ለኤፌሶን ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ 5:1-33

  • ጸያፍ ንግግርንና ምግባርን ማስወገድ (1-5)

  • እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ (6-14)

  • በመንፈስ ተሞሉ (15-20)

    • “ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት” (16)

  • ለባሎችና ለሚስቶች የተሰጠ ምክር (21-33)

5  ስለዚህ የተወደዳችሁ ልጆቹ በመሆን አምላክን የምትመስሉ ሁኑ፤+  ክርስቶስ እንደወደደንና*+ ጥሩ መዓዛ እንዳለው ሽታ ራሱን ስለ እኛ* መባና መሥዋዕት አድርጎ ለአምላክ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም በፍቅር መመላለሳችሁን ቀጥሉ።+  ለቅዱሳን የማይገባ ስለሆነ የፆታ ብልግናና* ማንኛውም ዓይነት ርኩሰት ወይም ስግብግብነት በመካከላችሁ ከቶ አይነሳ፤+  አሳፋሪ ምግባር፣ የማይረባ ንግግርም ሆነ ጸያፍ ቀልድ የማይገቡ ነገሮች ናቸው፤+ ከዚህ ይልቅ አምላክን የምታመሰግኑ ሁኑ።+  እንደምታውቁትና በሚገባ እንደምትገነዘቡት ሴሰኛ*+ ወይም ርኩስ ወይም ስግብግብ+ ማለትም ጣዖት አምላኪ የሆነ ማንኛውም ሰው በክርስቶስና በአምላክ መንግሥት ምንም ውርሻ የለውም።+  በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የአምላክ ቁጣ በማይታዘዙት ልጆች ላይ ስለሚመጣ ማንም በከንቱ ንግግር አያታላችሁ።  ስለዚህ ከእነዚህ ሰዎች ጋር አትተባበሩ፤  እናንተ በአንድ ወቅት ጨለማ ውስጥ ነበራችሁና፤ አሁን ግን የጌታ በመሆናችሁ+ ብርሃን ውስጥ ናችሁ።+ የብርሃን ልጆች ሆናችሁ መመላለሳችሁን ቀጥሉ፤  የብርሃን ፍሬ ሁሉንም ዓይነት ጥሩነት፣ ጽድቅና እውነት የያዘ ነውና።+ 10  በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ነገር ምን እንደሆነ ምንጊዜም መርምራችሁ አረጋግጡ፤+ 11  ፍሬ ቢስ በሆኑ የጨለማ ሥራዎች ከእነሱ ጋር መተባበራችሁን አቁሙ፤+ ይልቁንም አጋልጧቸው። 12  በድብቅ የሚፈጽሟቸው ነገሮች ለመናገር እንኳ የሚያሳፍሩ ናቸውና። 13  ደግሞም ተጋልጠው ይፋ የሚወጡት ነገሮች ሁሉ እንዲገለጡ የሚደረገው በብርሃን ነው፤ ስለዚህ የተጋለጡት ነገሮች በሙሉ ብርሃን ይሆናሉ። 14  በመሆኑም እንዲህ ተብሏል፦ “አንተ እንቅልፋም፣ ንቃ፤ ከሞትም ተነሳ፤+ ክርስቶስ በአንተ ላይ ያበራል።”+ 15  ስለዚህ የምትመላለሱት ጥበብ እንደጎደላቸው ሳይሆን እንደ ጥበበኛ ሰዎች መሆኑን ምንጊዜም በጥንቃቄ አስተውሉ፤ 16  ቀኖቹ ክፉዎች ስለሆኑ ጊዜያችሁን በተሻለ መንገድ ተጠቀሙበት።*+ 17  ከዚህ የተነሳ የይሖዋ* ፈቃድ ምን እንደሆነ አስተውሉ እንጂ የማመዛዘን ችሎታ የጎደላችሁ አትሁኑ።+ 18  በተጨማሪም መረን ለለቀቀ ሕይወት* ስለሚዳርጋችሁ በወይን ጠጅ አትስከሩ፤+ ከዚህ ይልቅ በመንፈስ መሞላታችሁን ቀጥሉ። 19  በመዝሙርና በውዳሴ እንዲሁም በመንፈሳዊ ዝማሬ እርስ በርሳችሁ* ተነጋገሩ፤ በልባችሁም ለይሖዋ* የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፤+ 20  በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም+ ስለ ሁሉም ነገር አምላካችንን እና አባታችንን ሁልጊዜ አመስግኑ።+ 21  ክርስቶስን በመፍራት አንዳችሁ ለሌላው ተገዙ።+ 22  ሚስቶች ለጌታ እንደሚገዙ ሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ፤+ 23  ምክንያቱም ክርስቶስ አካሉ ለሆነውና አዳኙ ለሆነለት ጉባኤ ራስ እንደሆነ+ ሁሉ ባልም የሚስቱ ራስ ነው።+ 24  ደግሞም ጉባኤው ለክርስቶስ እንደሚገዛ ሁሉ ሚስቶችም በሁሉም ነገር ለባሎቻቸው ይገዙ። 25  ባሎች ሆይ፣ ክርስቶስ ጉባኤውን እንደወደደና ራሱን ለጉባኤው አሳልፎ እንደሰጠ+ ሁሉ እናንተም ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ፤+ 26  እሱ ይህን ያደረገው ጉባኤውን በቃሉ አማካኝነት በውኃ አጥቦ በማንጻት ይቀድሰው ዘንድ ነው፤+ 27  ይህም ጉባኤውን ጉድፍ ወይም የቆዳ መጨማደድ ወይም እንዲህ ያሉ ጉድለቶች የማይገኙበት+ ቅዱስና እንከን የለሽ አድርጎ ውበቱን እንደጠበቀ ለራሱ ለማቅረብ ነው።+ 28  በተመሳሳይም ባሎች ሚስቶቻቸውን እንደ ገዛ አካላቸው አድርገው ሊወዷቸው ይገባል። ሚስቱን የሚወድ ሰው ራሱን ይወዳል፤ 29  የገዛ አካሉን* የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል፤ ክርስቶስም ለጉባኤው ያደረገው እንደዚሁ ነው፤ 30  ምክንያቱም እኛ የእሱ አካል ክፍሎች ነን።+ 31  “ከዚህ የተነሳ ሰው ከአባቱና ከእናቱ ይለያል፤ ከሚስቱም ጋር ይጣበቃል፤* ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ።”+ 32  ይህ ቅዱስ ሚስጥር+ ታላቅ ነው። እኔም እየተናገርኩ ያለሁት ስለ ክርስቶስና ስለ ጉባኤው ነው።+ 33  ይሁንና ከእናንተ እያንዳንዱ ራሱን እንደሚወድ ሁሉ ሚስቱንም ይውደድ፤+ በሌላ በኩል ደግሞ ሚስት ባሏን በጥልቅ ታክብር።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

“እንደወደዳችሁና” ማለትም ሊሆን ይችላል።
“ስለ እናንተ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
ወይም “ጊዜ ግዙ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ለሥርዓት አልበኝነት።”
“ከራሳችሁ ጋር” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ቃል በቃል “ሥጋውን።”
ወይም “ይኖራል።”