በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

ለንባብ በሚያመች መንገድ ማስተካከል—iOS

ለንባብ በሚያመች መንገድ ማስተካከል—iOS

JW Library፣ ለንባብ ልትጠቀምባቸው የምትችል በርካታ ገጽታዎች አሉት። እነዚህ ገጽታዎች አንድን ርዕስ ለማንበብ ስትከፍት በስክሪኑ አናት በስተቀኝ በኩል ይወጣሉ።

ከእነዚህ ገጽታዎች መካከል አንዳንዶቹን ለማግኘት ሌሎች የሚለውን መጫን ሊያስፈልግህ ይችላል።

ለንባብ በሚያመች መንገድ ለማስተካከል ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 ቋንቋ መለወጥ

እያነበብክ ያለውን ምዕራፍ ወይም ርዕስ በሌላ ቋንቋም ማንበብ ትችላለህ።

  • ቋንቋዎች የሚለውን ስትጫን የምታነብበው ጽሑፍ የሚገኝባቸውን ቋንቋዎች ዝርዝር በሙሉ ማየት ትችላለህ። በዝርዝሩ ውስጥ ከላይ የሚታዩት አዘውትረህ የምትጠቀምባቸው ቋንቋዎች ናቸው። ቀለል ባለ ቋንቋ የተዘጋጁ መጠበቂያ ግንብ መጽሔቶችንም እዚሁ ማግኘት ትችላለህ። የምትፈልገውን ቋንቋ ስም በመጻፍም ቋንቋውን ማግኘት ትችላለህ።

  • ያላወረድካቸው ቋንቋዎች የደመና ምልክት ይታይባቸዋል። ጽሑፉን ለማውረድ ቋንቋውን ተጫን። ጽሑፉን ስታወርድ የደመናው ምልክት ይጠፋል። ያወረድከውን ጽሑፍ ለማንበብ ቋንቋውን ተጫን።

 የፊደል መጠን ማስተካከል

የጽሑፉን መጠን፣ ለማንበብ በሚያመችህ መንገድ ማስተካከል ትችላለህ።

የፊደል መጠን ማስተካከያ የሚለውን ተጫን፤ ከዚያም የፊደል መጠን ማስተካከያውን በማንቀሳቀስ የጽሑፉን መጠን መቀነስ ወይም መጨመር ትችላለህ። የምታደርገው ማስተካከያ አፕሊኬሽኑ ውስጥ የሚገኙትን የሁሉንም ጽሑፎች የፊደል መጠን ይቀይረዋል።

 ምስል ወይም ጽሑፍ መመልከት

አንዳንድ ጽሑፎችን በምስል ወይም በጽሑፍ መልክ ማየት ይቻላል። የምትፈልገውን ቁልፍ በመጫን ከአንዱ ወደ ሌላው መቀያየር ትችላለህ።

  • ምስል አሳይ፦ ይህ ምርጫ ጽሑፉ ሲታተም የሚኖረውን ገጽታ ያሳያል። አንዳንዶች እንደ መዝሙር መጽሐፍ ያሉ ጽሑፎችን በምስል መልክ ማየትን ሊመርጡ ይችላሉ፤ ይህም የሙዚቃ ኖታውን እንዲያዩ ያስችላቸዋል።

  • ጽሑፍ አሳይ፦ ይህ ምርጫ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በሊንክ መልክ ያስቀምጣል፤ ሊንኩን ስትጫን በመረጥከው የፊደል መጠን ጥቅሱን ያወጣልሃል።

 መክፈቻ ምረጥ

መክፈቻ ምረጥ የሚለው ገጽታ በJW Library ላይ የሚገኙትን ነገሮች በሌሎች አፕሊኬሽኖች ለመክፈት ያስችልሃል።

መክፈቻ ምረጥ የሚለውን ቁልፍ ስትጫን የተለያዩ መክፈቻዎችን ያስመርጥሃል። ለምሳሌ በኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ክፈት የሚለውን ቁልፍ ስትጫን እያነበብክ ያለውን ጽሑፍ የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት ላይ ይከፍትልሃል።

 መጽሐፍ ቅዱሶችን ማስተካከል

በአንድ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኝን ጥቅስ ስትጫን ጥቅሱ በተለያዩ ትርጉሞች ይወጣል። ካወረድካቸው መጽሐፍ ቅዱሶች መካከል ጥቅሱን ማየት የምትፈልግባቸውን ትርጉሞች ለመምረጥ እንደምትፈልገው አስተካክል የሚለውን ተጫን።

የመደመር ወይም የመቀነስ ምልክቶቹን በመጫን አንድ ትርጉም በዝርዝሩ ውስጥ እንዲካከተት ወይም ከዚያ እንዲወጣ ማድረግ ትችላለህ። የዝርዝሩን ቅደም ተከተል ለማስተካከል አንድን መጽሐፍ ቅዱስ ወደ ላይ ወደ ታች አንቀሳቅስ።

JW Library ላይ ተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱሶችን መጫን የምትችለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ “መጽሐፍ ቅዱሶችን ማውረድና መጠቀም—iOS” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

ይህ ገጽታ የወጣው የካቲት 2015 ሲሆን እትሙ JW Library 1.4 ነው፤ ይህ እትም iOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።