በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በዛሬው ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

በዛሬው ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

በፍጥነት በሚለዋወጠው በዚህ ዓለም ውስጥ፣ የምታደርጋቸው ውሳኔዎች ዘላቂ ጥቅም እንደሚያስገኙልህ መተማመን የምትችለው እንዴት ነው? ዛሬ ትክክል ተደርጎ የሚቆጠረው ነገር ነገ ስህተት ተደርጎ እንደማይቆጠር እርግጠኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ መቼም ቢሆን የማትቆጭበት ውሳኔ ለማድረግ ይረዳሃል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስን የሰጠን ፈጣሪያችን ነው፤ እሱ ደግሞ እውነተኛ ደስታና አስተማማኝ ሕይወት የሚያስገኝልን ምን እንደሆነ ያውቃል።

“መልካም የሆነውን ነግሮሃል።”—ሚክያስ 6:8

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ጠቃሚ ምክር ልንተማመንበት እንችላለን። “አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ” ነው።—መዝሙር 111:8

በዚህ ተለዋዋጭ ዓለም ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስ ሊረዳህ የሚችለው እንዴት እንደሆነ ለመመርመር ለምን አትሞክርም?