በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኤርምያስ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ኤርምያስ ነቢይ ሆኖ ተሾመ (1-10)

    • የአልሞንድ ዛፍ ራእይ (11, 12)

    • የተጣደው ድስት ራእይ (13-16)

    • ኤርምያስ ተልእኮውን እንዲፈጽም ማበረታቻ ተሰጠው (17-19)

  • 2

    • እስራኤል ይሖዋን ትታ ሌሎች አማልክትን ተከተለች (1-37)

      • እስራኤል በባዕድ የወይን ተክል ተመሰለች (21)

      • ልብሶቿ በደም ቆሽሸዋል (34)

  • 3

    • እስራኤል የፈጸመችው ታላቅ ክህደት (1-5)

    • እስራኤልና ይሁዳ አመነዘሩ (6-11)

    • ንስሐ እንዲገቡ የቀረበ ጥሪ (12-25)

  • 4

    • ንስሐ መግባት በረከት ያስገኛል (1-4)

    • ከሰሜን ጥፋት ይመጣል (5-18)

    • ኤርምያስ የተሰማው ሐዘን (19-31)

  • 5

    • ሕዝቡ የይሖዋን ተግሣጽ አልሰማም (1-13)

    • ጥፋት ቢደርስባቸውም ሙሉ በሙሉ አልጠፉም (14-19)

    • ይሖዋ ሕዝቡን ተጠያቂ አደረገ (20-31)

  • 6

    • ኢየሩሳሌም የምትከበብበት ጊዜ ተቃረበ (1-9)

    • የይሖዋ ቁጣ በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ (10-21)

      • ‘ሰላም ሳይኖር “ሰላም ነው!” ይላሉ’ (14)

    • ከሰሜን ምድር ጨካኝ ወራሪዎች ይመጣሉ (22-26)

    • ኤርምያስ ብረትን እንደሚፈትን ሰው ሆኖ ያገለግላል (27-30)

  • 7

    • “‘የይሖዋ ቤተ መቅደስ ነው!’ እያላችሁ በአሳሳች ቃል አትታመኑ” (1-11)

    • ቤተ መቅደሱ እንደ ሴሎ ይሆናል (12-15)

    • የሐሰት አምልኮ ተወገዘ (16-34)

      • ‘የሰማይን ንግሥት’ አመለኩ (18)

      • በሂኖም ልጆቻቸውን ሠዉ (31)

  • 8

    • ሕዝቡ ብዙኃኑ የሚከተለውን መንገድ ተከተለ (1-7)

    • የይሖዋን ቃል ንቀው ምን ዓይነት ጥበብ ሊኖራቸው ይችላል? (8-17)

    • ኤርምያስ በይሁዳ ላይ በደረሰው ውድቀት የተነሳ አዘነ (18-22)

      • “በጊልያድ የበለሳን ዘይት የለም?” (22)

  • 9

    • ኤርምያስ የተሰማው ጥልቅ ሐዘን (1-3ሀ)

    • ይሖዋ ይሁዳን ተጠያቂ አደረገ (3ለ-16)

    • ከጽዮን የተሰማ የሐዘን እንጉርጉሮ (17-22)

    • “እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ በማወቁ ይኩራራ” (23-26)

  • 10

    • የብሔራት አማልክትና ሕያው የሆነው አምላክ (1-16)

    • የሚጠፉበትና የሚማረኩበት ጊዜ ተቃረበ (17, 18)

    • ኤርምያስ እጅግ አዘነ (19-22)

    • ነቢዩ ያቀረበው ጸሎት (23-25)

      • ሰው አካሄዱን አቃንቶ መምራት አይችልም (23)

  • 11

    • ይሁዳ ከአምላክ ጋር የገባችውን ቃል ኪዳን አፈረሰች (1-17)

      • “አማልክትህ የከተሞችህን ያህል በዝተዋል” (13)

    • ኤርምያስ ለመታረድ እንደሚነዳ በግ ሆነ (18-20)

    • ኤርምያስ ከአገሩ ሰዎች ተቃውሞ ገጠመው (21-23)

  • 12

    • ኤርምያስ አቤቱታ አቀረበ (1-4)

    • ይሖዋ የሰጠው መልስ (5-17)

  • 13

    • ከተልባ እግር የተሠራው ቀበቶ ተበላሸ (1-11)

    • በወይን ጠጅ የተሞሉ እንስራዎች ይሰባበራሉ (12-14)

    • ይሁዳ ልትሻሻል ባለመቻሏ በምርኮ ትወሰዳለች (15-27)

      • ‘ኢትዮጵያዊ መልኩን መለወጥ ይችላል?’ (23)

  • 14

    • ድርቅ፣ ረሃብና ሰይፍ (1-12)

    • ሐሰተኛ ነቢያት ተወገዙ (13-18)

    • ኤርምያስ ሕዝቡ ኃጢአት መሥራቱን አምኖ ተቀበለ (19-22)

  • 15

    • ይሖዋ ፍርዱን አይለውጥም (1-9)

    • የኤርምያስ ስሞታ (10)

    • ይሖዋ የሰጠው መልስ (11-14)

    • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (15-18)

      • የአምላክን ቃል መብላት የሚያስገኘው ደስታ (16)

    • ይሖዋ ኤርምያስን አበረታታው (19-21)

  • 16

    • ኤርምያስ እንዳያገባ፣ እንዳያለቅስና ወደ ግብዣ እንዳይሄድ ተነገረው (1-9)

    • ከተቀጡ በኋላ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው ይመለሳሉ (10-21)

  • 17

    • የይሁዳ ኃጢአት በጽላት ላይ ተቀርጿል (1-4)

    • በይሖዋ መታመን የሚያስገኘው በረከት (5-8)

    • ልብ ከዳተኛ ነው (9-11)

    • የእስራኤል ተስፋ የሆነው ይሖዋ (12, 13)

    • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (14-18)

    • “የሰንበትን ቀን ቀድሱ” (19-27)

  • 18

    • በሸክላ ሠሪው እጅ ውስጥ ያለ ጭቃ (1-12)

    • ይሖዋ ለእስራኤል ጀርባውን ሰጠ (13-17)

    • በኤርምያስ ላይ የተጠነሰሰ ሴራና እሱ ያቀረበው ልመና (18-23)

  • 19

    • ኤርምያስ ገንቦውን እንዲሰብር ተነገረው (1-15)

      • ልጆቻቸውን ለባአል ሠዉ (5)

  • 20

    • ጳስኮር ኤርምያስን መታው (1-6)

    • ኤርምያስ መስበኩን ሊያቆም አልቻለም (7-13)

      • የአምላክ ቃል እንደሚነድ እሳት ነው (9)

      • ይሖዋ እንደ አስፈሪ ተዋጊ ነው (11)

    • ኤርምያስ ያሰማው እሮሮ (14-18)

  • 21

    • ይሖዋ ሴዴቅያስ ያቀረበውን ልመና አልሰማም (1-7)

    • ‘የሕይወት መንገድና የሞት መንገድ’ (8-14)

  • 22

    • በክፉ ነገሥታት ላይ የተላለፈ የፍርድ መልእክት (1-30)

      • ስለ ሻሉም የተነገረ ቃል (10-12)

      • ስለ ኢዮዓቄም የተነገረ ቃል (13-23)

      • ስለ ኮንያሁ የተነገረ ቃል (24-30)

  • 23

    • መልካምና ክፉ እረኞች (1-4)

    • ‘በጻድቁ ቀንበጥ’ ሥር ያለስጋት መኖር (5-8)

    • ሐሰተኛ ነቢያት ተወገዙ (9-32)

    • “የይሖዋ ሸክም” (33-40)

  • 24

    • ጥሩ በለሶችና መጥፎ በለሶች (1-10)

  • 25

    • “ይሖዋ ከብሔራት ጋር ሙግት አለው” (1-38)

      • ብሔራት ባቢሎንን 70 ዓመት ያገለግሏታል (11)

      • የአምላክ ቁጣ ወይን ጠጅ ያለበት ጽዋ (15)

      • “ጥፋት ብሔራትን አንድ በአንድ ያዳርሳል” (32)

      • “ይሖዋ የገደላቸው” (33)

  • 26

    • ኤርምያስን ‘እንገድልሃለን’ ብለው ዛቱበት (1-15)

    • ኤርምያስ ከሞት ተረፈ (16-19)

      • የሚክያስ ትንቢት ተጠቀሰ (18)

    • ነቢዩ ዑሪያህ (20-24)

  • 27

    • የባቢሎን ቀንበር (1-11)

    • ሴዴቅያስ ለባቢሎን እንዲገዛ ተነገረው (12-22)

  • 28

    • ኤርምያስና ሐሰተኛው ነቢይ ሃናንያህ (1-17)

  • 29

    • ኤርምያስ በግዞት ወደ ባቢሎን ለተወሰዱት ሰዎች የጻፈው ደብዳቤ (1-23)

      • እስራኤላውያን ከ70 ዓመት በኋላ ይመለሳሉ (10)

    • ለሸማያህ የተላለፈ መልእክት (24-32)

  • 30

    • ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለሱና እንደሚፈወሱ የተነገረ ቃል (1-24)

  • 31

    • የእስራኤል ቀሪዎች ዳግመኛ በምድሪቱ ላይ ይሰፍራሉ (1-30)

      • ‘ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች’ (15)

    • “አዲስ ቃል ኪዳን” (31-40)

  • 32

    • ኤርምያስ መሬት ገዛ (1-15)

    • ኤርምያስ ያቀረበው ጸሎት (16-25)

    • ይሖዋ የሰጠው መልስ (26-44)

  • 33

    • ወደ ቀድሞው ሁኔታ እንደሚመለሱ ቃል ተገባላቸው (1-13)

    • ‘በጻድቁ ቀንበጥ’ ሥር ያለስጋት መኖር (14-16)

    • ከዳዊትና ከካህናቱ ጋር የተገባ ቃል ኪዳን (17-26)

      • የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳን (20)

  • 34

    • ለሴዴቅያስ የተነገረ የፍርድ መልእክት (1-7)

    • ለባሪያዎች ነፃነት አስገኝቶ የነበረው ቃል ኪዳን ፈረሰ (8-22)

  • 35

    • ሬካባውያን የተዉት ግሩም የታዛዥነት ምሳሌ (1-19)

  • 36

    • ኤርምያስ ባሮክን በቃሉ አስጻፈው (1-7)

    • ባሮክ ከጥቅልሉ ላይ ጮክ ብሎ አነበበ (8-19)

    • ኢዮዓቄም ጥቅልሉን አቃጠለው (20-26)

    • መልእክቱ በአዲስ ጥቅልል ላይ በድጋሚ ተጻፈ (27-32)

  • 37

    • ከለዳውያን ለጊዜው ኢየሩሳሌምን ለቀው ሄዱ (1-10)

    • ኤርምያስ ታሰረ (11-16)

    • ሴዴቅያስ ከኤርምያስ ጋር ተገናኘ (17-21)

      • ኤርምያስ ዳቦ ይሰጠው ነበር (21)

  • 38

    • ኤርምያስ ጉድጓድ ውስጥ ተጣለ (1-6)

    • ኤቤድሜሌክ ኤርምያስን አዳነው (7-13)

    • ኤርምያስ፣ እጁን እንዲሰጥ ሴዴቅያስን አሳሰበው (14-28)

  • 39

    • በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ጥፋት (1-10)

      • ሴዴቅያስ ሲሸሽ ተያዘ (4-7)

    • ኤርምያስ ጥበቃ አገኘ (11-14)

    • ኤቤድሜሌክ ሕይወቱ እንደሚተርፍ ተነገረው (15-18)

  • 40

    • ናቡዛራዳን ኤርምያስን በነፃ ለቀቀው (1-6)

    • ጎዶልያስ በምድሪቱ ላይ ተሾመ (7-12)

    • በጎዶልያስ ላይ ሴራ ተጠነሰሰ (13-16)

  • 41

    • እስማኤል ጎዶልያስን ገደለው (1-10)

    • ዮሃናን እስማኤልን አሳደደው (11-18)

  • 42

    • ሕዝቡ ኤርምያስን እንዲጸልይላቸው ለመኑት (1-6)

    • ይሖዋ “ወደ ግብፅ አትሂዱ” አላቸው (7-22)

  • 43

    • ሕዝቡ አሻፈረን ብለው ወደ ግብፅ ሄዱ (1-7)

    • የይሖዋ ቃል በግብፅ ወደነበረው ወደ ኤርምያስ መጣ (8-13)

  • 44

    • በግብፅ የነበሩ አይሁዳውያን እንደሚጠፉ ተነገረ (1-14)

    • ሕዝቡ የአምላክን ማስጠንቀቂያ አቃለለ (15-30)

      • ‘የሰማይን ንግሥት’ አመለኩ (17-19)

  • 45

    • ይሖዋ ለባሮክ ያስተላለፈው መልእክት (1-5)

  • 46

    • በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-26)

      • ናቡከደነጾር ግብፅን ድል ያደርጋል (13, 26)

    • ለእስራኤል የተገባ ቃል (27, 28)

  • 47

    • በፍልስጤማውያን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7)

  • 48

    • በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-47)

  • 49

    • በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-6)

    • በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (7-22)

      • ኤዶም ሙሉ በሙሉ ትደመሰሳለች (17, 18)

    • በደማስቆ ላይ የተነገረ ትንቢት (23-27)

    • በቄዳርና በሃጾር ላይ የተነገረ ትንቢት (28-33)

    • በኤላም ላይ የተነገረ ትንቢት (34-39)

  • 50

    • በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-46)

      • ከባቢሎን ሽሹ (8)

      • እስራኤል ወደ ምድሩ ይመለሳል (17-19)

      • የባቢሎን ውኃ ይደርቃል (38)

      • ባቢሎን የሚኖርባት አይገኝም (39, 40)

  • 51

    • በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-64)

      • ባቢሎን በድንገት በሜዶናውያን እጅ ትወድቃለች (8-12)

      • መጽሐፉ ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ተወረወረ (59-64)

  • 52

    • ሴዴቅያስ በባቢሎን ላይ ዓመፀ (1-3)

    • ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን ከበበ (4-11)

    • ከተማዋና ቤተ መቅደሱ በእሳት ጋዩ (12-23)

    • ሕዝቡ በግዞት ወደ ባቢሎን ተወሰደ (24-30)

    • ዮአኪን ተፈታ (31-34)