በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የራእይ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

የራእይ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የራእይ መጽሐፍ በግሪክኛ አፖካሊፕሲስ ተብሎ ይጠራል፤ ትርጉሙም “የተሸፈነን ነገር መግለጥ” ማለት ነው። ይህ ስያሜ ስለ ራእይ መጽሐፍ ትርጉም ይነግረናል፤ ይኸውም መጽሐፉ ሚስጥር ሆነው የቆዩ እንዲሁም መጽሐፉ ከተጻፈ ከረጅም ጊዜ በኋላ የሚፈጸሙ ነገሮችን እንደሚገልጥ ያስገነዝበናል። በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ትንቢቶች ገና አልተፈጸሙም።

የራእይ መጽሐፍ ይዘት

  •   መግቢያ።—ራእይ 1:1-9

  •   ኢየሱስ ለሰባቱ ጉባኤዎች የላካቸው ደብዳቤዎች።—ራእይ 1:10–3:22

  •   አምላክ በሰማይ ባለው ዙፋኑ ላይ ሆኖ በራእይ ታየ።—ራእይ 4:1-11

  •   ተከታታይ ክንውኖችን የሚያሳዩ ራእዮች፦

    •   ሰባት ማኅተሞች።—ራእይ 5:1–8:6

    •   ሰባት መለከቶች፤ የመጨረሻዎቹ ሦስት መለከቶች ሦስት ወዮታዎች እንደሚመጡ ያሳያሉ።—ራእይ 8:7–14:20

    •   ሰባት ሳህኖች፤ እያንዳንዳቸው በምድር ላይ የሚመጣን መለኮታዊ ፍርድ የሚወክሉ መቅሰፍቶችን ይዘዋል።—ራእይ 15:1–16:21

    •   የአምላክ ጠላቶች ሲጠፉ የሚያሳዩ ራእዮች።—ራእይ 17:1–20:10

    •   በሰማይና በምድር የሚወርደውን የአምላክ በረከት የሚያሳዩ ራእዮች።—ራእይ 20:11–22:5

  •   መደምደሚያ።—ራእይ 22:6-21

የራእይ መጽሐፍን ለመረዳት የሚያስችሉ ቁልፎች

  1.   መልእክቱ አዎንታዊ እንጂ የአምላክ አገልጋዮችን የሚያስፈራና በፍርሃት እንዲርዱ የሚያደርግ አይደለም። ብዙ ሰዎች የራእይ መጽሐፍ ስያሜውን ያገኘበትን አፖካሊፕስ የሚለውን ቃል ከውድመት ጋር ቢያያይዙትም የመጽሐፉ መግቢያና መደምደሚያ እንደሚያሳየው መጽሐፉን የሚያነብቡና በውስጡ ያለውን ሐሳብ ተረድተው በሥራ ላይ የሚያውሉ ሰዎች ደስታ ያገኛሉ።—ራእይ 1:3፤ 22:7

  2.   የራእይ መጽሐፍ በርካታ “ምልክቶች” የያዘ ሲሆን የእነዚህን ምልክቶች ትርጉም ቃል በቃል ልንወስድ አይገባም።—ራእይ 1:1

  3.   በመጽሐፉ ውስጥ የተገለጹ በርካታ ነገሮችና ምልክቶች ቀደም ሲል በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ውስጥ ተካትተዋል፦

  4.   ራእዮቹ መፈጸም የጀመሩት ‘በጌታ ቀን’ ማለትም በ1914 የአምላክ መንግሥት ሲቋቋምና ኢየሱስ ንጉሥ ሆኖ መግዛት ሲጀምር ነው። (ራእይ 1:10) በመሆኑም በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ያሉት ትንቢቶች በዋነኝነት ፍጻሜያቸውን የሚያገኙት በዘመናችን እንደሆነ መጠበቅ እንችላለን።

  5.   የራእይ መጽሐፍን ለመርዳት የሚያስፈልገን ነገር የቀሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ለመረዳት ከሚያስፈልገን ነገር ጋር ተመሳሳይ ነው፤ ይህም ከአምላክ የሚገኘውን ጥበብና መጽሐፉን የተረዱ ሰዎች የሚያደርጉልንን እገዛ ይጨምራል።—የሐዋርያት ሥራ 8:26-39፤ ያዕቆብ 1:5