በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘኁልቁ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • በሠራዊቱ ውስጥ እንዲያገለግሉ የተመዘገቡት ወንዶች (1-46)

    • ሌዋውያን ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ ናቸው (47-51)

    • እስራኤላውያን በየምድባቸው በሥርዓት ይሰፍራሉ (52-54)

  • 2

    • ሦስት ነገዶችን ባቀፈ ምድብ ተከፋፍለው ይሰፍራሉ (1-34)

      • የይሁዳ ምድብ በስተ ምሥራቅ ይሰፍራል (3-9)

      • የሮቤል ምድብ በስተ ደቡብ ይሰፍራል (10-16)

      • ሌዊ መሃል ላይ ይሰፍራል (17)

      • የኤፍሬም ምድብ በስተ ምዕራብ ይሰፍራል (18-24)

      • የዳን ምድብ በስተ ሰሜን ይሰፍራል (25-31)

      • የተመዘገቡት ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር (32-34)

  • 3

    • የአሮን ወንዶች ልጆች (1-4)

    • ሌዋውያን እንዲያገለግሉ ተመረጡ (5-39)

    • በኩሮቹን መዋጀት (40-51)

  • 4

    • ቀአታውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (1-20)

    • ጌድሶናውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (21-28)

    • ሜራራውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት (29-33)

    • የቆጠራው ውጤት (34-49)

  • 5

    • የረከሱ ሰዎች ተገልለው እንዲቆዩ ማድረግ (1-4)

    • ኃጢአትን መናዘዝና ካሳ መክፈል (5-10)

    • በዝሙት የተጠረጠረችን ሚስት እርግማን በሚያመጣው ውኃ መፈተን (11-31)

  • 6

    • የናዝራዊነት ስእለት (1-21)

    • ካህናት የሚባርኩበት መንገድ (22-27)

  • 7

    • የማደሪያ ድንኳኑ ሲመረቅ የቀረቡ መባዎች (1-89)

  • 8

    • አሮን ሰባቱን መብራቶች ለኮሰ (1-4)

    • ሌዋውያኑ ነጽተው ማገልገል ጀመሩ (5-22)

    • ሌዋውያን የሚያገለግሉበት የዕድሜ ገደብ (23-26)

  • 9

    • የፋሲካን በዓል በቀኑ ማክበር ላልቻለ ሰው የተደረገ ዝግጅት (1-14)

    • በማደሪያ ድንኳኑ ላይ የታየው ደመናና እሳት (15-23)

  • 10

    • ከብር የተሠሩት መለከቶች (1-10)

    • ከሲና ተነስተው ጉዞ ጀመሩ (11-13)

    • የጉዞ ቅደም ተከተላቸው (14-28)

    • ሆባብ እስራኤላውያንን መንገድ እንዲያሳይ ተጠየቀ (29-34)

    • ሙሴ፣ እስራኤላውያን ድንኳናቸውን ነቀለው ሲነሱ ያቀረበው ጸሎት (35, 36)

  • 11

    • ከይሖዋ የመጣ እሳት ባጉረመረሙት ሰዎች ላይ ነደደ (1-3)

    • የምንበላው ሥጋ አጣን ብለው አለቀሱ (4-9)

    • ሙሴ የእስራኤል ሕዝብ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ተሰማው (10-15)

    • ይሖዋ መንፈሱን ለ70ዎቹ ሽማግሌዎች ሰጠ (16-25)

    • ኤልዳድና ሞዳድ፤ ኢያሱ ለሙሴ ተቆረቆረ (26-30)

    • ድርጭቶች በሰፈሩ ዙሪያ ተበተኑ፤ ሕዝቡ በመስገብገቡ ተቀጣ (31-35)

  • 12

    • ሚርያምና አሮን ሙሴን ነቀፉት (1-3)

      • ሙሴ በምድር ላይ ካሉት ሰዎች ሁሉ ይልቅ ገር ነበር (3)

    • ይሖዋ ለሙሴ ተሟገተለት (4-8)

    • ሚርያም በሥጋ ደዌ ተመታች (9-16)

  • 13

    • አሥራ ሁለቱ ሰላዮች ወደ ከነአን ተላኩ (1-24)

    • አሥሩ ሰላዮች ያመጡት መጥፎ ወሬ (25-33)

  • 14

    • ሕዝቡ ወደ ግብፅ መመለስ ፈለገ (1-10)

      • ኢያሱና ካሌብ ያመጡት መልካም ወሬ (6-9)

    • ይሖዋ ተቆጣ፤ ሙሴ ስለ ሕዝቡ ማለደ (11-19)

    • በምድረ በዳ 40 ዓመት እንዲንከራተቱ ተፈረደባቸው (20-38)

    • እስራኤላውያን በአማሌቃውያን ድል ተመቱ (39-45)

  • 15

    • መባን አስመልክቶ የተሰጠ ሕግ (1-21)

      • ለእስራኤላውያንም ሆነ አብረዋቸው ለሚኖሩ የባዕድ አገር ሰዎች አንድ ዓይነት ሕግ ተሰጠ (15, 16)

    • ባለማወቅ ለተፈጸመ ኃጢአት የሚቀርብ መባ (22-29)

    • ሆን ብሎ ኃጢአት መሥራት የሚያስከትለው ቅጣት (30, 31)

    • የሰንበትን ሕግ የጣሰው በሞት ተቀጣ (32-36)

    • እስራኤላውያን በልብሳቸው ጫፍ ላይ ዘርፍ እንዲያደርጉ ተነገራቸው (37-41)

  • 16

    • ቆሬ፣ ዳታንና አቤሮን ዓመፁ (1-19)

    • ዓመፀኞቹ ተቀጡ (20-50)

  • 17

    • የአሮን በትር አበበች (1-13)

  • 18

    • የካህናቱና የሌዋውያኑ የሥራ ድርሻ (1-7)

    • የካህናቱ ድርሻ (8-19)

      • የጨው ቃል ኪዳን (19)

    • ሌዋውያን አሥራት መቀበልና ካገኙት ላይ አሥራት መስጠት ይጠበቅባቸዋል (20-32)

  • 19

    • ቀይ ላምና የሚያነጻው ውኃ (1-22)

  • 20

    • ሚርያም በቃዴስ ሞታ ተቀበረች (1)

    • ሙሴ ከዓለቱ ውኃ አፈለቀ፤ እንዲሁም ኃጢአት ሠራ (2-13)

    • ኤዶማውያን፣ እስራኤላውያን ክልላቸውን አቋርጠው እንዳያልፉ ከለከሉ (14-21)

    • አሮን ሞተ (22-29)

  • 21

    • የአራድ ንጉሥ ድል ተመታ (1-3)

    • የመዳብ እባብ (4-9)

    • እስራኤላውያን በሞዓብ ክልል ዞረው ሄዱ (10-20)

    • አሞራዊው ንጉሥ ሲሖን ድል ተመታ (21-30)

    • አሞራዊው ንጉሥ ኦግ ድል ተመታ (31-35)

  • 22

    • ባላቅ፣ እስራኤላውያንን እንዲረግምለት በለዓምን ቀጠረ (1-21)

    • የበለዓም አህያ ተናገረች (22-41)

  • 23

    • የመጀመሪያው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-12)

    • ሁለተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (13-30)

  • 24

    • ሦስተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (1-11)

    • አራተኛው የበለዓም ምሳሌያዊ አነጋገር (12-25)

  • 25

    • እስራኤላውያን ከሞዓብ ሴቶች ጋር የፆታ ብልግና ፈጸሙ (1-5)

    • ፊንሃስ እርምጃ ወሰደ (6-18)

  • 26

    • ሁለተኛው የእስራኤላውያን የሕዝብ ቆጠራ (1-65)

  • 27

    • የሰለጰአድ ሴቶች ልጆች (1-11)

    • ኢያሱ ሙሴን እንደሚተካ ተነገረው (12-23)

  • 28

    • የተለያዩ መባዎች የሚቀርቡበት መንገድ (1-31)

      • ዘወትር የሚቀርብ መባ (1-8)

      • በየሰንበቱ የሚቀርብ መባ (9, 10)

      • በየወሩ የሚቀርብ መባ (11-15)

      • በፋሲካ በዓል የሚቀርብ መባ (16-25)

      • በሳምንታት በዓል የሚቀርብ መባ (26-31)

  • 29

    • የተለያዩ መባዎች የሚቀርቡበት መንገድ (1-40)

      • መለከት የሚነፋበት ቀን (1-6)

      • የስርየት ቀን (7-11)

      • የዳስ በዓል (12-38)

  • 30

    • አንድ ወንድ ስእለት ቢሳል (1, 2)

    • አንዲት ወጣት ወይም አንዲት ሴት ስእለት ብትሳል (3-16)

  • 31

    • በምድያም ላይ የተወሰደ የበቀል እርምጃ (1-12)

      • በለዓም ተገደለ (8)

    • የጦር ምርኮን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ (13-54)

  • 32

    • ከዮርዳኖስ በስተ ምሥራቅ ያሉ የሰፈራ መንደሮች (1-42)

  • 33

    • እስራኤላውያን በምድረ በዳ ያደረጉት ጉዞ (1-49)

    • ከነአናውያንን ድል አድርጎ ስለማባረር የተሰጠ መመሪያ (50-56)

  • 34

    • የከነአን ወሰኖች (1-15)

    • ምድሪቱን እንዲያከፋፍሉ የተመደቡት ወንዶች (16-29)

  • 35

    • ለሌዋውያን የተሰጡ ከተሞች (1-8)

    • የመማጸኛ ከተሞች (9-34)

  • 36

    • ውርስ የሚሰጣቸው ሴቶች የሚያገቡትን ሰው በተመለከተ የወጣ ሕግ (1-13)