ኢሳይያስ 11:1-16
11 ከእሴይ+ ጉቶ፣ ቅርንጫፍ ይወጣል፤ከሥሮቹም የሚወጣው ቀንበጥ ፍሬ ያፈራል።+
2 በእሱም ላይ የይሖዋ መንፈስ፣+የጥበብና+ የማስተዋል መንፈስ፣የምክርና የኃይል+ መንፈስ፣የእውቀትና ይሖዋን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።
3 ይሖዋን በመፍራትም ደስ ይሰኛል።+
ዓይኑ እንዳየ አይፈርድምወይም ጆሮው በሰማው ነገር ላይ ብቻ ተመሥርቶ አይወቅስም።+
4 ለችግረኞች በትክክል* ይፈርዳል፤በምድር ላሉ የዋሆች ጥቅም ሲል ሌሎችን ፍትሐዊ በሆነ መንገድ ይወቅሳል።
በአፉም በትር ምድርን ይመታል፤+በከንፈሩም እስትንፋስ* ክፉዎችን ይገድላል።+
5 ጽድቅ የወገቡ መታጠቂያ፣ታማኝነትም የጎኑ መታጠቂያ ይሆናል።+
6 ተኩላ ከበግ ጠቦት ጋር የሚቀመጥበት ጊዜ ይኖራል፤+ነብርም ከፍየል ግልገል ጋር ይተኛል፤ጥጃ፣ አንበሳና* የሰባ ከብት አብረው ይሆናሉ፤*+ትንሽ ልጅም ይመራቸዋል።
7 ላምና ድብ አብረው ይበላሉ፤ልጆቻቸውም አብረው ይተኛሉ።
አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል።+
8 ጡት የሚጠባ ሕፃንም በእባብ* ጉድጓድ ላይ ይጫወታል፤ጡት የጣለውም ሕፃን እጁን በመርዘኛ እባብ ጎሬ ላይ ያደርጋል።
9 በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ላይምንም ዓይነት ጉዳት ወይም ጥፋት አያደርሱም፤+ምክንያቱም ውኃ ባሕርን እንደሚሸፍንምድርም በይሖዋ እውቀት ትሞላለች።+
10 በዚያን ቀን የእሴይ ሥር+ ለሕዝቦች ምልክት* ሆኖ ይቆማል።+
ብሔራት ከእሱ መመሪያ ይሻሉ፤*+ማረፊያ ስፍራውም እጅግ የከበረ ይሆናል።
11 በዚያን ቀን ይሖዋ ዳግመኛ እጁን ዘርግቶ የተረፉትን የሕዝቡን ቀሪዎች ለሁለተኛ ጊዜ ከአሦር፣+ ከግብፅ፣+ ከጳትሮስ፣+ ከኢትዮጵያ፣*+ ከኤላም፣+ ከሰናኦር፣* ከሃማትና ከባሕር ደሴቶች+ መልሶ ይሰበስባል።
12 ለብሔራት ምልክት* ያቆማል፤ በየቦታው የተሰራጩትን እስራኤላውያንም መልሶ ያመጣቸዋል፤+ እንዲሁም የተበታተኑትን የይሁዳ ሰዎች ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ይሰበስባል።+
13 የኤፍሬም ቅናት ይወገዳል፤+ይሁዳንም የሚጠሉ ይጠፋሉ።
ኤፍሬም በይሁዳ አይቀናም፤ይሁዳም ኤፍሬምን አይጠላውም።+
14 በምዕራብ በኩል በፍልስጤም ተረተር* ላይ በድንገት ይወርዳሉ፤ግንባር ፈጥረው በምሥራቅ የሚኖሩ ሕዝቦችን ይዘርፋሉ።
በኤዶምና+ በሞዓብ+ ላይ እጃቸውን* ይዘረጋሉ፤አሞናውያንም ተገዢዎቻቸው ይሆናሉ።+
15 ይሖዋ የግብፅን ባሕረ ሰላጤ* ይከፍላል፤*+በወንዙም*+ ላይ እጁን በዛቻ ያወዛውዛል።
በሚያቃጥል እስትንፋሱ* የወንዙን ሰባት ጅረቶች ይመታል፤*ሰዎችም ከነጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋል።
16 እስራኤል ከግብፅ ምድር በወጣበት ጊዜ እንደሆነው ሁሉ፣ከሕዝቡ የተረፉት ቀሪዎችም+ ከአሦር የሚወጡበት ጎዳና+ ይኖራል።
የግርጌ ማስታወሻዎች
^ ወይም “በጽድቅ።”
^ ወይም “መንፈስ።”
^ ወይም “ደቦል አንበሳና።”
^ “ጥጃና አንበሳ አብረው ይሰማራሉ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ወይም “በጉበና።” በእስያና በአፍሪካ የሚገኝ እጅግ መርዘኛ የሆነ እባብ፤ ኮብራ።
^ ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”
^ ወይም “ብሔራት እሱን ይፈልጉታል።”
^ ባቢሎንን ያመለክታል።
^ ወይም “ከኩሽ።”
^ ወይም “ለምልክት የሚተከል ምሰሶ።”
^ ወይም “ኃይላቸውን።”
^ ቃል በቃል “ትከሻ።”
^ ቃል በቃል “ምላስ።”
^ “ያደርቃል” ማለትም ሊሆን ይችላል።
^ ኤፍራጥስን ያመለክታል።
^ ወይም “መንፈሱ።”
^ “ወንዙን መትቶ ሰባት ጅረት ያደርገዋል” ማለትም ሊሆን ይችላል።