በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም​—iOS

መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም​—iOS

JW Library በዋነኝነት የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት እንዲረዳ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሶችን ለማውረድና ለመጠቀም ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 መጽሐፍ ቅዱስ ማውረድ

የተለያዩ ትርጉሞችን በማውረድ ኢንተርኔት ሳይኖርም ማንበብና ማጥናት ትችላለህ።

  • መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ስትጫን የመጻሕፍቱን ዝርዝር ታገኛለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን በመጫን የተለያዩ ትርጉሞችን ማግኘት ትችላለህ። ብዙ ጊዜ የምትጠቀምባቸው ቋንቋዎች በዝርዝሩ ውስጥ ከላይ ይገኛሉ። የቋንቋውን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሙን ስም በመጻፍም መፈለግ ትችላለህ። ለምሳሌ “int” ብለህ በመጻፍ በእንግሊዝኛ የሚገኘውን ኪንግደም ኢንተርሊኒየር ወይም “port” ብለህ በመጻፍ በፖርቱጋልኛ የሚገኙ መጽሐፍ ቅዱሶችን በሙሉ ማግኘት ትችላለህ።

  • ያላወረድካቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች የደመና ምልክት ይታይባቸዋል። መጽሐፍ ቅዱሱን ለማውረድ ቋንቋውን ተጫን። መጽሐፍ ቅዱሱን ስታወርድ የደመናው ምልክት ይጠፋል። ለማንበብ ስትፈልግ ያወረድከውን መጽሐፍ ቅዱስ ተጫን።

የምትፈልገውን መጽሐፍ ቅዱስ በዝርዝሩ ውስጥ ካላገኘህ ትንሽ ቆይተህ ሞክር። አዳዲስ ትርጉሞች ሲወጡ በዝርዝሩ ውስጥ ይካተታሉ።

 መጽሐፍ ቅዱሱን ማጥፋት

አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ካልፈለግከው ወይም ተጨማሪ ማስቀመጫ ቦታ ለማግኘት ከፈለግክ ልታጠፋው ትችላለህ።

የመጽሐፍ ቅዱሶችን ዝርዝር ለማግኘት የቋንቋ ምልክቱን ተጫን። ማጥፋት የምትፈልገውን መጽሐፍ ቅዱስ ከግራ ወደ ቀኝ አንሸራት፤ ከዚያም አጥፋ የሚለውን ተጫን።

 መጽሐፍ ቅዱሱን ማደስ

አንዳንድ ጊዜ ያወረድካቸው መጽሐፍ ቅዱሶች መታደስ ያስፈልጋቸው ይሆናል።

መታደስ በሚያስፈልጋቸው ላይ አነቃቃ የሚል ምልክት ይታያል። መጽሐፍ ቅዱሱን ስትጫን መታደስ እንደሚያስፈልገው የሚጠቁም መልእክት ይታያል። ለማደስ ከፈለግክ አውርድ የሚለውን ተጫን፤ ያልታደሰውን ማንበብ ከፈልግክ ግን በኋላ የሚለውን ተጫን።

ይህ ገጽታ የወጣው የካቲት 2015 ሲሆን እትሙ JW Library 1.4 ነው፤ ይህ እትም በiOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር​—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።