በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ዲያብሎስን የፈጠረው አምላክ ነው?

ዲያብሎስን የፈጠረው አምላክ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 አምላክ ክፉ ወይም ዲያብሎስ አድርጎ የፈጠረው አካል የለም። ከዚህ ይልቅ አንድ የአምላክ ፍጥረት ከጊዜ በኋላ ዲያብሎስ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ አምላክ ሲናገር “ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ ትክክል ነው፤ የማይሳሳት ታማኝ አምላክ፣ ቀጥተኛና ጻድቅ አምላክም እርሱ ነው” ይላል። (ዘዳግም 32:3-5) ከዚህ ጥቅስ መመልከት እንደምንችለው ሰይጣን በአንድ ወቅት ፍጹምና ጻድቅ ከሆኑት የአምላክ መላእክት መካከል አንዱ ነበር።

 ኢየሱስ በዮሐንስ 8:44 ላይ ዲያብሎስ “በእውነት ውስጥ ጸንቶ አልቆመም” ብሎ መናገሩ በአንድ ወቅት ሰይጣን እውነተኛና ነቀፋ የሌለበት እንደነበረ ይጠቁማል።

 ይሁንና የማሰብ ችሎታ እንዳላቸው ሌሎች የይሖዋ ፍጥረታት ሁሉ በኋላ ላይ ሰይጣን የሆነው መልአክም ትክክል ወይም ስህተት የሆነውን የመምረጥ ነፃነት ነበረው። አምላክን በሚጻረር መንገድ ለመሄድ በመምረጥና የመጀመሪያዎቹ ሰብዓዊ ባልና ሚስት ከእሱ ጎን እንዲሰለፉ በማድረግ ራሱን ሰይጣን ማለትም “ተቃዋሚ” አደረገ።​—ዘፍጥረት 3:1-5፤ ራእይ 12:9