ንቁ! ሐምሌ 2013 | ለሰው ልጆች ችግሮች መፍትሔ የሚያስገኘው የአምላክ መንግሥት ነው

ይህ እትም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሕዝብ ተቃውሞዎች የተስፋፉበትን ምክንያት እንዲሁም መፍትሔ ማግኘት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያብራራል።

ከዓለም አካባቢ

ከርዕሰ ጉዳዮቹ መካከል፦ በሥራ አመልካቾች ላይ የሚደረግ መድልዎ እና በአውስትራሊያ በትንባሆ ኩባንያዎች ላይ የወጣ አዲስ ሕግ።

ለቤተሰብ

ልጆች እልኸኛ ሲሆኑ ምን ማድረግ ይቻላል?

ልጃችሁ እልኸኛ ቢሆን ምን ማድረግ ትችላላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ተፈታታኝ ሁኔታ ለመወጣት ይረዳችኋል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

ተቃውሞ ማሰማት መፍትሔ ይሆናል?

ሰዎች ተቃውሟቸውን መግለጻቸው ለውጥ ለማምጣት የሚያስችል ከፍተኛ ኃይል ሊኖረው ይችላል። ይሁን እንጂ ለፍትሕ መጓደል፣ ለሙስና እና ለጭቆና መፍትሔ ሊያስገኝ ይችላል?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

የፍትሕ መጓደል የሌለበት ቦታ አልነበረም

በሰሜን አየርላንድ የተወለደ አንድ ወጣት እውነተኛ ፍትሕ ማግኘት ስለሚቻልበት መንገድ አመለካከቱን እንዲቀይር ያደረገው ምንድን ነው?

የበረሃዋን ድመት ተዋወቁ

ስለ በረሃዋ ድመት (ሳንድ ካት) ሰምተህ ታውቃለህ? ስለዚህች ድመት እና በቀላሉ የማትገኝበትን ምክንያት እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

አገሮችና ሕዝቦች

አዘርባጃንን እንጎብኝ

የአዘርባጃን ሰዎች (አዜሪዎች) ተጫዋችና ሰው ወዳድ ናቸው። ስለ አገራቸውና ስለ ባሕላቸው እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

የአምላክ መንግሥት

አንዳንድ ሰዎች፣ የአምላክ መንግሥት በአማኞች ልብ ውስጥ ያለ ነገር እንደሆነ እንዲሁም በሰብዓዊ ጥረት ይህን መንግሥት ማምጣት እንደሚቻል ያምናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል?

ንድፍ አውጪ አለው?

የአርክቲኩ የመሬት አደሴ ቁኒ አስገራሚ አንጎል

ይህ ትንሽ እንስሳ የሰውነቱ የሙቀት መጠን ከዜሮ በታች በሚወርድበት ወቅት በሕይወት መትረፍ የሚችለው እንዴት ነው?

በተጨማሪም . . .

የጤና ችግር ቢኖርብኝ ምን ላድርግ? (ክፍል 2)

አንዳንድ ወጣቶች ከባድ የጤና ችግር ቢያጋጥማቸውም በሽታቸውን እንዲቋቋሙና አዎንታዊ አመለካከት እንዲይዙ የረዳቸው ምን እንደሆነ ራሳቸው የተናገሩትን ተመልከት።

የያዕቆብ ወንዶች ልጆች ታሪክ

ወንድምህ፣ እህትህ ወይም ጓደኛህ አንተ በጣም የምትፈልገውን ነገር ሲያገኙ ምን ዓይነት አመለካከት ሊኖርህ ይገባል?