በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት መናገር

የይሖዋ ምሥክሮች የአምላክን ቃል እና በውስጡ የሚገኘውን እውነት በተቻለ መጠን ለብዙ ሰዎች ለመናገር በሚያደርጉት ጥረት ያገኟቸውን ተሞክሮዎች እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት የሚያገለግል የሕዝብ ስልክ

ዳያኒ ኤሌክትሪክም ሆነ ኢንተርኔት በሌለበት ርቆ የሚገኝ መንደር በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ማስጀመር የቻለችው እንዴት ነው?

በውጤቱ በጣም ተደነቀች

ዴሲካር የተባለች በቬኔዙዌላ የምትኖር አንዲት ነጠላ ወላጅ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አዲስ የአገልግሎት ዘዴ ተጠቅማ ውጤታማ መሆን የቻለችው እንዴት ነው?

ለደብዳቤዎቿ አድናቆታቸውን ገልጸዋል

ደብዳቤ በመጻፍ መስበክ የትኞቹን ጥሩ ውጤቶች ያስገኛል?

“ስልካችሁን ስጠብቅ ነበር”

አንድ ባልና ሚስት ራሳቸውን አደፋፍረው በስልክ ምሥክርነት በመካፈላቸው ምን በረከት አግኝተዋል?

ውጥረት ውስጥ ላሉ የሆስፒታል ሠራተኞች የተሰጠ እርዳታ

በአንድ ሆስፒታል ያሉ ነርሶችና ሌሎች ሠራተኞች በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አበረታች ሐሳብ ያገኙት እንዴት ነው?

በወረርሽኙ ወቅት መስበካቸውን ቀጥለዋል

ወንድሞችና እህቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የሚያጽናና መልእክት ለሰዎች በሚሰብኩበት መንገድ ላይ ማስተካከያ በማድረግ ደስታቸውንና አዎንታዊ አመለካከታቸውን ይዘው መቀጠል ችለዋል።

ለውሾቼ የሚበላ ነገር ሰጧቸው

የጽሑፍ ጋሪ ይዘው የቆሙ የይሖዋ ምሥክር ባልና ሚስት፣ በዚያ ለሚያልፍ አንድ ሰው ብቻ ሳይሆን ለውሾቹም ደግነት ያሳዩ ነበር። ታዲያ ይህ ምን ውጤት አስገኘ?

ጎርፉ ምሥራች አመጣ

በኒካራጓ የሚገኙ መንደሮች ከባድ ዝናብ ከጣለ በኋላ ካልተጠበቀ ምንጭ እርዳታ አገኙ።

ዓይነ ስውር የሆነች ሴት ያቀረበችው ጸሎት መልስ አገኘ

ሚንግጂየ እውነተኛ ክርስቲያኖችን ለማግኘት ጸልያ ነበር። ጸሎቷ ምላሽ እንዳገኘ የተሰማት ለምንድን ነው?

ለአንድ ሰው የተጀመረው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለብዙዎች ተረፈ

በጓቴማላ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች የኬክቺ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆኑ በርካታ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ማስተማር ችለዋል።

ቄሱ ለጥያቄዎቹ መልስ አገኘ

አንድ ቄስና ባለቤቱ ልጃቸውን በሞት በማጣታቸው ምክንያት አምርረው እያለቀሱ ነበር። በኋላ ግን ሞትን በተመለከተ ለነበሯቸው ጥያቄዎች የሚያረካ መልስ አገኙ።

ፓስተሩ እሱ መስሏቸው ነበር

ቺሊ ውስጥ አንድ የይሖዋ ምሥክር ምሥራቹን ለመስበክና አምላክ ሰዎች እንዲሞቱ ዓላማው እንዳልነበር ለማስረዳት የሚያስችል ለየት ያለ አጋጣሚ አገኘ።

የማሮኒ ወንዝን ተከትሎ የተካሄደ ዘመቻ

አሥራ ሦስት የይሖዋ ምሥክሮች ተስፋ ሰጪ የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት በአማዞን ደን ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ለማካፈል ዘመቻ አካሄዱ።

በፖሊሶች ታጅቦ መስበክ

የይሖዋ ምሥክሮች በአንዲት ትንሽ ደሴት ላይ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ሲሰብኩ ፖሊሶች የረዷቸው እንዴት ነው?

መኪናቸውን አቁመው እርዳታ አበረከቱ

አምስት ወጣቶች በረዶውንና ብርዱን ተቋቁመው አንድን ሰው የረዱት ለምንድን ነው?

ሐቀኝነት የሚያስገኘው ውጤት

በደቡብ አፍሪካ የምትኖር አንዲት እህት በካፌ ውስጥ ያገኘችውን የተረሳ ቦርሳ ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት ያደረገችው ለምን እንደሆነ አንብብ።

“ይሖዋን ለማገልገል አቅሜ የፈቀደውን ሁሉ አደርጋለሁ”

ኢርማ ዕድሜያቸው ወደ 90 ዓመት ቢጠጋም ስለ መጽሐፍ ቅዱስ በሚገልጹ ደብዳቤዎቻቸው አማካኝነት የብዙዎችን ልብ መንካት ችለዋል።

እንደምትወጂያቸው ንገሪያቸው

መጽሐፍ ቅዱስ የአንድ ቤተሰብ አባላት ፍቅርና ደስታ የሰፈነበት ሕይወት እንዲመሩ የረዳቸው እንዴት ነው?

“አዲስና ደስ የሚል አቀራረብ ነው!”

jw.org በተባለው ድረ ገጽ ላይ የሚገኙ ቪዲዮዎች የመምህራንንና የተማሪ አማካሪዎችን ጨምሮ የብዙ ሰዎችን ቀልብ እየሳቡ ነው።

ክርስቲያናዊ ደግነት ያስገኘው ውጤት

አንዲት ክርስቲያን ያሳየችው ደግነት ተቃዋሚ የነበረን አንድ ሰው የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ለመማር ያነሳሳው እንዴት ነው?

ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጥ!

አንድ ሰው እውነትን አይቀበልም ብላችሁ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ። ከጊዜ በኋላ እውነትን የተቀበሉ ሰዎችን ተሞክሮ እንድታነብ እንጋብዝሃለን። እነዚህ ሰዎች እውነትን ሊቀበሉ የቻሉት ለምን እንደሆነ ተመልከት።

ሁልዳ ግቧ ላይ ደረሰች

ሁልዳ ለአገልግሎትና ለክርስቲያናዊ ስብሰባዎች የሚረዳት ታብሌት መግዛት የቻለችው እንዴት ነው?

የታሰበበት ዘመቻ ያስገኘው ውጤት

በቺሊ የምትኖር አንዲት የአሥር ዓመት ልጅ በትምህርት ቤቷ የሚገኙ የማፑዱንጉን ቋንቋ ተናጋሪዎችን በአንድ ልዩ ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኙ ለመጋበዝ ስትል ያከናወነችውን ትጋት የተሞላበት ተግባር ለማወቅ ይህን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ከሰዎች ውጫዊ ገጽታ ባሻገር ለመመልከት ትሞክራላችሁ?

አንድ የይሖዋ ምሥክር ፈጽሞ ሰው እንዲቀርበው የማይፈልግን አስቸጋሪ የሆነ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በትዕግሥት ማናገሩ ምን ውጤት አስገኘ?