ሚክያስ 5:1-15

  • በመላው ምድር ላይ ታላቅ የሚሆን ገዢ (1-6)

    • ከቤተልሔም የሚወጣ ገዢ (2)

  • የተረፉት እንደ ጠልና እንደ አንበሳ ይሆናሉ (7-9)

  • ምድሪቱ ትነጻለች (10-15)

5  “አንቺ ጥቃት የተሰነዘረብሽ ሴት ልጅ ሆይ፣አሁን ሰውነትሽን ትተለትያለሽ፤ዙሪያችንን ተከበናል።+ የእስራኤልን ፈራጅ ጉንጩን በዱላ ይመቱታል።+   ከይሁዳ አእላፋት* መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽውቤተልሔም ኤፍራታ+ ሆይ፣ምንጩ ከጥንት፣ ከረጅም ዘመን በፊት የሆነ፣በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።+   ስለዚህ ልትወልድ የተቃረበችው ሴት እስክትወልድ ድረስአሳልፎ ይሰጣቸዋል። የቀሩት ወንድሞቹም ወደ እስራኤል ሕዝብ ይመለሳሉ።   እሱ በይሖዋ ብርታትና በአምላኩ በይሖዋ ስም ታላቅነት ይነሳል፤መንጋውንም እንደ እረኛ ይጠብቃል።+ እነሱም በዚያ ያለስጋት ይቀመጣሉ፤+በዚያን ጊዜ ታላቅነቱ እስከ ምድር ዳርቻ ይደርሳልና።+   እሱም ሰላም ያመጣል።+ አሦራዊው ምድራችንን ከወረረና የማይደፈሩ ማማዎቻችንን ከረገጠ+በእሱ ላይ ሰባት እረኞችን፣ አዎ ከሰው ልጆች መካከል ስምንት አለቆችን* እናስነሳበታለን።   እነሱ የአሦርን ምድር በሰይፍ ይቀጣሉ፤+የናምሩድንም+ ምድር መግቢያዎች ይቆጣጠራሉ። አሦራዊው ምድራችንን ሲወርና ክልላችንን ሲረግጥእሱ ይታደገናል።+   የተረፉት የያዕቆብ ወገኖች በብዙ ሕዝቦች መካከል፣ከይሖዋ ዘንድ እንደሚወርድናሰውን ተስፋ እንደማያደርግወይም የሰው ልጆችን እንደማይጠባበቅ ጠል፣በአትክልትም ላይ እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ።   በዱር እንስሳት መካከል እንዳለ አንበሳ፣በሚያልፍበት ጊዜ እየረጋገጠና እየሰባበረ እንደሚሄድ፣በበግ መንጎች መካከል እንዳለ ደቦል አንበሳ፣የተረፉት የያዕቆብ ወገኖችም በብሔራት፣በብዙ ሕዝቦችም መካከል እንዲሁ ይሆናሉ፤ሊያስጥል የሚችልም አይኖርም።   እጅህ ከባላጋራዎችህ በላይ ከፍ ከፍ ትላለች፤ጠላቶችህም ሁሉ ይወገዳሉ።” 10  “በዚያም ቀን” ይላል ይሖዋ፣“ፈረሶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ ሠረገሎችህንም አጠፋለሁ። 11  በምድርህ ላይ የሚገኙትን ከተሞች እደመስሳለሁ፤የተመሸጉ ስፍራዎችህንም ሁሉ አፈራርሳለሁ። 12  ጥንቆላህን አስወግዳለሁ፤*ከእንግዲህም አስማተኛ በመካከልህ አይኖርም።+ 13  የተቀረጹ ምስሎችህንና ዓምዶችህን ከመካከልህ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ወዲህ ለእጆችህ ሥራ አትሰግድም።+ 14  የማምለኪያ ግንዶችህንም* ከመካከልህ እነቅላለሁ፤+ከተሞችህንም እደመስሳለሁ። 15  ታዛዥ ያልሆኑትን ብሔራት፣በቁጣና በንዴት እበቀላለሁ።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጎሳዎች።”
ወይም “መሪዎችን።”
ቃል በቃል “ከእጅህ አስወግዳለሁ።”