በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የኢዮብ መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • የኢዮብ ንጹሕ አቋምና የነበረው ሀብት (1-5)

    • ሰይጣን የኢዮብን የልብ ዝንባሌ በተመለከተ ጥያቄ አነሳ (6-12)

    • ኢዮብ ንብረቱንና ልጆቹን አጣ (13-19)

    • ኢዮብ አምላክን አላማረረም (20-22)

  • 2

    • ሰይጣን የኢዮብን የልብ ዝንባሌ በተመለከተ በድጋሚ ጥያቄ አነሳ (1-5)

    • ሰይጣን ኢዮብን በቁስል እንዲመታው ተፈቀደለት (6-8)

    • የኢዮብ ሚስት “አምላክን እርገምና ሙት!” አለችው (9, 10)

    • የኢዮብ ሦስት ጓደኞች መጡ (11-13)

  • 3

    • ኢዮብ የተወለደበትን ቀን ረገመ (1-26)

      • መከራ የደረሰበት ለምን እንደሆነ ጠየቀ (20, 21)

  • 4

    • የኤሊፋዝ የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-21)

      • የኢዮብን ንጹሕ አቋም አጣጣለ (7, 8)

      • መንፈስ ሹክ ያለውን መልእክት ተናገረ (12-17)

      • ‘አምላክ በአገልጋዮቹ ላይ እምነት የለውም’ (18)

  • 5

    • ኤሊፋዝ ንግግሩን ቀጠለ (1-27)

      • ‘አምላክ ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኮል ይይዛቸዋል’ (13)

      • ‘ኢዮብ የአምላክን ተግሣጽ መናቅ አይኖርበትም’ (17)

  • 6

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-30)

      • ማማረሩ ስህተት እንዳልሆነ ገለጸ (2-6)

      • አጽናኞቹ ከዳተኞች ሆኑበት (15-18)

      • “በሐቀኝነት የተነገረ ቃል አያቆስልም!” (25)

  • 7

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-21)

      • ሕይወት እንደ ግዳጅ አገልግሎት ነው (1, 2)

      • “ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው?” (20)

  • 8

    • የበልዳዶስ የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-22)

      • የኢዮብ ልጆች ኃጢአት ሠርተው ሊሆን እንደሚችል ጠቆመ (4)

      • ‘ንጹሕ ብትሆን ኖሮ አምላክ ይጠብቅህ ነበር’ (6)

      • ኢዮብ አምላክ የለሽ እንደሆነ ጠቆመ (13)

  • 9

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-35)

      • ሟች ሰው ከአምላክ ጋር ሊሟገት አይችልም (2-4)

      • ‘‘አምላክ የማይመረመሩ ነገሮችን ያደርጋል’ (10)

      • ሰው ከአምላክ ጋር ሊከራከር አይችልም (32)

  • 10

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-22)

      • ‘አምላክ ከእኔ ጋር የሚሟገተው ለምንድን ነው?’ (2)

      • ሟች የሆነው ኢዮብ ራሱን ከአምላክ ጋር አነጻጸረ (4-12)

      • ‘ትንሽ ፋታ ላግኝ’ (20)

  • 11

    • የሶፋር የመጀመሪያ ዙር ንግግር (1-20)

      • ‘ከንቱ ንግግር ተናግረሃል’ ብሎ ኢዮብን ወቀሰው (2, 3)

      • ክፉ ነገር ከማድረግ እንዲቆጠብ ኢዮብን አሳሰበው (14)

  • 12

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-25)

      • “ከእናንተ አላንስም” (3)

      • “መሳለቂያ ሆኛለሁ” (4)

      • ‘በአምላክ ዘንድ ጥበብ አለ’ (13)

      • አምላክ ከፈራጆችና ከነገሥታት በላይ ነው (17, 18)

  • 13

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-28)

      • ‘አምላክን ባነጋግር እመርጣለሁ’ (3)

      • “ሁላችሁም የማትረቡ ሐኪሞች ናችሁ” (4)

      • “ትክክል እንደሆንኩ አውቃለሁ” (18)

      • አምላክ እንደ ጠላት የቆጠረው ለምን እንደሆነ ጠየቀ (24)

  • 14

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-22)

      • የሰው ሕይወት አጭርና በመከራ የተሞላ ነው (1)

      • “ዛፍ እንኳ ተስፋ አለው” (7)

      • “ምነው በመቃብር ውስጥ በሰወርከኝ!” (13)

      • “ሰው ከሞተ በኋላ ዳግመኛ በሕይወት ሊኖር ይችላል?” (14)

      • አምላክ የእጁን ሥራ ይናፍቃል (15)

  • 15

    • የኤሊፋዝ ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-35)

      • ኢዮብ ፈሪሃ አምላክ እንደሌለው ተናገረ (4)

      • ኢዮብ እብሪተኛ እንደሆነ ገለጸ (7-9)

      • ‘አምላክ በቅዱሳኑ ላይ እምነት የለውም’ (15)

      • ‘ሥቃይ የሚደርስበት ሰው ክፉ ነው’ (20-24)

  • 16

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-22)

      • “ሁላችሁም የምታስጨንቁ አጽናኞች ናችሁ!” (2)

      • አምላክ እሱን ዒላማ እንዳደረገው ተናገረ (12)

  • 17

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-16)

      • “ፌዘኞች ከበውኛል” (2)

      • “አምላክ የሰዎች መቀለጃ አደረገኝ” (6)

      • “መቃብር፣ ቤቴ ይሆናል” (13)

  • 18

    • የበልዳዶስ ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-21)

      • የኃጢአተኞችን ዕጣ ፋንታ ገለጸ (5-20)

      • ኢዮብ አምላክን እንደማያውቅ ጠቆመ (21)

  • 19

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-29)

      • “የጓደኞቹን” ተግሣጽ ተቃወመ (1-6)

      • ሰዎች እንደራቁት ተናገረ (13-19)

      • ‘የሚዋጀኝ ሕያው ነው’ (25)

  • 20

    • የሶፋር ሁለተኛ ዙር ንግግር (1-29)

      • ኢዮብ እንደዘለፈው ተሰማው (2, 3)

      • ኢዮብ ክፉ እንደሆነ የሚጠቁም ቃል ተናገረ (5)

      • ኢዮብ በኃጢአት እንደሚደሰት ተናገረ (12, 13)

  • 21

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-34)

      • ‘ክፉዎች የሚሳካላቸው ለምንድን ነው?’ (7-13)

      • “የአጽናኞቹን” ክፋት አጋለጠ (27-34)

  • 22

    • የኤሊፋዝ ሦስተኛ ዙር ንግግር (1-30)

      • “ሰው አምላክን ሊጠቅመው ይችላል?” (2, 3)

      • ኢዮብን በስግብግብነትና ፍትሕ በማዛባት ወነጀለው (6-9)

      • ‘ወደ አምላክ ብትመለስ ትታደሳለህ’ (23)

  • 23

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-17)

      • ጉዳዩን በአምላክ ፊት ማቅረብ ፈለገ (1-7)

      • አምላክን ማግኘት እንደማይችል ተናገረ (8, 9)

      • “ምንም ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ” (11)

  • 24

    • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-25)

      • “አምላክ ለምን ጊዜ አልወሰነም?” (1)

      • አምላክ ክፋትን እንደሚፈቅድ ተናገረ (12)

      • ኃጢአተኞች ጨለማን ይወዳሉ (13-17)

  • 25

    • የበልዳዶስ ሦስተኛ ዙር ንግግር (1-6)

      • ‘‘ሰው በአምላክ ፊት እንዴት ንጹሕ ሊሆን ይችላል?’ (4)

      • ሰው ንጹሕ አቋሙን ቢጠብቅ ዋጋ እንደሌለው ተናገረ (5, 6)

  • 26

    • ኢዮብ የሰጠው መልስ (1-14)

      • “ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!” (1-4)

      • ‘አምላክ ምድርን ያለምንም ነገር አንጠልጥሏል’ (7)

      • ‘የአምላክ መንገድ ዳር ዳር ናቸው’ (14)

  • 27

    • ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን ለመጠበቅ ወሰነ (1-23)

      • “ንጹሕ አቋሜን አላጎድፍም!” (5)

      • አምላክ የለሽ ሰው ተስፋ የለውም (8)

      • “ንግግራችሁ ጨርሶ ባዶ የሆነው ለምንድን ነው?” (12)

      • ክፉዎች ባዷቸውን ይቀራሉ (13-23)

  • 28

    • ኢዮብ የምድርን ውድ ሀብት ከጥበብ ጋር አነጻጸረ (1-28)

      • ሰው ማዕድን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት (1-11)

      • ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለች (18)

      • ይሖዋን መፍራት እውነተኛ ጥበብ ነው (28)

  • 29

    • ኢዮብ መልካሙን ዘመን አስታወሰ (1-25)

      • በከተማዋ በር ላይ የተከበረ ሰው ነበር (7-10)

      • የተከተለው የፍትሕ ጎዳና (11-17)

      • ሰው ሁሉ ምክሩን ይሰማ ነበር (21-23)

  • 30

    • ኢዮብ የደረሰበትን ሁኔታ ገለጸ (1-31)

      • የማይረቡ ሰዎች አፌዙበት (1-15)

      • አምላክ ምንም እየረዳው እንዳልሆነ ተሰምቶት ነበር (20, 21)

      • ‘ቆዳዬ ጠቆረ’ (30)

  • 31

    • ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን እንዳላጎደፈ በመግለጽ ተሟገተ (1-40)

      • “ከዓይኔ ጋር ቃል ኪዳን ገብቻለሁ” (1)

      • አምላክ እንዲመዝነው ጠየቀ (6)

      • አመንዝራ አልነበረም (9-12)

      • የገንዘብ ፍቅር አልነበረውም (24, 25)

      • ጣዖት አምላኪ አልነበረም (26-28)

  • 32

    • ወጣቱ ኤሊሁ በውይይቱ መሳተፍ ጀመረ (1-22)

      • በኢዮብና በኢዮብ ጓደኞች ላይ ተቆጣ (2, 3)

      • በአክብሮት ዝም ብሎ ቆየ (6, 7)

      • “ዕድሜ በራሱ ሰውን ጥበበኛ አያደርገውም” (9)

      • ኤሊሁ ለመናገር ተነሳሳ (18-20)

  • 33

    • ኤሊሁ፣ ኢዮብ ራሱን በማመጻደቁ ወቀሰው (1-33)

      • “ቤዛ አግኝቻለሁ!” (24)

      • ወደ ወጣትነቱ ዘመን ይመለስ (25)

  • 34

    • ኤሊሁ፣ የአምላክ ፍትሕና መንገድ ትክክል መሆኑን ገለጸ (1-37)

      • ኢዮብ፣ አምላክ ፍትሕ እንደነፈገው ተናግሯል (5)

      • እውነተኛው አምላክ ክፋት አይሠራም (10)

      • ኢዮብ እውቀት ይጎድለዋል (35)

  • 35

    • ኤሊሁ፣ ኢዮብ ያቀረበው ሐሳብ የተሳሳተ መሆኑን ጠቆመ (1-16)

      • ኢዮብ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ እንደሆነ ተናግሯል (2)

      • አምላክ እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ሰው የሚሠራው ኃጢአት ሊጎዳው አይችልም (5, 6)

      • ኢዮብ አምላክን መጠባበቅ አለበት (14)

  • 36

    • ኤሊሁ የአምላክን ታላቅነት ከፍ ከፍ አደረገ (1-33)

      • ታዛዦች ይበለጽጋሉ፤ አምላክ የለሾች ግን ተቀባይነት አያገኙም (11-13)

      • ‘እንደ አምላክ ያለ አስተማሪ ማን ነው?’ (22)

      • ኢዮብ አምላክን ከፍ ከፍ ማድረግ ይጠበቅበታል (24)

      • “አምላክ እኛ ልናውቀው ከምንችለው በላይ ታላቅ ነው” (26)

      • አምላክ ዝናብንና መብረቅን ይቆጣጠራል (27-33)

  • 37

    • የተፈጥሮ ኃይሎች የአምላክን ታላቅነት ይገልጣሉ (1-24)

      • አምላክ የሰውን ሥራ መግታት ይችላል (7)

      • “የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በጥሞና አስብ” (14)

      • “አምላክ ከመረዳት ችሎታችን በላይ ነው” (23)

      • ማንም ሰው ጥበበኛ ነኝ ብሎ አያስብ (24)

  • 38

    • ይሖዋ፣ ሰው አነስተኛ ፍጡር መሆኑን ገለጸ (1-41)

      • ‘ምድር ስትፈጠር አንተ የት ነበርክ?’ (4-6)

      • የአምላክ ልጆች በደስታ እልል አሉ (7)

      • የተፈጥሮ ክስተቶችን በተመለከተ የቀረቡ ጥያቄዎች (8-32)

      • ‘ሰማያት የሚመሩባቸው ሕጎች’ (33)

  • 39

    • እንስሳት የሰውን አላዋቂነት ያሳያሉ (1-30)

      • የተራራ ፍየሎችና ርኤሞች (1-4)

      • የዱር አህያ (5-8)

      • የዱር በሬ (9-12)

      • ሰጎን (13-18)

      • ፈረስ (19-25)

      • ሲላ እና ንስር (26-30)

  • 40

    • ይሖዋ ያቀረባቸው ተጨማሪ ጥያቄዎች (1-24)

      • ኢዮብ መልስ እንደሌለው አምኖ ተቀበለ (3-5)

      • “የእኔን ፍትሕ ትጠራጠራለህ?” (8)

      • አምላክ የብሄሞትን ጉልበት ገለጸ (15-24)

  • 41

    • አምላክ የሌዋታንን አስደናቂ አፈጣጠር ገለጸ (1-34)

  • 42

    • ኢዮብ ለይሖዋ የሰጠው መልስ (1-6)

    • ሦስቱ የኢዮብ ጓደኞች ተወገዙ (7-9)

    • ይሖዋ ኢዮብን መልሶ ባረከው (10-17)

      • የኢዮብ ወንዶችና ሴቶች ልጆች (13-15)