በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 አገሮችና ሕዝቦች

አዘርባጃንን እንጎብኝ

አዘርባጃንን እንጎብኝ

አዘርባጃን በደቡባዊ ካውካሰስ ከሚገኙት ሦስት አገሮች ትልቋ ነች። ከአንድ ሺህ ዓመታት ገደማ በፊት የቱርኪክ ጎሣዎች በዚህ አካባቢ በብዛት መስፈር ጀመሩ። እነዚህ ሰፋሪዎች የአካባቢውን ነዋሪዎች አንዳንድ ባሕሎች የተቀበሉ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ደግሞ ከሰፋሪዎቹ ባሕሎች የተወሰኑትን ወርሰዋል። በመሆኑም የአዘርባጃን ቋንቋ ከቱርክና ከቱርክመን ቋንቋ ጋር መቀራረቡ የሚያስገርም አይደለም።

የአዘርባጃን ሰዎች (አዜሪዎች) ተጫዋችና ሰው ወዳድ በመሆናቸው ይታወቃሉ። ቤተሰቦች የሚቀራረቡ ሲሆን ዘመዳሞች በችግር ጊዜ አንዳቸው ለሌላው መድረሳቸው የተለመደ ነው።

አዜሪዎች ሙዚቃና ግጥም ይወዳሉ። ሙጋም የሚባል የሙዚቃ ዓይነት ያላቸው ሲሆን ዘፋኙ በባሕላዊ የሙዚቃ መሣሪያዎች ታጅቦ ጥንታዊ የአዜሪ ግጥሞችን ይደረድራል። የሙጋም አቀንቃኝ፣ ጥንታዊ የሙጋም ሙዚቃዎችን ጠንቅቆ የሚያውቅ እንዲሁም ዜማዎችን ወዲያው የመድረስ ችሎታ ያለው ሊሆን ይገባል።

በአዘርባጃን ባሕል ሻይ ትልቅ ቦታ አለው

 በአዘርባጃን ባሕል ሻይ ትልቅ ቦታ አለው። ሻይ አነስ ባሉ ብርጭቆዎች ከስኳር እንክብል ጋር ይቀርባል፤ የለውዝ ዝርያ የሆኑ ፍሬዎች እና ዘቢብም አብረው ሊቀርቡ ይችላሉ። ሻይ ቤቶች በትናንሽ ከተሞች ሳይቀር ይገኛሉ።

ከአገሪቱ በስተ ምሥራቅ የሚገኘው የካስፒያን ባሕር ስተርጅን የሚባለው የዓሣ ዝርያ መኖሪያ ነው። ቤሉጋ የሚባለው የስተርጅን ዝርያ ከ100 ዓመት በላይ ሊኖር ይችላል። እስካሁን ከተያዙት ትላልቅ ስተርጅኖች አንዱ 8.5 ሜትር ርዝመትና 1,297 ኪሎ ግራም ክብደት አለው! ብላክ ካቪያር ተብለው የሚጠሩት የስተርጅን እንቁላሎች ታዋቂና ውድ ናቸው፤ ይህም ስተርጅኖች ተፈላጊ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

አዜሪዎች ስለ አምላክ መነጋገር የሚወዱ ሃይማኖተኛ ሰዎች ናቸው። አብዛኞቹ የአዘርባጃን ነዋሪዎች ሙስሊሞች ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ሌሎች ሃይማኖቶችም ይገኛሉ፤ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ሲሆን ከእነዚህም ብዙዎቹ የአዘርባጃን ተወላጆች ናቸው።

የአዜሪ ባሕላዊ ሙዚቀኞች

ይህን ታውቅ ነበር?

የይሖዋ ምሥክሮች ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ በመጠቀም በመላው ዓለም በሚሊዮን ከሚቆጠሩ ሰዎች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ያጠናሉ። ይህ መጽሐፍ አዘርባጃኒን ጨምሮ ከ250 በሚበልጡ ቋንቋዎች ይገኛል።