በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ማክሲም ዚንችዬንኮ እና ባለቤቱ ካሪና

ጥር 23, 2024 | የታደሰው፦ ሚያዝያ 18, 2024
ዓለም አቀፋዊ ዜና

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “እምነት ላለው ሰው፣ ሁሉ ነገር ይቻላል”

ወቅታዊ መረጃ—ወንድም ተፈረደበት | “እምነት ላለው ሰው፣ ሁሉ ነገር ይቻላል”

ሚያዝያ 16, 2024 በሴቫስቶፖል የሚገኘው የናኪሞቭስኪ አውራጃ ፍርድ ቤት፣ ወንድም ማክሲም ዚንችዬንኮ ጥፋተኛ ነው በማለት የሁለት ዓመት የግዳጅ የጉልበት ሥራ በይኖበታል። ማረሚያ ተቋም ውስጥ እየኖረ በተመደበለት አካባቢ የሚሰጠውን ሥራ ማከናወን ይኖርበታል።

አጭር መግለጫ

ይሖዋ፣ ማክሲምም ሆነ የእሱን ፈቃድ የሚያደርጉ ሁሉ ለሚያሳዩት ድፍረትና ጽናት ወሮታ እንደሚከፍላቸው እንተማመናለን።​—ዕብራውያን 10:35, 36

የክሱ ሂደት

  1. ግንቦት 17, 2023

    በጽንፈኛ ድርጅት እንቅስቃሴ በመካፈል ተከሰሰ

  2. ግንቦት 22, 2023

    ቤቱ ተፈተሸ። በማክሲም እና በካሪና ላይ ምርመራ ተካሄደባቸው፤ ወደ ጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ እንዲገባ ተደረገ

  3. ግንቦት 24, 2023

    ከጊዜያዊ ማረፊያ ጣቢያ ወጥቶ የቁም እስረኛ እንዲሆን ተደረገ

  4. ሐምሌ 12, 2023

    ጉዳዩ በፍርድ ቤት መታየት ጀመረ