በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

ጽሑፍ ማቅለም—iOS

ጽሑፍ ማቅለም—iOS

JW Library ላይ ጽሑፎችን ስታነብብ ቃላትን ወይም ሐረጎችን ማቅለም ትችላለህ።

ጽሑፍ ለማቅለም ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 ጽሑፍ ማቅለም

አንድን ጽሑፍ በሁለት መንገዶች ማቅለም ይቻላል።

አንድን ቃል ተጭነህ በመቆየት ምረጥ። ጫፍ ላይ ያሉትን ምልክቶች በማንቀሳቀስ የምታቀልመውን መጠን መምረጥ ትችላለህ። ቃሉን ስትጫን ከሚመጣው ማውጫ ውስጥ የማቅለሚያ ምልክቱን ተጫን፤ ከዚያም የምትፈልገውን ቀለም ምረጥ።

አንድን ቃል ወይም ሐረግ በአንዴ ለማቅለም ተጭነህ ያዘው፤ ከዚያም ጎትተው። ስትጎትት ጽሑፉን እያቀለምክ ትሄዳለህ። ስትጨርስ ለአጭር ጊዜ ማውጫው ይታያል። ይህን ማውጫ በመጠቀም ቀለም መቀየር ወይም ማጥፋት ትችላለህ።

 ቀለሙን መቀየር

ቀለም ለመለወጥ ያቀለምከውን ጽሑፍ ተጫን፤ ከዚያም ሌላ ቀለም ምረጥ። ቀለሙን ለማጥፋት ያቀለምከውን ጽሑፍ ተጫን፤ ከዚያም አጥፋ የሚለውን ቁልፍ ተጫን።

ይህ ገጽታ የወጣው ኅዳር 2015 ሲሆን እትሙ JW Library 1.6 ነው፤ ይህ እትም iOS 7.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።