በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2024 | ትክክል ወይስ ስህተት?​—አስተማማኝ መመሪያ ከየት ይገኛል?

ትክክል እና ስህተት የሆነውን ነገር የምትወስነው እንዴት ነው? ብዙዎች በሕሊናቸውና በተማሯቸው እሴቶች ላይ ተመሥርተው ውሳኔ ያደርጋሉ። አንዳንዶች ደግሞ ውሳኔ የሚያደርጉት በሌሎች ሰዎች አመለካከት ላይ ተመሥርተው ነው። አንተስ ትክክል እና ስህተት የሆነውን ነገር የምትወስነው ምንን መሠረት አድርገህ ነው? ለአንተም ሆነ ለቤተሰብህ ዘላቂ ጥቅም የሚያስገኝ ውሳኔ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

 

ትክክል ወይስ ስህተት? በሁላችንም ፊት የተደቀነ ጥያቄ

አንድ ነገር ትክክል ነው ወይስ ስህተት የሚል ጥያቄ ሲፈጠርብህ መመሪያ የምታገኘው ከየት ነው?

ትክክል ወይስ ስህተት? ብዙዎች የሚመሩት በምንድን ነው?

ትክክልና ስህተት የሆነውን ነገር በተመለከተ ውሳኔ ስናደርግ በራሳችን ወይም በሌሎች ስሜት ልንመራ እንችላለን። ሆኖም ይበልጥ አስተማማኝ የሆነ የመመሪያ ምንጭ ይኖር ይሆን?

ትክክል ወይስ ስህተት? መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጠናል

መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ እንደያዘ እርግጠኛ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

ትክክል ወይስ ስህተት? ውጤታማ የሆነ መመሪያ

በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጤታማና አስተማማኝ መመሪያ ያገኙባቸውን አራት የሕይወት ዘርፎች ተመልከት።

በዛሬው ጊዜ አስተማማኝ መመሪያ ማግኘት የምትችለው ከየት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ መቼም ቢሆን የማትቆጭበት ውሳኔ እንድታደርግ ይረዳሃል።