በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዳንኤል መጽሐፍ

ምዕራፎች

1 2 3 4 5 6 7 8 9 10 11 12

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ባቢሎናውያን ኢየሩሳሌምን ከበቡ (1, 2)

    • የንጉሥ ዘር ለሆኑ ወጣት ምርኮኞች የተሰጠ ልዩ ሥልጠና (3-5)

    • የአራት ዕብራውያን ታማኝነት ተፈተነ (6-21)

  • 2

    • ንጉሥ ናቡከደነጾር የሚረብሽ ሕልም አየ (1-4)

    • ሕልሙን ሊፈታ የሚችል ጥበበኛ ሰው ጠፋ (5-13)

    • ዳንኤል የአምላክን እርዳታ ጠየቀ (14-18)

    • ሚስጥሩን ስለገለጠለት አምላክን አወደሰ (19-23)

    • ዳንኤል ሕልሙን ለንጉሡ ነገረው (24-35)

    • የሕልሙ ፍቺ (36-45)

      • ምስሉን የሚያደቅ ድንጋይ (44, 45)

    • ንጉሡ ዳንኤልን አከበረው (46-49)

  • 3

    • ንጉሥ ናቡከደነጾር ያቆመው የወርቅ ምስል (1-7)

      • ለምስሉ እንዲሰግዱ አዘዘ (4-6)

    • ሦስት ዕብራውያን ባለመስገዳቸው ተከሰሱ (8-18)

      • ‘የአንተን አማልክት አናገለግልም’ (18)

    • የእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ (19-23)

    • ከእሳቱ በተአምር ዳኑ (24-27)

    • ንጉሡ የዕብራውያንን አምላክ ከፍ ከፍ አደረገ (28-30)

  • 4

    • ንጉሥ ናቡከደነጾር ለአምላክ ንጉሣዊ ሥልጣን እውቅና ሰጠ (1-3)

    • ንጉሡ ስለ አንድ ዛፍ ያየው ሕልም (4-18)

      • የወደቀው ዛፍ ሰባት ዘመናት ያልፉበታል (16)

      • አምላክ የሰው ልጆችን ይገዛል (17)

    • ዳንኤል የሕልሙን ትርጉም ተናገረ (19-27)

    • የመጀመሪያው ፍጻሜ በንጉሡ ላይ ደረሰ (28-36)

      • ንጉሡ ለሰባት ዘመናት አእምሮውን ሳተ (32, 33)

    • ንጉሡ የሰማይ አምላክን ከፍ ከፍ አደረገ (37)

  • 5

    • ንጉሥ ቤልሻዛር ያዘጋጀው ግብዣ (1-4)

    • በግድግዳ ላይ የተጻፈው የእጅ ጽሑፍ (5-12)

    • ዳንኤል የጽሑፉን ፍቺ እንዲያሳውቅ ተጠየቀ (13-25)

    • የጽሑፉ ፍቺ፦ የባቢሎን ውድቀት (26-31)

  • 6

    • የፋርስ ባለሥልጣናት በዳንኤል ላይ አሴሩ (1-9)

    • ዳንኤል መጸለዩን ቀጠለ (10-15)

    • ዳንኤል በአንበሶች ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ (16-24)

    • ንጉሥ ዳርዮስ የዳንኤልን አምላክ አከበረ (25-28)

  • 7

    • የአራቱ አራዊት ራእይ (1-8)

      • እብሪተኛ የሆነ ትንሽ ቀንድ ብቅ አለ (8)

    • ከዘመናት በፊት የነበረው አምላክ ችሎት ተቀመጠ (9-14)

      • የሰው ልጅ ንግሥና ተሰጠው (13, 14)

    • የራእዩ ትርጉም ለዳንኤል ተገለጸለት (15-28)

      • አራቱ አራዊት አራት ነገሥታት ናቸው (17)

      • ቅዱሳኑ መንግሥት ይቀበላሉ (18)

      • አሥር ቀንዶች ወይም ነገሥታት ይነሳሉ (24)

  • 8

    • የአንድ አውራ በግና የአንድ አውራ ፍየል ራእይ (1-14)

      • አንድ ትንሽ ቀንድ ራሱን ከፍ ከፍ አደረገ (9-12)

      • ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ምሽቶችና ንጋቶች እስኪያልፉ ድረስ (14)

    • ገብርኤል ራእዩን ተረጎመ (15-27)

      • የአውራ በጉና የአውራ ፍየሉ ማንነት ተገለጸ (20, 21)

      • “አስፈሪ መልክ ያለው ንጉሥ ይነሳል” (23-25)

  • 9

    • ዳንኤል ያቀረበው የኑዛዜ ጸሎት (1-19)

      • ኢየሩሳሌም ለ70 ዓመት ባድማ ትሆናለች (2)

    • ገብርኤል ወደ ዳንኤል መጣ (20-23)

    • በትንቢት የተነገሩ 70 ሳምንታት (24-27)

      • መሲሑ ከ69 ሳምንታት በኋላ ይገለጣል (25)

      • መሲሑ ይቆረጣል (26)

      • ከተማዋና ቅዱሱ ስፍራ ይጠፋሉ (26)

  • 10

    • ከአምላክ የተላከ መልእክተኛ ወደ ዳንኤል መጣ (1-21)

      • ሚካኤል መልአኩን ረዳው (13)

  • 11

    • የፋርስና የግሪክ ነገሥታት (1-4)

    • የደቡቡ ንጉሥና የሰሜኑ ንጉሥ (5-45)

      • አስገባሪ ይነሳል (20)

      • የቃል ኪዳኑ መሪ ይሰበራል (22)

      • የምሽጎቹ አምላክ ይከበራል (38)

      • የደቡቡ ንጉሥና የሰሜኑ ንጉሥ እርስ በርስ ይገፋፋሉ (40)

      • ከምሥራቅና ከሰሜን የሚመጣ ወሬ ይረብሸዋል (44)

  • 12

    • ‘የፍጻሜው ዘመንና’ ከዚያ በኋላ ያለው ጊዜ (1-13)

      • ሚካኤል ይነሳል (1)

      • ጥልቅ ማስተዋል ያላቸው ሰዎች ያበራሉ (3)

      • እውነተኛው እውቀት ይበዛል (4)

      • ዳንኤል ዕጣ ፋንታውን ለመቀበል ይነሳል (13)