ 13  ነገሥታት የጽድቅ ንግግር ደስ ያሰኛቸዋል። ሐቁን የሚናገር ሰው ይወዳሉ።+ 14  የንጉሥ ቁጣ እንደ ሞት መልእክተኛ ነው፤+ጥበበኛ ሰው ግን ቁጣውን ያበርደዋል።*+ 15  የንጉሥ ፊት ሲፈካ ሰው በደስታ ይኖራል፤ሞገሱም ዝናብ እንዳዘለ የበልግ ደመና ነው።+ 16  ጥበብን ማግኘት ወርቅ ከማግኘት ምንኛ የተሻለ ነው!+ ማስተዋልን ማግኘትም ብር ከማግኘት ይመረጣል።+ 17  ቅኖች ከክፋት ጎዳና ይርቃሉ። መንገዱን የሚጠብቅ ሁሉ በሕይወት ይኖራል።*+ 18  ኩራት ጥፋትን፣የትዕቢት መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።+ 19  የትዕቢተኞችን ምርኮ ከመካፈል ይልቅከየዋሆች ጋር የትሕትና መንፈስ* ማሳየት ይሻላል።+ 20  አንድን ነገር ጠለቅ ብሎ የሚያስተውል ሰው ስኬታማ ይሆናል፤*በይሖዋ የሚታመንም ደስተኛ ነው። 21  ልቡ ጥበበኛ የሆነ ሰው አስተዋይ ይባላል፤+በደግነት የሚናገርም* የማሳመን ችሎታ አለው።+ 22  ጥልቅ ማስተዋል ለባለቤቱ የሕይወት ምንጭ ነው፤ሞኞች ግን በገዛ ሞኝነታቸው ይቀጣሉ። 23  የጥበበኛ ሰው ልብ፣ አንደበቱ ጥልቅ ማስተዋል እንዲኖረው ያደርጋል፤+ለንግግሩም የማሳመን ችሎታ ይጨምርለታል። 24  ደስ የሚያሰኝ ቃል እንደ ማር እንጀራ ነው፤ለነፍስ* ጣፋጭ፣ ለአጥንትም ፈውስ ነው።+ 25  ለሰው ትክክለኛ መስሎ የሚታይ መንገድ አለ፤በመጨረሻ ግን ወደ ሞት ይመራል።+ 26  ሠራተኛን የምግብ ፍላጎቱ* ተግቶ እንዲሠራ ያደርገዋል፤ረሃቡ* እንዲህ እንዲያደርግ ያስገድደዋልና።+ 27  የማይረባ ሰው ክፋትን ይምሳል፤+ንግግሩ እንደሚለበልብ እሳት ነው።+ 28  ነገረኛ ሰው* ጭቅጭቅ ያስነሳል፤+ስም አጥፊም የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+ 29  ዓመፀኛ ሰው ባልንጀራውን ክፉ ነገር እንዲሠራ ያግባባዋል፤ወደተሳሳተ መንገድም ይመራዋል። 30  በዓይኑ እየጠቀሰ ተንኮል ይሸርባል። ከንፈሮቹን ነክሶ ሸር ይሠራል። 31  ሽበት በጽድቅ መንገድ ሲገኝ+የውበት* ዘውድ ነው።+ 32  ቶሎ የማይቆጣ ሰው+ ከኃያል ሰው፣ስሜቱን የሚቆጣጠርም* ከተማን ድል ከሚያደርግ ሰው ይሻላል።+ 33  ዕጣ ጭን ላይ ይጣላል፤+ውሳኔውን በሙሉ የሚያስተላልፈው ግን ይሖዋ ነው።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ትክክለኛው መልስ።” ቃል በቃል “የምላስ መልስ።”
ቃል በቃል “ልብን ማዘጋጀት የሰው ድርሻ ነው።”
ቃል በቃል “ንጹሕ።”
ቃል በቃል “መንፈስን።”
ቃል በቃል “ሥራህን ለይሖዋ አስተላልፍ።”
ወይም “መለኮታዊ ውሳኔ።”
ወይም “ያስወግደዋል።”
ወይም “ነፍሱን ይጠብቃል።”
ቃል በቃል “የተዋረደ መንፈስ።”
ቃል በቃል “ጥሩ ነገር ያገኛል።”
ወይም “በሚማርክ መንገድ የሚናገርም።” ቃል በቃል “ከንፈሩ ጣፋጭ የሆነም።”
ወይም “ለአፍ።” የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሱ።”
ቃል በቃል “አፉ።”
ወይም “ሴረኛ።”
ወይም “የክብር።”
ቃል በቃል “መንፈሱን የሚገዛም።”