በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ድህነት የማይኖርበት ዓለም ይመጣል?

አምላክ ድህነት የሌለበት ዓለም የሚያመጣው እንዴት ነው?—ማቴዎስ 6:9, 10

የከፋ ድህነት በሚያስከትለው የምግብ እጥረትና በሽታ ሳቢያ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ይሞታሉ። ምንም እንኳ ሀብታም የሆኑ አገሮች ቢኖሩም አብዛኛው የሰው ዘር ግን አሁንም በድህነት እየማቀቀ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ድህነት ከሰው ልጆች ጋር የኖረ ችግር እንደሆነ ይናገራል።—ዮሐንስ 12:8ን አንብብ።

ድህነትን ለማጥፋት መላውን ዓለም የሚገዛ አንድ መንግሥት ያስፈልጋል። ይህ መንግሥት በምድር ላይ ያለው ሀብት ለሁሉም እኩል እንዲዳረስ ለማድረግና ለድህነት ዋነኛ መንስኤ የሆነውን ጦርነትን ለማስወገድ ኃይል ያለው ሊሆን ይገባል። አምላክ እንደዚህ ዓይነት መንግሥት ለማምጣት ቃል ገብቷል።—ዳንኤል 2:44ን አንብብ።

ድህነትን ማጥፋት የሚችለው ማን ነው?

አምላክ ልጁን ኢየሱስን በመላው የሰው ዘር ላይ እንዲገዛ ሾሞታል። (መዝሙር 2:4-8) ኢየሱስ ድሆችን ከችግራቸው የሚገላግላቸው ከመሆኑም ሌላ ጭቆናንና ዓመፅን ያጠፋል።—መዝሙር 72:8, 12-14ን አንብብ።

ኢየሱስ በትንቢት የተነገረለት “የሰላም መስፍን” እንደመሆኑ መጠን በዓለም ላይ ሰላምና ደህነት ያሰፍናል። ከዚያም በምድር ላይ ያለ ሁሉ የግል ንብረቱ በሆነ ቤት ውስጥ የሚኖር ሲሆን አርኪ ሥራና የተትረፈረፈ ምግብ ያገኛል።—ኢሳይያስ 9:6, 7ን እና 65:21-23ን አንብብ።