በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ማንነት

ማንነትህን አግኝተኸዋል? የትኞቹ እሴቶች ይገልጹኛል ብለህ ታስባለህ? ማንነትህን ፈልገህ ማግኘትህ የራስህ ሰው እንድትሆን ይረዳሃል፤ ሌሎች ሰዎች እንዳሻቸው እንዲቆጣጠሩህም አትፈቅድም።

ስብዕናዬ

ማንነትን ፍለጋ

በሕይወትህ የሚያጋጥሙህን ችግሮች በስኬት ማለፍ የምትችልበትን ሚስጥር ተመልከት።

ከሰዎች ጋር የመጨዋወት ችሎታዬን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?

ጭውውት ለመጀመርና ለማስቀጠል የሚረዷችሁ ሦስት ምክሮች።

በሚዲያ ላይ የሚታዩ እኩዮቼን መምሰል የሌለብኝ ለምንድን ነው?—ክፍል 1 (ለሴቶች)

የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው የሚሰማቸው በርካታ ወጣቶች በሚዲያ ላይ የሚታዩ ሰዎችን እየመሰሉ እንደሆነ አይገባቸውም።

በሚዲያ ላይ የሚታዩ እኩዮቼን መምሰል የሌለብኝ ለምንድን ነው?—ክፍል 2፦ ለወንዶች

በሚዲያ ላይ የሚታዩ እኩዮችህን ለመምሰል መሞከርህ ተወዳጅ እንዳትሆን ሊያደርግ እንደሚችል አስበህ ታውቃለህ?

ኃላፊነት የሚሰማው ሰው ነኝ?

አንዳንድ ወጣቶች ከሌሎች የበለጠ ነፃነት ይሰጣቸዋል። ለምን?

ሐቀኛ መሆን ለምን አስፈለገ?

ሐቀኛ ያልሆኑ ሰዎች ይጠቀሙ የለ?

ምን ያህል ሐቀኛ ነህ?

ይህን ባለሦስት ክፍል መልመጃ በመጠቀም ራስህን መርምር።

መንፈሰ ጠንካራ ነኝ?

ችግር ማጋጠሙ አይቀርም፤ ያጋጠመህ ችግር ቀላልም ሆነ ከባድ የመንፈስ ጥንካሬ ማዳበር ያስፈልግሃል።

ለውጥን ማስተናገድ የሚቻለው እንዴት ነው?

ለውጥ የማይቀር ነገር ነው። አንዳንዶች ያጋጠማቸውን ለውጥ ለማስተናገድ ምን እንዳደረጉ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የሚሰጥህን እርማት እንዴት ልትቀበል ይገባል?

ስሜትህን እንደጎዳ የተሰማህ ምክር ወይም እርማት እንዲያውም በጣም ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፤ እንዴት?

እርማት ሲሰጠኝ ምን ላድርግ?

አንዳንድ ሰዎች ትንሽ እርማት ሲሰጣቸው ቅስማቸው ወዲያው ይሰበራል። አንተስ እንዲህ ዓይነት ባሕርይ አለህ?

ሕሊናዬን ማሠልጠን የምችለው እንዴት ነው?

ሕሊናህ ያለህን የሥነ ምግባር አቋምና ምን ዓይነት ሰው እንደሆንክ ያሳይሃል። ሕሊናህ ስለ አንተ ምን ይላል?

መድልዎ ምንድን ነው?

መድልዎ በታሪክ ዘመናት ሁሉ የሰው ልጆችን ሲያጠቃ ቆይቷል። ይህ በሽታ በውስጥህ ሥር እንዳይሰድ የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር ተግባራዊ አድርግ።

ከራሴ ፍጽምና እጠብቃለሁ?

ጥሩ ደረጃ ላይ ለመድረስ በሚደረግ ጥረትና ሊደረስበት የማይችል ግብ ላይ ለመድረስ በመጣጣር መካከል ሰፊ ልዩነት አለ።

ፍጽምና የመጠበቅ ዝንባሌን ማሸነፍ የሚቻለው እንዴት ነው?

ይህ የመልመጃ ሣጥን ከራስህም ሆነ ከሌሎች በምትጠብቀው ነገር ረገድ ምክንያታዊ እንድትሆን ይረዳሃል።

ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ መሆን ምን ያህል አስፈላጊ ነው?

አንዳንዶች፣ ብዙ ፎሎወር ወይም ላይክ ለማግኘት ሲሉ ሕይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ያደርጋሉ። ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዋቂ መሆን ይህን ያህል መሥዋዕት ሊከፈልለት የሚገባ ነገር ነው?

ሁለት ዓይነት ሕይወት መኖሬን እንዴት ላቁም?

ይህን የማታለል ጎዳና መከተልህን ለማቆም የሚረዱህ አራት እርምጃዎች።

የእኩዮችን ተጽዕኖ መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

የእኩዮች ተጽዕኖ ጥሩ ሰዎችን መጥፎ ነገር እንዲያደርጉ ሊገፋፋቸው ይችላል። የእኩዮች ተጽዕኖን በተመለከተ ማወቅ የሚገባህ ነገር ምንድን ነው? እንዴትስ መቋቋም ትችላለህ?

የእኩዮቼን ተጽዕኖ መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን ከተከተልክ ይሳካልሃል፤ እንዴት የሚለውን ተመልከት።

በእኩዮች ተጽዕኖ አትሸነፍ!

የራስህ አቋም ያለህ ሰው ለመሆን የሚረዱ አራት ቀላል ዘዴዎች ቀርበውልሃል።

ለምታምንበት ነገር የጸና እምነት ይኑርህ!

ኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ የማስጠንቀቂያ መልእክት እንዲያውጅ የረዳው ምን እንደሆነ ለማወቅ ይህን መልመጃ እንድትሠራ እንጋብዝሃለን።

ጥሩ አርዓያ የሚሆነኝን ሰው መምረጥ የምችለው እንዴት ነው?

አርዓያ የሚሆንህ ሰው ማግኘትህ ችግር ውስጥ ከመግባት እንድትድን፣ ግቦችህ ላይ እንድትደርስና በሕይወትህ ስኬታማ እንድትሆን ሊረዳህ ይችላል። ሆኖም አርዓያ አድርገህ የምትመርጠው ማንን ነው?

አርዓያ የሚሆንህን ሰው ምረጥ

ይህ የመልመጃ ሣጥን አርዓያ የሚሆንህን ሰው አሊያም ማዳበር የምትፈልገውን ባሕርይ ለመምረጥ ይረዳሃል።

ተግባሬ

ሌሎችን መርዳት ያለብኝ ለምንድን ነው?

ለሌሎች ጥሩ ነገር ማድረግ ቢያንስ በሁለት መንገዶች ጥቅም ያስገኝልሃል። እነዚህ ሁለት ጥቅሞች ምንድን ናቸው?

ሌሎችን ለመርዳት ላደርጋቸው ያሰብኳቸው ነገሮች

ለሰዎች እርዳታ ለመስጠት ሩቅ መሄድ አያስፈልግህም። ይህ የመልመጃ ሣጥን በዚህ ረገድ የሚረዱ ሦስት ቀላል እርምጃዎችን ይዟል።

ስህተት ስሠራ ምን ማድረግ ይኖርብኛል?

የማይሳሳት ሰው የለም፤ ከስህተቱ የሚማረው ግን ሁሉም ሰው አይደለም።

ፈታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የምችለው እንዴት ነው?

ተገቢ ያልሆኑ ምኞቶችን ለመቆጣጠር ልትወስዳቸው የምትችላቸውን ሦስት እርምጃዎች አንብብ።

ፈታኝ ስሜቶችን መቋቋም የሚቻልበት መንገድ

ሰዎች ከፈለጉ ፈታኝ የሆኑ ስሜቶችን ማሸነፍ ይችላሉ። ሁልጊዜ ትክክለኛ የሆነውን ለማድረግ ያለህን ቁርጠኝነት ለማጠናከር እንዲሁም በፈተና እንዳትሸነፍ የሚረዱህን ስድስት ምክሮች ተመልከት።

መልኬ

አለባበሴ እንዴት ነው?

ከአለባበስ ጋር የተያያዙ ሦስት የተለመዱ ስህተቶችን ማስወገድ የምትችለው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

አለባበስህ ምን ይመስላል?

ይህ መልመጃ ጥሩ አለባበስ እንዲኖርህ ይረዳሃል።

ወጣቶች ስለ ቁመና ምን ይላሉ?

ወጣቶች ስለ መልክ ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ ከባድ የሚሆንባቸው ለምን ሊሆን ይችላል? በዚህ ረገድ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

መልክና ቁመናዬ በጣም የሚያሳስበኝ ለምንድን ነው?

ለጉዳዩ ሚዛናዊ አመለካከት እንዲኖርህ የሚረዱህን ነገሮች ተመልከት።

ስለ መልኬ ከልክ በላይ እየተጨነቅሁ ነው?

መልክሽን የማትወጂው ከሆነ፣ ሚዛናዊ አመለካከት ማዳበር የምትችዪው እንዴት ነው?

ብነቀስ ምን ችግር አለው?

ጥበብ የሚንጸባረቅበት ውሳኔ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

ከመነቀስህ በፊት ቆም ብለህ አስብ

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የያዘ ንቅሳት ብነቀስስ?