በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ጥሩ ወላጅ ለመሆን ምን ያስፈልጋል?

ልጅህ አምላክን እንዲወድ ታስተምረዋለህ?

እርስ በርስ የሚዋደዱና የሚከባበሩ ወላጆች ያሏቸው ልጆች በጥሩ ሁኔታ ያድጋሉ። (ቆላስይስ 3:14, 19) ጥሩ ወላጆች ልክ እንደ ይሖዋ አምላክ ልጆቻቸውን ይወዳሉ እንዲሁም ያሞግሷቸዋል።—ማቴዎስ 3:17ን አንብብ።

የሰማዩ አባታችን አገልጋዮቹን ያዳምጣል እንዲሁም ለስሜቶቻቸው ትኩረት ይሰጣል። ወላጆችም የይሖዋን ምሳሌ በመከተል ልጆቻቸው የሚናገሩትን ማዳመጣቸው ተገቢ ነው። (ያዕቆብ 1:19) ወላጆች ልጆቻቸው የሚያሰሙትን ቅሬታ ጨምሮ ስሜታቸውን ሲገልጹ መስማት ይኖርባቸዋል።—ዘኁልቁ 11:11, 15ን አንብብ።

ልጆቻችሁን ኃላፊነት የሚሰማቸው እንዲሆኑ አድርጋችሁ ማሳደግ የምትችሉት እንዴት ነው?

ወላጅ እንደመሆንህ መጠን መመሪያ የመስጠት ሥልጣን አለህ። (ኤፌሶን 6:1) በዚህ ረገድ አምላክ የተወውን ምሳሌ ተከተል። አምላክ ግልጽ ደንቦችን በማውጣትና ደንቦቹን መተላለፍ የሚያስከትለውን መዘዝ በመግለጽ ለልጆቹ ፍቅር እንዳለው አሳይቷል። (ዘፍጥረት 3:3) አምላክ ሰዎች እንዲታዘዙት ከማስገደድ ይልቅ ትክክል የሆነውን ነገር ማድረጋቸው ምን ጥቅም እንደሚያስገኝላቸው ያስተምራቸዋል።—ኢሳይያስ 48:18, 19ን አንብብ።

ልጆችህ አምላክን እንዲወዱ የመርዳት ግብ ይኑርህ። እንዲህ ካደረግክ ከአንተ ጋር በማይሆኑበት ጊዜም ጭምር በጥበብ መመላለስ ይችላሉ። አምላክ፣ ራሱ ምሳሌ በመሆን እንደሚያስተምር ሁሉ አንተም ለልጆችህ ምሳሌ በመሆን አምላክን እንዲወዱት አስተምራቸው።—ዘዳግም 6:5-7⁠ን፤ ኤፌሶን 4:32⁠ን እና 5:1ን አንብብ።