በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘፍጥረት መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ሰማያትና ምድር ተፈጠሩ (1, 2)

    • ምድር የተሰናዳችባቸው ስድስት ቀናት (3-31)

      • የመጀመሪያ ቀን፦ ብርሃን፤ ቀንና ሌሊት (3-5)

      • ሁለተኛ ቀን፦ ጠፈር (6-8)

      • ሦስተኛ ቀን፦ የብስና ተክሎች (9-13)

      • አራተኛ ቀን፦ በሰማያት ላይ ያሉ ብርሃን ሰጪ አካላት (14-19)

      • አምስተኛ ቀን፦ ዓሣዎችና ወፎች (20-23)

      • ስድስተኛ ቀን፦ በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሳትና ሰዎች (24-31)

  • 2

    • በሰባተኛው ቀን አምላክ ከሥራው አረፈ (1-3)

    • የሰማይና የምድር ፈጣሪ የሆነው ይሖዋ አምላክ (4)

    • የመጀመሪያዎቹ ወንድና ሴት በኤደን ገነት (5-25)

      • ሰው ከአፈር ተሠራ (7)

      • የተከለከለው የእውቀት ዛፍ (15-17)

      • ሴት ከአዳም ተፈጠረች (18-25)

  • 3

    • ሰው ኃጢአት ውስጥ የወደቀበት ሁኔታ (1-13)

      • የመጀመሪያው ውሸት (4, 5)

    • ይሖዋ በዓመፀኞቹ ላይ ያስተላለፈው ፍርድ (14-24)

      • ስለ ሴቲቱ ዘር የተነገረ ትንቢት (15)

      • ከኤደን ገነት ተባረሩ (23, 24)

  • 4

    • ቃየንና አቤል (1-16)

    • የቃየን ዘሮች (17-24)

    • ሴትና ልጁ ሄኖስ (25, 26)

  • 5

    • ከአዳም እስከ ኖኅ (1-32)

      • አዳም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ (4)

      • ሄኖክ ከአምላክ ጋር ሄደ (21-24)

  • 6

    • የአምላክ ልጆች የሰዎችን ሴቶች ልጆች አገቡ (1-3)

    • ኔፍሊሞች ተወለዱ (4)

    • ይሖዋ በሰው ልጆች ክፋት አዘነ (5-8)

    • ኖኅ መርከብ እንዲሠራ ተልእኮ ተሰጠው (9-16)

    • አምላክ የጥፋት ውኃ እንደሚመጣ ተናገረ (17-22)

  • 7

    • ወደ መርከቡ ገቡ (1-10)

    • ምድር አቀፍ የጥፋት ውኃ (11-24)

  • 8

    • የጥፋት ውኃው ከምድር ላይ እየቀነሰ ሄደ (1-14)

      • ኖኅ ርግብ ላከ (8-12)

    • ከመርከቡ ወጡ (15-19)

    • አምላክ ምድርን በተመለከተ የገባው ቃል (20-22)

  • 9

    • ለመላው የሰው ዘር የተሰጠ መመሪያ (1-7)

      • ስለ ደም የተሰጠ ሕግ (4-6)

    • የቀስተ ደመና ቃል ኪዳን (8-17)

    • ስለ ኖኅ ዘሮች የተነገሩ ትንቢቶች (18-29)

  • 10

    • የብሔራት ስም ዝርዝር (1-32)

      • የያፌት ዘሮች (2-5)

      • የካም ዘሮች (6-20)

        • ናምሩድ ይሖዋን ተቃወመ (8-12)

      • የሴም ዘሮች (21-31)

  • 11

    • የባቤል ግንብ (1-4)

    • ይሖዋ ቋንቋቸውን ዘበራረቀ (5-9)

    • ከሴም እስከ አብራም (10-32)

      • የታራ ቤተሰብ (27)

      • አብራም ዑርን ለቆ ወጣ (31)

  • 12

    • አብራም ከካራን ወደ ከነአን ሄደ (1-9)

      • አምላክ ለአብራም የሰጠው ተስፋ (7)

    • አብራምና ሦራ በግብፅ (10-20)

  • 13

    • አብራም ወደ ከነአን ተመለሰ (1-4)

    • አብራምና ሎጥ ተለያዩ (5-13)

    • አምላክ ለአብራም በድጋሚ ተስፋ ሰጠው (14-18)

  • 14

    • አብራም ሎጥን ታደገው (1-16)

    • መልከጼዴቅ አብራምን ባረከው (17-24)

  • 15

    • አምላክ ከአብራም ጋር የገባው ቃል ኪዳን (1-21)

      • ለ400 ዓመት እንደሚጨቆኑ ትንቢት ተነገረ (13)

      • አምላክ ለአብራም ዳግመኛ ቃል ገባለት (18-21)

  • 16

    • አጋርና እስማኤል (1-16)

  • 17

    • አብርሃም የብዙ ብሔራት አባት ይሆናል (1-8)

      • አብራም፣ አብርሃም ተባለ (5)

    • የግርዘት ቃል ኪዳን (9-14)

    • ሦራ፣ ሣራ ተባለች (15-17)

    • ይስሐቅ የሚባል ልጅ እንደሚወልድ ቃል ተገባለት (18-27)

  • 18

    • ሦስት መላእክት ወደ አብርሃም መጡ (1-8)

    • ሣራ ወንድ ልጅ እንደምትወልድ ቃል ተገባላት፤ እሷም ሳቀች (9-15)

    • አብርሃም ስለ ሰዶም ያቀረበው ጥያቄ (16-33)

  • 19

    • መላእክት ወደ ሎጥ መጡ (1-11)

    • ሎጥና ቤተሰቡ ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ ተነገራቸው (12-22)

    • ሰዶምና ገሞራ ጠፉ (23-29)

      • የሎጥ ሚስት የጨው ዓምድ ሆነች (26)

    • ሎጥና ሴቶች ልጆቹ (30-38)

      • የሞዓባውያንና የአሞናውያን መገኛ (37, 38)

  • 20

    • አቢሜሌክ ሣራን ለአብርሃም መለሰለት (1-18)

  • 21

    • ይስሐቅ ተወለደ (1-7)

    • እስማኤል በይስሐቅ ላይ አፌዘበት (8, 9)

    • አጋርና እስማኤል ተባረሩ (10-21)

    • አብርሃም ከአቢሜሌክ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (22-34)

  • 22

    • አብርሃም ይስሐቅን መሥዋዕት እንዲያደርግ ተጠየቀ (1-19)

      • በአብርሃም ዘር አማካኝነት የሚገኝ በረከት (15-18)

    • የርብቃ ቤተሰብ (20-24)

  • 23

    • ሣራ ሞታ ተቀበረች (1-20)

  • 24

    • ለይስሐቅ ሚስት መፈለግ (1-58)

    • ርብቃ ወደ ይስሐቅ ሄደች (59-67)

  • 25

    • አብርሃም በድጋሚ አገባ (1-6)

    • አብርሃም ሞተ (7-11)

    • የእስማኤል ወንዶች ልጆች (12-18)

    • ያዕቆብና ኤሳው ተወለዱ (19-26)

    • ኤሳው የብኩርና መብቱን ሸጠ (27-34)

  • 26

    • ይስሐቅና ርብቃ በጌራራ ኖሩ (1-11)

      • አምላክ የሰጠውን ተስፋ በድጋሚ ለይስሐቅ አረጋገጠለት (3-5)

    • በውኃ ጉድጓዶች የተነሳ የተፈጠረ ግጭት (12-25)

    • ይስሐቅ ከአቢሜሌክ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (26-33)

    • ሁለቱ የኤሳው ሂታውያን ሚስቶች (34, 35)

  • 27

    • ይስሐቅ ያዕቆብን ባረከው (1-29)

    • ኤሳው መባረክ ቢፈልግም በድርጊቱ አልተጸጸተም (30-40)

    • ኤሳው ያዕቆብን ጠላው (41-46)

  • 28

    • ይስሐቅ ያዕቆብን ወደ ጳዳንአራም ላከው (1-9)

    • ያዕቆብ በቤቴል ያለመው ሕልም (10-22)

      • አምላክ የሰጠውን ተስፋ በድጋሚ ለያዕቆብ አረጋገጠለት (13-15)

  • 29

    • ያዕቆብ ከራሔል ጋር ተገናኘ (1-14)

    • ያዕቆብ ራሔልን ወደዳት (15-20)

    • ያዕቆብ ሊያንና ራሔልን አገባ (21-29)

    • ያዕቆብ ከሊያ የወለዳቸው አራት ወንዶች ልጆች፦ ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊና ይሁዳ (30-35)

  • 30

    • ባላ ዳንንና ንፍታሌምን ወለደች (1-8)

    • ዚልጳ ጋድንና አሴርን ወለደች (9-13)

    • ሊያ ይሳኮርንና ዛብሎንን ወለደች (14-21)

    • ራሔል ዮሴፍን ወለደች (22-24)

    • የያዕቆብ መንጋ እየበዛ ሄደ (25-43)

  • 31

    • ያዕቆብ በድብቅ ወደ ከነአን ኮበለለ (1-18)

    • ላባ ያዕቆብን ተከታትሎ ደረሰበት (19-35)

    • ያዕቆብ ከላባ ጋር የገባው ቃል ኪዳን (36-55)

  • 32

    • መላእክት ያዕቆብን አገኙት (1, 2)

    • ያዕቆብ ከኤሳው ጋር ለመገናኘት ተዘጋጀ (3-23)

    • ያዕቆብ ከአንድ መልአክ ጋር ታገለ (24-32)

      • ያዕቆብ፣ እስራኤል ተባለ (28)

  • 33

    • ያዕቆብ ከኤሳው ጋር ተገናኘ (1-16)

    • ያዕቆብ ወደ ሴኬም ተጓዘ (17-20)

  • 34

    • ዲና ተደፈረች (1-12)

    • የያዕቆብ ወንዶች ልጆች የተንኮል ድርጊት ፈጸሙ (13-31)

  • 35

    • ያዕቆብ ባዕዳን አማልክትን አስወገደ (1-4)

    • ያዕቆብ ወደ ቤቴል ተመለሰ (5-15)

    • ቢንያም ተወለደ፤ ራሔል ሞተች (16-20)

    • የእስራኤል 12 ወንዶች ልጆች (21-26)

    • ይስሐቅ ሞተ (27-29)

  • 36

    • የኤሳው ዘሮች (1-30)

    • የኤዶም ነገሥታትና አለቆች (31-43)

  • 37

    • የዮሴፍ ሕልሞች (1-11)

    • ዮሴፍና ቅናት ያደረባቸው ወንድሞቹ (12-24)

    • ዮሴፍ ለባርነት ተሸጠ (25-36)

  • 38

    • ይሁዳና ትዕማር (1-30)

  • 39

    • ዮሴፍ በጶጢፋር ቤት (1-6)

    • ዮሴፍ ከጶጢፋር ሚስት ሸሸ (7-20)

    • ዮሴፍ እስር ቤት ተጣለ (21-23)

  • 40

    • ዮሴፍ የእስረኞቹን ሕልም ፈታላቸው (1-19)

      • “ሕልምን የሚፈታው አምላክ አይደለም?” (8)

    • የፈርዖን የልደት በዓል (20-23)

  • 41

    • ዮሴፍ የፈርዖንን ሕልሞች ፈታለት (1-36)

    • ፈርዖን ዮሴፍን ከፍ ከፍ አደረገው (37-46ሀ)

    • ዮሴፍ እህል እንዲያከፋፍል ተሾመ (46ለ-57)

  • 42

    • የዮሴፍ ወንድሞች ወደ ግብፅ ሄዱ (1-4)

    • ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ፤ እንዲሁም ፈተናቸው (5-25)

    • የዮሴፍ ወንድሞች ወደ አባታቸው ወደ ያዕቆብ ተመለሱ (26-38)

  • 43

    • የዮሴፍ ወንድሞች ቢንያምን ይዘው ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ግብፅ ሄዱ (1-14)

    • ዮሴፍ በድጋሚ ከወንድሞቹ ጋር ተገናኘ (15-23)

    • ዮሴፍ ከወንድሞቹ ጋር በማዕድ ተቀመጠ (24-34)

  • 44

    • የዮሴፍ የብር ጽዋ በቢንያም ከረጢት ውስጥ ተገኘ (1-17)

    • ይሁዳ ስለ ቢንያም ተማጸነ (18-34)

  • 45

    • ዮሴፍ ለወንድሞቹ ማንነቱን ገለጠላቸው (1-15)

    • የዮሴፍ ወንድሞች ያዕቆብን ይዘው ለመምጣት ሄዱ (16-28)

  • 46

    • ያዕቆብና ቤተሰቡ ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7)

    • ወደ ግብፅ የሄዱት ሰዎች ስም ዝርዝር (8-27)

    • ዮሴፍ በጎሸን ከያዕቆብ ጋር ተገናኘ (28-34)

  • 47

    • ያዕቆብ ከፈርዖን ጋር ተገናኘ (1-12)

    • የዮሴፍ ጥበብ የተሞላበት አስተዳደር (13-26)

    • እስራኤል በጎሸን መኖር ጀመረ (27-31)

  • 48

    • ያዕቆብ የዮሴፍን ሁለት ወንዶች ልጆች ባረካቸው (1-12)

    • ኤፍሬም የበለጠ በረከት አገኘ (13-22)

  • 49

    • ያዕቆብ ሊሞት በተቃረበበት ጊዜ የተናገረው ትንቢት (1-28)

      • ሴሎ ከይሁዳ ይወጣል (10)

    • ያዕቆብ ስለሚቀበርበት ሁኔታ የሰጠው ትእዛዝ (29-32)

    • ያዕቆብ ሞተ (33)

  • 50

    • ዮሴፍ ያዕቆብን በከነአን ቀበረው (1-14)

    • ዮሴፍ ወንድሞቹን ይቅር እንዳላቸው በድጋሚ አረጋገጠላቸው (15-21)

    • ዮሴፍ የሚሞትበት ጊዜ ቀረበ (22-26)

      • ዮሴፍ አፅሙን አስመልክቶ የሰጠው ትእዛዝ (25)