በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

panitan/stock.adobe.com

የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ

ኢየሱስ ድህነትን ያስወግዳል

ኢየሱስ ድህነትን ያስወግዳል

 ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ለሰዎች ታላቅ ፍቅር አሳይቷል፤ በተለይ ለድሆችና ለተጨነቁ ሰዎች ልዩ ፍቅር ያሳይ ነበር። (ማቴዎስ 9:36) እንዲያውም ለሰዎች ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 15:13) በቅርቡ ደግሞ፣ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ያለውን ሥልጣን ተጠቅሞ ድህነትን ከመላው ምድር ያስወግዳል።

 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ማራኪ ቃላትን በመጠቀም ኢየሱስ የሚያደርገውን ነገር ይገልጻል፦

  •   “በሕዝቡ መካከል ላሉት ችግረኞች ጥብቅና ይቁም፤ የድሃውን ልጆች ያድን።”​—መዝሙር 72:4

 ኢየሱስ ላደረገልን ነገር እንዲሁም ወደፊት ለሚያደርግልን ነገር ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? በሉቃስ 22:19 ላይ ኢየሱስ ተከታዮቹን የሞቱን መታሰቢያ እንዲያከብሩ ነግሯቸዋል። በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ ኢየሱስ በሞተበት ዕለት ላይ አንድ ስብሰባ ያደርጋሉ። እሁድ፣ መጋቢት 24, 2024 የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ አብረኸን እንድታከብር እንጋብዝሃለን።

በዓሉ የሚከበርበት ቦታ