በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

JW Library መጠቀም ጀምር​—iOS

JW Library መጠቀም ጀምር​—iOS

JW Libraryን ለመጠቀም በመምረጥህ ደስ ብሎናል። ይህ አፕሊኬሽን የተዘጋጀው መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት እንዲረዳህ ነው። የአፕሊኬሽኑን ዋና ዋና ገጽታዎች ለማግኘት ከስክሪኑ ግርጌ ላይ የሚገኙትን ቁልፎች መጠቀም ትችላለህ።

መጽሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ክፍል የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ለማንበብና ለመጫን ያስችልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ የመጽሐፉን ስም ከዚያም ምዕራፉን ተጫን። በምታነብበት ወቅት የግርጌ ማስታወሻዎችን፣ የኅዳግ ማጣቀሻዎችንና አቻ ትርጉሞችን በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ መመልከት ትችላለህ።

 ሌላ ጥቅስ ለማውጣት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን እንደገና ተጫን፤ በዚህ ጊዜ የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍትን ዝርዝር ታገኛለህ።

የሕትመት ውጤቶች

የሕትመት ውጤቶች በሚለው ክፍል ውስጥ የተለያዩ ጽሑፎችን እንዲሁም የኦዲዮና የቪዲዮ ፕሮግራሞችን ታገኛለህ። የምትፈልገውን ጽሑፍ ለማንበብ መጀመሪያ ጽሑፉን ከዚያም ርዕሱን ተጫን። በምታነብበት ወቅት ጥቅሶቹንም ማየት ትችላለህ። ጥቅሱን ስትጫነው በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ ይከፈትልሃል። በማጥኛ ሣጥኑ ውስጥ ያለው ሊንክ ስትጫን ጥቅሱ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይወጣልሃል።

 ሌላ ጽሑፍ መክፈት ከፈለግክ የሕትመት ውጤቶች የሚለውን በድጋሚ ተጫን፤ ይህም ወደ ሕትመት ውጤቶቹ ዝርዝር ይወስድሃል።

የዕለት ጥቅስ

የዕለቱን ጥቅስ ለማየት የዕለት ጥቅስ የሚለውን ተጫን።

 ስብሰባዎች

በዚህ ሳምንት በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ የሚጠኑትን ጽሑፎች ለማየት ስብሰባዎች የሚለውን ተጫን።

 ኢንተርኔት

ኢንተርኔት በሚለው ክፍል ውስጥ ወደ ድረ ገጾቻችን የሚወስዱ ሊንኮች ይገኛሉ።

 አዳዲስ ገጽታዎች

JW Library ላይ ያሉትን አዳዲስ ገጽታዎች በሙሉ ለማግኘት አፕሊኬሽኑን በየጊዜው ማደስ ያስፈልግሃል።

ለምትጠቀምበት መሣሪያ የተዘጋጀውን አዲስ iOS መጫንህ ጠቃሚ ነው። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ተመልከት፦ https://support.apple.com/en-us/HT204204.

አዳዲስ ገጽታዎች ሲመጡ ያለምንም ጥያቄ እንዲታደስልህ ከፈለግክ የመሣሪያህ ማስተካከያ ውስጥ በመግባት ማስተካከል ትችላለህ። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተለውን ሊንክ ተመልከት፦ https://support.apple.com/en-us/HT202180.