በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ጨዋነት ቀረ እንዴ?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ጨዋነት ቀረ እንዴ?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ጨዋነት እየጠፋ ነው። አክብሮት የጎደላቸው ታካሚዎች በሐኪሞች ላይ ይጮኻሉ፤ ሥነ ምግባር የጎደላቸው የምግብ ቤት ደንበኞች አስተናጋጆችን ይሳደባሉ፤ ሥርዓት አልበኛ ተጓዦች የበረራ አስተናጋጆችን ይማታሉ፤ ባለጌ ልጆች በአስተማሪዎቻቸው ላይ ያሾፋሉ፣ ይዝታሉ ይባስ ብሎም ጥቃት ይሰነዝራሉ፤ አንዳንድ ፖለቲከኞች በቅሌት ይያዛሉ፤ ሌሎች ፖለቲከኞች ደግሞ ጨዋነታቸውን ለማስመሥከር ይሞክራሉ።

 መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥ ጨዋ ምግባር የሚባለው ምን እንደሆነ ይናገራል። በተጨማሪም በዛሬው ጊዜ ጨዋነት የጠፋው ለምን እንደሆነ ያብራራል።

ጨዋነት የጠፋው ለምንድን ነው?

 በዛሬው ጊዜ ጨዋነት ማለትም ጥሩ፣ ተገቢ እና ተቀባይነት ያለው ምግባር በመላው ዓለም እያሽቆለቆለ ነው።

  •   በቅርቡ የተደረገ አንድ ጥናት እንደሚያሳየው አሜሪካውያን በዛሬው ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስ የሚታየው ሥነ ምግባር ካለፉት 22 ዓመታት ሁሉ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደደረሰ ይሰማቸዋል።

  •   በ28 አገሮች ውስጥ በሚገኙ 32,000 ሰዎች ላይ የተደረገ ሌላ ጥናት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉት ሰዎች መካከል 65 በመቶ የሚሆኑት የሰው ልጆች የሥነ ምግባር ደረጃ በሕይወታቸው አይተው በማያውቁት መጠን እንዳሽቆለቆለ ይሰማቸዋል።

 መጽሐፍ ቅዱስ በዘመናችን እንዲህ ያለ ምግባር እንደሚስፋፋ ትንቢት ተናግሯል።

  •   “በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ ይህን እወቅ። ምክንያቱም ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ፣ ገንዘብ የሚወዱ፣ ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች፣ ተሳዳቢዎች፣ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፣ የማያመሰግኑ፣ . . . ተፈጥሯዊ ፍቅር የሌላቸው [እና ጨካኞች ይሆናሉ]።”​—2 ጢሞቴዎስ 3:1-3

 ይህ ትንቢት እየተፈጸመ ያለው እንዴት እንደሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት “መጽሐፍ ቅዱስ በዛሬው ጊዜ ስለሚኖሩ ሰዎች ባሕርይ እና ምግባር ትንቢት ተናግሯል?” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።

ጨዋ ለመሆን የሚረዳ አስተማማኝ መመሪያ

 ጨዋነት እየጠፋ ባለበት በዚህ ዓለም ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ምግባር ለማሳየት የሚረዳ አስተማማኝ መመሪያ እንደያዘ ተገንዝበዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው የሥነ ምግባር መመሪያ “አሁንም ሆነ ለዘላለም፣ ምንጊዜም አስተማማኝ” ነው። (መዝሙር 111:8) አንዳንድ ምሳሌዎችን እስቲ እንመልከት፦

  •   መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “ሰዎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር ሁሉ እናንተም አድርጉላቸው።”​—ማቴዎስ 7:12

     ትርጉሙ፦ ሌሎች በደግነትና በአክብሮት እንዲይዙን እንደምንፈልግ ሁሉ እኛም ሌሎችን በዚሁ መንገድ ልንይዝ ይገባል።

  •   መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? “አሁን አታላይነትን ስላስወገዳችሁ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።”​—ኤፌሶን 4:25

     ትርጉሙ፦ በምንናገረውና በምናደርገው ነገር ሁሉ ሐቀኞች ልንሆን ይገባል።

 ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሚከተሉትን ማንበብ ትችላለህ፦