በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል? ሳይበርሴክስ ስህተት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላል? ሳይበርሴክስ ስህተት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፖርኖግራፊ፣ ስለ ሳይበርሴክስ ወይም እነዚህን ስለመሳሰሉ ሌሎች ድርጊቶች በቀጥታ አይናገርም። ይሁን እንጂ ከጋብቻ ውጪ የፆታ ግንኙነት እንድንፈጽም ወይም ስለ ወሲብ የተዛባ አመለካከት እንድንይዝ ለሚገፋፉ ነገሮች አምላክ ምን ዓይነት አመለካከት እንዳለው በግልጽ ይናገራል። እስቲ የሚከተሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እንመልከት፦

  •   “በምድራዊ የአካል ክፍሎቻችሁ ውስጥ ያሉትን ዝንባሌዎች ግደሉ፤ እነሱም ዝሙት፣ ርኩሰት፣ የፆታ ምኞት፣ . . . ናቸው።” (ቆላስይስ 3:5) ፖርኖግራፊ መመልከት መጥፎ ፍላጎቶችን ከመግደል ይልቅ ያቀጣጥላቸዋል። ይህም አንድን ሰው በአምላክ ፊት ርኩስ ወይም ቆሻሻ ያደርገዋል።

  •   “የፆታ ስሜቱ እስኪቀሰቀስ ድረስ አንዲትን ሴት በምኞት የሚመለከት ሁሉ በዚያን ጊዜ በልቡ ከእሷ ጋር አመንዝሯል።” (ማቴዎስ 5:28) ወሲባዊ ምስሎች መጥፎ ነገር እንድናውጠነጥን የሚያደርጉን ሲሆን ይህ ደግሞ ወደ መጥፎ ድርጊት ያመራል።

  •   “ዝሙትና ማንኛውም ዓይነት ርኩሰት ወይም ስግብግብነት በመካከላችሁ ከቶ አይነሳ።” (ኤፌሶን 5:3) ብልግናን በቀልድ መልክ ማንሳት እንኳ ተገቢ ካልሆነ የብልግና ድርጊት ሲፈጸም የሚያሳይ ፊልም መመልከት ወይም ስለዚህ ጉዳይ ማንበብ ስህተት እንደሆነ ግልጽ ነው።

  •   “የሥጋ ሥራዎች የታወቁ ናቸው፤ እነሱም፦ ዝሙት፣ ርኩሰት፣ . . . እነዚህን የመሳሰሉ ናቸው። እነዚህን በተመለከተ አስቀድሜ እንዳስጠነቀቅኳችሁ ሁሉ አሁንም አስጠነቅቃችኋለሁ፤ እንዲህ ያሉትን ነገሮች የሚፈጽሙ የአምላክን መንግሥት አይወርሱም።” (ገላትያ 5:19-21) አምላክ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ብሎም በሳይበርሴክስ፣ በፎን ሴክስና በሴክስቲንግ የሚካፈሉ ሰዎችን የሚመለከታቸው ርኩስ እንደሆኑ ወይም ብልሹ ሥነ ምግባር እንዳላቸው አድርጎ ነው። እንዲህ ያለ ልማድ የአምላክን ሞገስ ሙሉ በሙሉ ሊያሳጣን ይችላል።