በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንደኛ ሳሙኤል መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ሕልቃና እና ሁለቱ ሚስቶቹ (1-8)

    • ልጅ ያልነበራት ሐና፣ ይሖዋ ልጅ እንዲሰጣት ጸለየች (9-18)

    • ሳሙኤል ተወለደ እንዲሁም ለይሖዋ ተሰጠ (19-28)

  • 2

    • የሐና ጸሎት (1-11)

    • ሁለቱ የኤሊ ወንዶች ልጆች የፈጸሙት ኃጢአት (12-26)

    • ይሖዋ በኤሊ ቤት ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (27-36)

  • 3

    • ሳሙኤል ነቢይ ሆነ (1-21)

  • 4

    • ፍልስጤማውያን ታቦቱን ማረኩ (1-11)

    • ኤሊና ልጆቹ ሞቱ (12-22)

  • 5

    • ታቦቱ በፍልስጤማውያን ምድር (1-12)

      • ዳጎን ተዋረደ (1-5)

      • ፍልስጤማውያን በመቅሰፍት ተመቱ (6-12)

  • 6

    • ፍልስጤማውያን ታቦቱን ወደ እስራኤል መለሱ (1-21)

  • 7

    • ታቦቱ በቂርያትየአሪም (1)

    • ሳሙኤል እስራኤላውያን ‘ይሖዋን ብቻ እንዲያገለግሉ’ አጥብቆ አሳሰበ (2-6)

    • እስራኤላውያን ምጽጳ ላይ ድል ተቀዳጁ (7-14)

    • ሳሙኤል በእስራኤላውያን ላይ ፈራጅ ሆኖ አገለገለ (15-17)

  • 8

    • እስራኤላውያን ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ጠየቁ (1-9)

    • ሳሙኤል ሕዝቡን አስጠነቀቀ (10-18)

    • ይሖዋ ንጉሥ እንዲነግሥላቸው ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀበለ (19-22)

  • 9

    • ሳሙኤል ሳኦልን አገኘው (1-27)

  • 10

    • ሳኦል ንጉሥ እንዲሆን ተቀባ (1-16)

    • ሳኦል ሕዝቡ ፊት ቀረበ (17-27)

  • 11

    • ሳኦል አሞናውያንን ድል መታ (1-11)

    • የሳኦል ንግሥና በድጋሚ ጸና (12-15)

  • 12

    • የሳሙኤል የመሰነባበቻ ንግግር (1-25)

      • ‘ከንቱ ነገሮችን አትከተሉ’ (21)

      • ይሖዋ ሕዝቡን አይተውም (22)

  • 13

    • ሳኦል ወታደሮችን መረጠ (1-4)

    • ሳኦል የትዕቢት እርምጃ ወሰደ (5-9)

    • ሳሙኤል ሳኦልን ገሠጸው (10-14)

    • እስራኤላውያን ያለ ጦር መሣሪያ ተዋጉ (15-23)

  • 14

    • ዮናታን በሚክማሽ ጀብዱ ፈጸመ (1-14)

    • አምላክ በእስራኤላውያን ጠላቶች ላይ ሽብር ለቀቀባቸው (15-23)

    • ሳኦል ሕዝቡ ምግብ እንዳይቀምስ አስማለ (24-46)

      • ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በላ (32-34)

    • ሳኦል ያካሄዳቸው ጦርነቶች፤ የሳኦል ቤተሰብ (47-52)

  • 15

    • ሳኦል አጋግን ባለመግደሉ የታዘዘውን ሳይፈጽም ቀረ (1-9)

    • ሳሙኤል ሳኦልን ገሠጸው (10-23)

      • ‘መታዘዝ ከመሥዋዕት ይበልጣል’ (22)

    • የሳኦል ንግሥና በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት አጣ (24-29)

    • ሳሙኤል አጋግን ገደለው (30-35)

  • 16

    • ሳሙኤል ዳዊትን ንጉሥ እንዲሆን ቀባው (1-13)

      • ‘ይሖዋ የሚያየው ልብን ነው’ (7)

    • የአምላክ መንፈስ ከሳኦል ተወሰደ (14-17)

    • ዳዊት ለሳኦል በገና ይጫወትለት ጀመር (18-23)

  • 17

    • ዳዊት ጎልያድን አሸነፈ (1-58)

      • ጎልያድ እስራኤላውያንን ተገዳደረ (8-10)

      • ዳዊት ጎልያድን ሊገጥመው ተስማማ (32-37)

      • ዳዊት በይሖዋ ስም ተዋጋ (45-47)

  • 18

    • የዳዊትና የዮናታን ወዳጅነት (1-4)

    • ሳኦል፣ ዳዊት ባገኘው ድል ቀና (5-9)

    • ሳኦል ዳዊትን ሊገድለው ሞከረ (10-19)

    • ዳዊት የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን አገባ (20-30)

  • 19

    • ሳኦል ዳዊትን ይበልጥ ጠላው (1-13)

    • ዳዊት ከሳኦል አመለጠ (14-24)

  • 20

    • ዮናታን የዳዊት ታማኝ ወዳጅ መሆኑን አስመሠከረ (1-42)

  • 21

    • ዳዊት ከገጸ ኅብስቱ በላ (1-9)

    • ዳዊት አእምሮው እንደተነካ ሰው ሆነ (10-15)

  • 22

    • ዳዊት ወደ አዱላም፣ በኋላም ወደ ምጽጳ ሄደ (1-5)

    • ሳኦል የኖብን ካህናት አስገደለ (6-19)

    • አብያታር አመለጠ (20-23)

  • 23

    • ዳዊት የቀኢላን ከተማ ታደጋት (1-12)

    • ሳኦል ዳዊትን አሳደደው (13-15)

    • ዮናታን ዳዊትን አበረታታው (16-18)

    • ዳዊት ከሳኦል ለጥቂት አመለጠ (19-29)

  • 24

    • ዳዊት ሳኦልን ሳይገድለው ቀረ (1-22)

      • ዳዊት፣ ይሖዋ ለቀባው ንጉሥ አክብሮት እንዳለው አሳየ (6)

  • 25

    • ሳሙኤል ሞተ (1)

    • ናባል፣ ዳዊት ለላካቸው ሰዎች መጥፎ ምላሽ ሰጠ (2-13)

    • አቢጋኤል ጥበብ የተሞላበት እርምጃ ወሰደች (14-35)

      • ‘በይሖዋ ዘንድ በደንብ የታሰረ የሕይወት ከረጢት’ (29)

    • ይሖዋ ማስተዋል የጎደለውን ናባልን ቀሰፈው (36-38)

    • ዳዊት አቢጋኤልን አገባ (39-44)

  • 26

    • ዳዊት በድጋሚ ሳኦልን ሳይገድለው ቀረ (1-25)

      • ዳዊት፣ ይሖዋ ለቀባው ንጉሥ አክብሮት እንዳለው አሳየ (11)

  • 27

    • ፍልስጤማውያን ጺቅላግን ለዳዊት ሰጡት (1-12)

  • 28

    • ሳኦል በኤንዶር የምትኖር አንዲት መናፍስት ጠሪ ጠየቀ  (1-25)

  • 29

    • ፍልስጤማውያን በዳዊት ላይ ጥርጣሬ አደረባቸው (1-11)

  • 30

    • አማሌቃውያን በጺቅላግ ላይ ጥቃት ሰነዘሩ፤ በእሳትም አቃጠሏት (1-6)

      • ዳዊት በአምላኩ በይሖዋ ራሱን አበረታ (6)

    • ዳዊት አማሌቃውያንን ድል አደረጋቸው (7-31)

      • ዳዊት ምርኮኞቹን አስመለሰ (18, 19)

      • ዳዊት ምርኮ መከፋፈልን በተመለከተ ያወጣው ደንብ (23, 24)

  • 31

    • ሳኦልና ሦስት ወንዶች ልጆቹ ሞቱ (1-13)