በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

አምላክ ሥላሴ ነው?

አምላክ ሥላሴ ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በርካታ አብያተ ክርስቲያናት አምላክ ሥላሴ እንደሆነ ያስተምራሉ። ይሁን እንጂ፣ ዚ ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንዲህ ይላል፦ “ሥላሴ የሚለው ቃልም ሆነ ይህን መሠረተ ትምህርት የሚደግፍ ሐሳብ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ፈጽሞ አይገኝም። . . . ይህ ትምህርት ቀስ በቀስ እየዳበረ የመጣው ከበርካታ መቶ ዘመናትና ከብዙ ክርክር በኋላ ነው።”

 እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ፣ አምላክ የሥላሴ ክፍል እንደሆነ አንድም ቦታ ላይ አይናገርም። ቀጥሎ ያሉትን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች እስቲ ልብ በል፦

 “አምላካችን እግዚአብሔር አንድ እግዚአብሔር ነው።”—ዘዳግም 6:4

 “ስምህ እግዚአብሔር የሆነው አንተ ብቻ፣ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል እንደ ሆንህ ይወቁ።”—መዝሙር 83:18

 “የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንዲችሉ ብቸኛው እውነተኛ አምላክ ስለሆንከው ስለ አንተና ስለላክኸው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እውቀት መቅሰማቸውን መቀጠል አለባቸው።”—ዮሐንስ 17:3

 ‘አምላክ አንድ ብቻ ነው።’—ገላትያ 3:20

 ታዲያ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት፣ አምላክ ሥላሴ እንደሆነ የሚናገሩት ለምንድን ነው?