በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳይኖሰሮች ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳይኖሰሮች ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዳይኖሰሮች በቀጥታ አይናገርም። ሆኖም ‘ሁሉንም ነገሮች የፈጠረው’ አምላክ እንደሆነ ይናገራል። በመሆኑም አምላክ ከፈጠራቸው ነገሮች መካከል ዳይኖሰሮችም እንደሚገኙበት ግልጽ ነው። a (ራእይ 4:11) መጽሐፍ ቅዱስ ዳይኖሰሮችን በቀጥታ ባይጠቅስም ስለተለያዩ ዓይነት ፍጥረታት ይናገራል፤ ከእነዚህ ፍጥረታት መካከል ዳይኖሰሮችም ይገኙበት ይሆናል፦

ዳይኖሰሮች የተገኙት በዝግመተ ለውጥ ነው?

 የቅሪተ አካላት ማስረጃዎች የሚያሳዩት ዳይኖሰሮች ቀስ በቀስ በዝግመተ ለውጥ እንደመጡ ሳይሆን አንድ ወቅት ላይ ወደ ሕልውና እንደመጡ ነው። ይህም እንስሳትን በሙሉ የፈጠረው አምላክ እንደሆነ ከሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ጋር ይስማማል። መጽሐፍ ቅዱስ መዝሙር 146:6 ላይ አምላክ “የሰማይ፣ የምድር፣ የባሕርና በውስጣቸው ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ” እንደሆነ ይናገራል።

ዳይኖሰሮች በምድር ላይ የነበሩት መቼ ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ የባሕርና የመሬት ፍጥረታት የተፈጠሩት በአምስተኛውና በስድስተኛው የፍጥረት ቀናት እንደሆነ ይናገራል፤ እነዚህ ቀናት ረጅም ዘመናትን ያመለክታሉ። b (ዘፍጥረት 1:20-25, 31) ስለዚህ ዳይኖሰሮች የተፈጠሩትም ሆነ በምድር ላይ የነበሩት በዚህ ረጅም ጊዜ ውስጥ ሊሆን ይችላል።

ብሄሞትና ሌዋታን ዳይኖሰሮች ናቸው?

 አይደሉም። በኢዮብ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን የእነዚህን እንስሳት ምንነት በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፤ ሆኖም ብሄሞት ጉማሬን፣ ሌዋታን ደግሞ አዞን እንደሚያመለክት ይገመታል። ይህም መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ እንስሳት ከሚሰጠው መግለጫ ጋር ይስማማል። (ኢዮብ 40:15-23፤ 41:1, 14-17, 31) ያም ሆነ ይህ “ብሄሞት” እና “ሌዋታን” የተባሉት እነዚህ እንስሳት ዳይኖሰሮች እንዳልሆኑ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። ምክንያቱም አምላክ ኢዮብን እነዚህን እንስሳት እንዲመለከት ነግሮታል፤ ኢዮብ በሕይወት የኖረው ደግሞ ዳይኖሰሮች ከምድር ላይ ከጠፉ ከረጅም ዘመን በኋላ ነው።—ኢዮብ 40:16፤ 41:8

ዳይኖሰሮች የጠፉት ለምንድን ነው?

 መጽሐፍ ቅዱስ ዳይኖሰሮች ስለጠፉበት መንገድ ምንም አይናገርም። ይሁን እንጂ ሁሉም ነገሮች የተፈጠሩት “[በአምላክ] ፈቃድ” እንደሆነ ይናገራል፤ ስለዚህ አምላክ ዳይኖሰሮችን የፈጠረበት የራሱ ዓላማ እንዳለው ግልጽ ነው። ይህ ዓላማው ከተፈጸመ በኋላ አምላክ ዳይኖሰሮች እንዲጠፉ ፈቅዷል።

a የቅሪተ አካል ማስረጃዎች ዳይኖሰሮች በምድር ላይ እንደኖሩ ያረጋግጣሉ። እንዲያውም በአንድ ወቅት የተለያየ ዓይነትና መጠን ያላቸው ዳይኖሰሮች በምድር ላይ በብዛት እንደነበሩ የቅሪተ አካል ማስረጃዎች ያሳያሉ።

b በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ቀን” የሚለው ቃል በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን ሊያመለክት ይችላል።—ዘፍጥረት 1:31፤ 2:1-4፤ ዕብራውያን 4:4, 11