በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

በቅርብ የታዩ የሚለውን ገጽታ መጠቀም—iOS

በቅርብ የታዩ የሚለውን ገጽታ መጠቀም—iOS

JW Library በቅርቡ ያነበብከውን ርዕስ ወይም ምዕራፍ መዝግቦ የሚይዝ ገጽታ አለው። ይህም ቀደም ብለህ ያነበብከውን ጥቅስ በፍጥነት ለማውጣት ይረዳሃል።

በቅርብ የታዩ የሚለውን ገጽታ ለመጠቀም ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 በቅርብ የታዩትን መክፈት

በቅርቡ ያነበብካቸውን ጥቅሶች ለማየት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ቁልፍ ተጭነህ ቆይ። ወደምትፈልገው ጥቅስ ለመመለስ በቅርብ የታዩ ከሚለው ውስጥ የምትፈልገውን ተጫን።

በቅርቡ ያነበብካቸውን ጽሑፎች ለማየት የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ቁልፍ ተጭነህ ቆይ። በቅርብ የታዩ ርዕሶችን ለመክፈት ከዝርዝሩ ውስጥ የምትፈልገውን ተጫን።

 በቅርብ የታዩትን ማጥፋት

በቅርብ የታዩ የሚለውን ለመክፈት መጽሐፍ ቅዱስ ወይም የሕትመት ውጤቶች የሚለውን ቁልፍ ተጭነህ ቆይ። ዝርዝሩን ለማጥፋት አጥፋ የሚለውን ቁልፍ ተጫን።

ይህ ገጽታ የወጣው ግንቦት 2014 ሲሆን እትሙ JW Library 1.2 ነው፤ ይህ እትም iOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።