በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

John Moore/Getty Images

ጤንነት—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

ጤንነት—የአምላክ መንግሥት ምን እርምጃ ይወስዳል?

 “ኮቪድ-19 በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ የጤና ስጋት መሆኑ አብቅቷል ማለት ዓለማችን ይህ ቫይረስ ከሚያሳድረው ተጽዕኖ ነፃ ሆናለች ማለት አይደለም። . . . ቀጣዩ ወረርሽኝ ሲከሰት፣ ደግሞም መከሰቱ አይቀርም፣ ዝግጁ ሆነን መጠበቅ አለብን።”—ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ገብረየሱስ፣ የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር፣ ግንቦት 22, 2023

 ብዙ ሰዎች ኮቪድ-19 ካስከተላቸው አካላዊና አእምሯዊ ችግሮች ጋር አሁንም እየታገሉ ነው። መንግሥታትና የጤና ተቋማት አሁን ላሉብን የጤና ችግሮች መፍትሔ መስጠት ይቅርና ወደፊት ለሚከሰት ወረርሽኝ ዝግጁ ሆነው መጠበቅ ይችሉ ይሆን?

 መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሚያስፈልገንን የጤና እንክብካቤ ስለሚያደርግልን አንድ መስተዳድር ይናገራል። የሰማይ አምላክ “መንግሥት” ወይም መስተዳድር ‘እንደሚያቋቁም’ ይናገራል። (ዳንኤል 2:44) በዚህ መንግሥት አገዛዝ ሥር “ማንኛውም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ አይልም።” (ኢሳይያስ 33:24) ሁሉም ሰው ጥሩ ጤንነትና የወጣትነት ብርታት ይኖረዋል።—ኢዮብ 33:25