በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አምላክ ወደ እሱ ብጸልይ ይረዳኛል?

አምላክ ወደ እሱ ብጸልይ ይረዳኛል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አዎ፣ አምላክ ከፈቃዱ ጋር የሚስማሙ ነገሮችን ከልባቸው የሚጠይቁ ሰዎችን ይረዳቸዋል። ከዚህ ቀደም ጸልየህ ባታውቅም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘አምላክ ሆይ፣ እርዳኝ’ ብለው የጸለዩ ሰዎችን ታሪክ ማንበብህ ሊያጽናናህ ይችላል። ለምሳሌ ያህል፦

  •   “እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።”—መዝሙር 109:26

  •   “እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”—መዝሙር 30:10

 እርግጥ ነው፣ እነዚህን ሐሳቦች የጻፈው ግለሰብ በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት እንደነበረው ግልጽ ነው። ያም ሆኖ አምላክ ‘ልባቸውና መንፈሳቸው የተሰበረ’ ሰዎች በሙሉ ትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ይዘው ወደ እሱ የሚቀርቡትን ጸሎት ይሰማል።​—መዝሙር 34:18

 አምላክ ሩቅ እንደሆነ ወይም የአንተ ችግር እንደማያሳስበው ተሰምቶህ ስጋት ሊያድርብህ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያላል፦ “እግዚአብሔር በከፍታ ስፍራ ቢሆንም፣ ዝቅ ያለውን ይመለከተዋል፤ ትዕቢተኛውን ከሩቅ ያውቀዋል።” (መዝሙር 138:6) እንዲያውም ኢየሱስ በአንድ ወቅት ደቀ መዛሙርቱን “የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል” ብሏቸው ነበር። (ማቴዎስ 10:30) አምላክ ስለ ራሳችን የማናውቃቸውን ጥቃቅን ነገሮች እንኳ ያውቃል። ታዲያ ስለሚያስጨንቀን ነገር ስንጸልይ እኛን ለማዳመጥ ይበልጥ ፈቃደኛ ይሆናል ብሉ ማሰቡ ምክንያታዊ አይሆንም?​—1 ጴጥሮስ 5:7