በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በስተ ግራ፦ Yasser Qudaih/Anadolu via Getty Images፤ በስተ ቀኝ፦ RONALDO SCHEMIDT/AFP via Getty Images

ነቅታችሁ ጠብቁ!

ውጊያው የሚያበቃው መቼ ነው?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ውጊያው የሚያበቃው መቼ ነው?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 13, 2024 ኢራን በእስራኤል ላይ ቀጥተኛ ጥቃት መሰንዘሯን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንዲህ ብለዋል፦ “አሁኑኑ ውጥረት ማብረድ ያስፈልጋል። ግጭት ከማባባስ መታቀብ የግድ ነው።”

 በመካከለኛው ምሥራቅ እየተካሄደ ያለው ውጊያ በመላው ዓለም ላይ እየተካሄዱ ላሉት ግጭቶች አንዱ ማሳያ ነው።

 “ዓለማችን፣ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ የአሁኑን ያህል ብዙ ደም አፋሳሽ ግጭቶች አስተናግዳ አታውቅም፤ ሁለት ቢሊዮን ሰዎች ማለትም ከዓለም ሕዝብ አንድ አራተኛው የችግሩ ገፈት ቀማሽ ሆኗል።”—የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት፣ ጥር 26, 2023

 ደም አፋሳሽ ግጭቶች ካሉባቸው አገራት መካከል እስራኤል፣ ጋዛ፣ ሶርያ፣ አዘርባጃን፣ ዩክሬን፣ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ኒጀር፣ ምያንማር እና ሄይቲ ይገኙበታል። a

 ውጊያው የሚያበቃው መቼ ነው? የዓለም መሪዎች ሰላም ማምጣት ይሳካላቸው ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

በጦርነት የታመሰች ዓለም

 ዛሬ በዓለም ላይ የምናያቸው ግጭቶች፣ ጦርነት ሙሉ በሙሉ የሚወገድበት ጊዜ እንደቀረበ ያመላክቱናል። እነዚህ ጦርነቶች መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዘመናችን የሚናገረው ትንቢት ፍጻሜ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ የምንኖርበትን ዘመን “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ” ብሎ ይጠራዋል።​—ማቴዎስ 24:3

  •   “ጦርነትና የጦርነት ወሬ ትሰማላችሁ። . . . ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳል።”​—ማቴዎስ 24:6, 7

 የዘመናችን ጦርነቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት ፍጻሜ ናቸው የምንልበትን ምክንያት ለማወቅ “‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ወይም ‘የመጨረሻው ዘመን’ ምልክት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

ጦርነቶችን ሁሉ የሚቋጭ ጦርነት

 ጦርነቶች ሁሉ መቋጫ የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ መጽሐፍ ቅዱስ አስቀድሞ ተናግሯል። ይህ ሊሳካ የሚችለው እንዴት ነው? በሰው ልጆች ጥረት አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ “ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ ታላቅ ቀን [በሚካሄደው] ጦርነት” ማለትም በአርማጌዶን ነው። (ራእይ 16:14, 16) ይህን ጦርነት ተከትሎ አምላክ ምድር ላይ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የገባው ቃል ይፈጸማል።​—መዝሙር 37:10, 11, 29

 ጦርነቶችን ሁሉ ስለሚያስወግደው የአምላክ ጦርነት ይበልጥ ለማወቅ “የአርማጌዶን ጦርነት ምንድን ነው?” የሚለውን ርዕስ አንብብ።

a ACLED “በዓለም ዙሪያ ደም አፋሳሽ ግጭቶች የተከሰቱባቸው ቦታዎች ዝርዝር” ጥር 2024