የማቴዎስ ወንጌል 2:1-23

  • ኮከብ ቆጣሪዎች መጡ (1-12)

  • ወደ ግብፅ መሸሽ (13-15)

  • ሄሮድስ ወንዶች ልጆችን ገደለ (16-18)

  • ወደ ናዝሬት ተመለሱ (19-23)

2  በንጉሥ ሄሮድስ* ዘመን+ ኢየሱስ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ከተወለደ በኋላ ኮከብ ቆጣሪዎች* ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው፣  “የተወለደው የአይሁዳውያን ንጉሥ የሚገኘው የት ነው?+ በምሥራቅ ሳለን ኮከቡን በማየታችን ልንሰግድለት* መጥተናል” አሉ።  ንጉሥ ሄሮድስና መላው የኢየሩሳሌም ሕዝብ ይህን ሲሰሙ ተሸበሩ።  ንጉሡም የሕዝቡን የካህናት አለቆችና ጸሐፍት በሙሉ ሰብስቦ ክርስቶስ* የት እንደሚወለድ ጠየቃቸው።  እነሱም እንዲህ አሉት፦ “በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም+ ነው፤ ምክንያቱም ነቢዩ እንዲህ ብሎ ጽፏል፦  ‘በይሁዳ ምድር የምትገኚው አንቺ ቤተልሔም ሆይ፣ ለሕዝቤ ለእስራኤል እረኛ የሚሆን ገዢ ከአንቺ ስለሚወጣ በይሁዳ ገዢዎች ዘንድ ከሁሉ የተናቅሽ ከተማ አትሆኚም።’”+  ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹን በድብቅ ጠርቶ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በትክክል አረጋገጠ።  ኮከብ ቆጣሪዎቹንም “ሄዳችሁ ሕፃኑን በደንብ ፈልጉ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም ሄጄ እንድሰግድለት መጥታችሁ ንገሩኝ” ብሎ ወደ ቤተልሔም ላካቸው።  እነሱም ንጉሡ የነገራቸውን ከሰሙ በኋላ ጉዟቸውን ቀጠሉ፤ እነሆም፣ በምሥራቅ ሳሉ ያዩት ኮከብ+ ሕፃኑ ባለበት ቦታ እስከቆመበት ጊዜ ድረስ ከፊት ከፊታቸው ይሄድ ነበር። 10  ኮከቡ መቆሙን ሲያዩ በጣም ተደሰቱ። 11  ወደ ቤት ሲገቡም ልጁን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።* ዕቃ መያዣቸውንም ከፍተው ወርቅ፣ ነጭ ዕጣንና ከርቤ በስጦታ መልክ አቀረቡለት። 12  ይሁንና ወደ ሄሮድስ ተመልሰው እንዳይሄዱ በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጣቸው+ በሌላ መንገድ አድርገው ወደ አገራቸው ሄዱ። 13  እነሱ ከሄዱ በኋላ የይሖዋ* መልአክ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ+ “ሄሮድስ ሕፃኑን አፈላልጎ ሊገድለው ስላሰበ ተነስ፣ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፤ እኔ እስካሳውቅህም ድረስ እዚያው ቆይ” አለው። 14  ስለዚህ ዮሴፍ ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ በሌሊት ወደ ግብፅ ሄደ። 15  ሄሮድስ እስኪሞት ድረስ እዚያው ቆየ። በመሆኑም ይሖዋ* “ልጄን ከግብፅ ጠራሁት”+ ብሎ በነቢዩ አማካኝነት የተናገረው ቃል ተፈጸመ። 16  ከዚያም ሄሮድስ ኮከብ ቆጣሪዎቹ እንዳታለሉት ሲያውቅ በጣም ተናደደ፤ ኮከቡ የታየበትን ጊዜ በተመለከተ ከኮከብ ቆጣሪዎቹ ባገኘው መረጃ መሠረት+ ሰዎች ልኮ በቤተልሔምና በአካባቢዋ ሁሉ የሚገኙትን ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑትን ወንዶች ልጆች በሙሉ አስገደለ። 17  በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የተናገረው የሚከተለው ቃል ተፈጸመ፦ 18  “የለቅሶና የዋይታ ድምፅ በራማ ተሰማ። ራሔል+ ስለ ልጆቿ አለቀሰች፤ ልጆቿ ስለሌሉ ልትጽናና አልቻለችም።”+ 19  ሄሮድስ ከሞተ በኋላ የይሖዋ* መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ተገልጦ+ 20  “ተነስ፣ የሕፃኑን ሕይወት* ለማጥፋት የሚፈልጉት ሰዎች ስለሞቱ ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ እስራኤል ምድር ተመለስ” አለው። 21  ዮሴፍም ተነሳ፤ ሕፃኑንና የሕፃኑን እናት ይዞ ወደ እስራኤል ምድር ተመለሰ። 22  ሆኖም አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ፋንታ ይሁዳን እየገዛ እንዳለ በመስማቱ ወደዚያ መሄድ ፈራ። በተጨማሪም በሕልም መለኮታዊ ማስጠንቀቂያ ስለተሰጠው+ ወደ ገሊላ+ ምድር ሄደ። 23  ደግሞም “የናዝሬት ሰው* ይባላል” ተብሎ በነቢያት የተነገረው+ ይፈጸም ዘንድ ናዝሬት+ ወደምትባል ከተማ መጥቶ መኖር ጀመረ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ሰብአ ሰገል።”
ወይም “እጅ ልንነሳው።”
ወይም “መሲሑ፤ የተቀባው።”
ወይም “እጅ ነሱት።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ነፍስ።”
“ቀንበጥ” የሚል ትርጉም ካለው የዕብራይስጥ ቃል የመጣ ሳይሆን አይቀርም።