በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች የሌሎችን ሃይማኖት ያከብራሉ?

የይሖዋ ምሥክሮች የሌሎችን ሃይማኖት ያከብራሉ?

 ሃይማኖታቸው ምንም ይሁን ምን መጽሐፍ ቅዱስ ‘ሁሉንም ሰው እንድናከብር’ የሚሰጠንን ምክር እንከተላለን። (1 ጴጥሮስ 2:17) ለምሳሌ ያህል፣ በአንዳንድ አገሮች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች ይገኛሉ። ያም ሆኖ ሌሎች ሃይማኖቶች በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ እንዲታገዱ ለማድረግ በፖለቲካ ሰዎች ወይም በሕግ አውጪዎች ላይ ጫና ለማሳደር አንሞክርም። እንዲሁም ሥነ ምግባራዊና ሃይማኖታዊ አቋማችንን በሌሎች ላይ ለመጫን በማሰብ ይህን የሚያንጸባርቅ ሕግ እንዲወጣ ቅስቀሳ አናካሂድም። ከዚህ ይልቅ ሌሎች እኛን እንዲያከብሩን እንደምንፈልግ ሁሉ እኛም ሌሎችን እናከብራለን።​—ማቴዎስ 7:12